usd ቤኪማር ኢንዱስትሪ ኃ

usd ቤኪማር ኢንዱስትሪ ኃ


Walia Tender

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ 

የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ 7ኛ ፍ/ብሄር ችሎት በመ/ቁ 169477በቤኪማር ኢንዱስትሪስ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ላይ የመከሰር ፍርድ መስጠቱን ተከትሎ የማህበሩ ንብረት ሲያጣራ ቆይቷል፡፡ ማህበሩ የተለያዩ ለልብስ ማምረቻነት የገዛቸውን ማሽነሪዎች እና የቢሮ መገልገያ እቃዎችን ያካተተ የዝግ ጨረታ ሽያጭ ይካሄዳል፡፡ በጨረታ የመሸጥ ፍላጎት ያለው በመሆኑ ማንኛውም ተጫራች የንብረቶችን ሙሉ ዝርዝር ከንብረት ጠባቂው ሰመቀበል እና በአካል በመመልከት በጨረታው መካፈል የሚችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡ የማህበሩ ንብረቶች Praise Business PLC በተባለ ድርጅት ግምት የተሰራላቸው ሲሆን በግምቱ መሰረትም የጨረታ መነሻ ዋጋው 6,341,144.00/ስድስት ሚሊዮን ሶስት መቶ አርባ አንድ ሺህ አንድ መቶ አርባ አራት ብር/ ነው፡፡ አጠቃላይ የማሽኖቹ ብዛት 21 ሲሆን የንብረቶቹ አይነትም፡

  1. Knitting machines with accessories 
  2. Support machines 
  3. Other items 

ማሳሰቢያ 

  1.  ተጫራቾች የመነሻ ዋጋውን 1/10(አንድ አስረኛ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረለት የክፍያ ማዘዣ(ሲፒኦ) በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡ - 
  2. ተጫራቶች ንብረቶቹን ቦሌ ክ/ከተማ ገርጅ በሚገኘው በደስታ የፋብሪካ ቅጥር ግቢ ከመስከረም 18 ቀን 2013 ዓ.ም እስከ መስከረም 20 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ከጠዋቱ 5፡00 እስከ 6፡00 ድረስ ብቻ መመልከት ይችላሉ፡፡
  3. ማንኛውም ተጫራች ንብረቶቹን ባሉበት ሁኔታ በጥቅል (በአጠቃላይ) መግዛት የሚችል መሆን አለበት፡፡ ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያ ላይ የጥቅል እና ዝርዝር ዋጋ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡ 
  4. ማሽኖቹ ከቀረጥ ነጻ የገቡ በመሆናቸው ገዥው የሚፈለገውን ቀረጥ የሚከፍል ይሆናል፡፡ 
  5. አሸናፊ ተጫራች እንደ አስፈላጊነቱ የስም ማዛወሪያ ይከፍላል፡፡ 
  6. ተጫራቶችን የንብረቶቹን ዝርዝር የሚያሳየውን ሰነድ ከመስከረም 18 ቀን 2013 ዓ.ም እስከ መስከረም 24 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ከንብረት ጠባቂው አሸናፊ ይርጋ ወይም ገርጅ ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ አጠገብ ከሚገኘው ባዋ ህንጻ 2ኛ ፎቅ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡ 
  7. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የጨረታ ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ከመስከረም 26 ቀን 2013 ዓ.ም እስከ መስከረም 29 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ገርጅ ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ አጠገብ በሚገኘው ባዋ ህንጻ 2ኛ ፎቅ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
  8. የጨረታው ሳጥን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ገርጅ ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ አጠገብ በሚገኘው ባዋ ህንጻ 2ኛ ፎቅ ስብሰባ አዳራሽ በ30/01/2013 ዓ.ም ከቀኑ 5፡00 ይከፈታል፡፡ 
  9. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ30 (ሰላሳ) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ያስያዙት ገንዘብ ለማህበሩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፡፡ 
  10. ማህበሩ አስፈላጊ ሆኖ ካገኘው ጨረታውን የመሰረዝ ሙሉ መብት ይኖረዋል፡፡ 
  11. ማህበሩ ንብረቶቹ በገዥ ስም እንዲዛወሩ ለሚመለከተው አካል ደብዳቤ ይጽፋል፡፡ 
  12. ተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0912365168/0921146680 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡ 

ቤኪማር ኢንዱስትሪ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር 

__________________

Posted:አዲስ ዘመን መስከረም 9፣2013

Deadline:መስከረም 29 ቀን 2013

__________________
© walia tender


Report Page