usd የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን
Walia Tenderየተለያየ ዓይነትና ደረጃ ያላቸው የዕጣን ምርቶች ሽያጭ የወጣ የጨረታማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኢግስኮ- ኢምዘደውአ/ ሸ01 ሐ/2013
በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የኢትዮጵያ ምርጥ ዘርና የደን ውጤቶችአቅርቦት ዘርፍ አዳማ፣ ቻግኒ፣ አሶሳ እና ሽሬ ቅ/ጽ/ቤቶች የሚገኙ የተለያየ ዓይነትናደረጃ ያላቸው ብዛት 2353 ኩንታል የዕጣን ምርቶች ባሉበት ሁኔታ በጨረታአወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በዘርፉ የተሰማራችሁና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉሁሉ በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፤ የተጨማሪ እሴትታክስ ምዝገባ የምስክርነት ወረቀት፤ የንግድ ምዝገባ የምስክርነት ወረቀት፤ በጨረታለመሳተፍ የሚሰጥ የምስክርነት ወረቀት (ክሊራንስ) ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከ11፡00 ሰዓት በፊት) በዋናው መ/ቤትየግብርና ምርት ማሳደጊያዎች አቅርቦት ዘርፍ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 4 የማይመለስ ብር 100.00 ( አንድ መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ከ20% ያላነሰCPO በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የኢትዮጵያ ምርጥ ዘርና የደንውጤቶች ኦቅርቦት ዘርፍ ስም ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል የጨረታው ዋጋ ለ60 ቀናትየፀና መሆን ይኖርበታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የሚጠይቀውን በሙሉ አሟልቶ ማቅረብይጠበቅበታል የተለያየ ዓይነት ደረጃ ያላቸው የዕጣን ምርቶች ተጫራቹ በሚሰጠውዋጋ ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ ያጨመራል፡፡
- ጨረታው ነሐሴ 15 ቀን 2012 ዓ. ም ከቀኑ በ8 ፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀንከቀኑ 8 ፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዘርፉመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ከቀረበው ዝርዝር ምርቶች ውስጥ በሙሉ ወይምበከፊል መጫረት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፤
- ዘርፉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝመብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር 011 663 21 93/ ፋክስ 011 663 08 92
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን
የኢትዮጵያ ምርጥ ዘርና ደን ውጤቶች አቅርቦት ዘርፍ
Posted:አዲስ ዘመን ነሀሴ 5 ቀን 2012
Deadline: August 21, 2020
© walia tender