usd car ኢስት ዌስት ኢትዮ ትራንስፖረት

usd car ኢስት ዌስት ኢትዮ ትራንስፖረት

Walia Tender

የጨረታ ማስታወቂያ 

የጨረታ ቁጥር ኢዌስት/02/2013 

ኢስት ዌስት ኢትዮ ትራንስፖረት ኃየተያግልማህበር የድርጅቱ ንብረት የሆኑ የተለያዩ ያገለገሉ ከባድና ቀላል ተሸከርካሪዎቸን ፤ የደረቅና ቦቴ ተሳቢዎችን ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። 

ስለሆነም በጨረታ መካፈል የሚፈልግ ድርጅት ወይም ግለሰብ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ሁኔታዎች በማሟላት ቀርበዉ መወዳደር ይችላሉ። 

  1.  ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘዉን የጨረታ ሰነድ ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ከመስከረም 06 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ እሰክ መስከረም 28 ቀን 2013 ዘወትር በሥራ ሰዓት ቃሊቲ በሚገኘዉ ከድርጅቱ ዋናዉ መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 በመምጣት የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር ከፍለዉ መዉሰድ ይችላሉ። 
  2.  ተጫራቾች ማስታወቂያዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 28 ቀን የጨረታ ሰነድ ገዝተዉ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ባለዉ ጊዜ ዉስጥ ተሸከርካሪዎችን ቃሊቲ ካዲስኮ ቀለም ፋብሪካ አካባቢ በሚገኘዉ ዋናዉ መ/ቤት ጋራዥና ቃሊቲ ከጣና ኢንጂነሪንግ ወረድ ብሎ በሚገኘዉ የድርጅቱ ተሸከርካሪ ማቆሚያ በመምጣት መመልከት ይችላሉ። 
  3. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ተሸከርካሪ ለእያንዳንዱ የጨረታ መነሻ ዋጋ አስራ አምስት በመቶ (15%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ( Bid Bond) በኢስት ዌስት ኢትዮ ትራንስፖርት ኃ.የተወየግል.ማኅበር (EAST-WEST ETHIO TRANSPORT PLC)ስም ከመወዳደሪያ ሰነዶች ጋር በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ የጨረታ ቁጥሩን በመግለጽ እስጽ መስከረም 28 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በዋናዉ መ/ቤት ለጨረታ በተዘጋጀዉ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የተሸከርካሪዉን የመነሻ ዋጋ አስራ አምስት በመቶ (15%) ያላሲያዙ ተጫራቾች ከጨረታዉ ዉድቅ ይደረጋሉ። 
  4. ጨረታዉ መስከረም 28 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያዉ ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ቃሊቲ በሚገኘዉ የድርጅቱ ዋናዉ መ/ቤት የሰራተኞች ክበብ ይከፈታል። 
  5. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈስገ በስልክ ቁጥር 0114-39-24-35፤ 0114-39-36-60፤ 0114-39-20-38 ደዉስዉ መጠየቅ ይችላሉ።
  6. . ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ። 

ኢስት ዌስት ኢትዮ ትራንስፖረት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር

__________________

Posted:አዲስ ዘመን መስከረም 7፣2013

Deadline:መስከረም 28 ቀን 2013

__________________
© walia tender

Report Page