usd ማገርኮን ኃ/የተ/የግ/
Walia Tenderየጨረታ ማስታወቂያ
ያገለገሉ የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች እና ልዩ ልዩ የግንባታ ዕቃዎች እንዲሁም የቢሮ ዕቃዎችን ለመሸጥ የወጣ ጨረታ
ማገርኮን ኃ/የተ/የግ/ማህበር በጥሩ ይዞታ ላይ የሚገኙ ያገለገሉ ማሽነሪዎች ተሽከርካሪዎች እና ልዩ ልዩ የግንባታ ዕቃዎችን እንዲሁም የቢሮ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::
ስለሆነም፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ከ3ኛው ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 50.00( ሃምሳ ብር) መ/ ቤቱ ገንዘብ ቤት በመክፈል የጨረታውን ሰነድ ማግኘት ይችላል::
- . የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አቃቂ ቃሊቲ ሳሪቲ በሚገኘው የመ/ቤቱ ዋና መጋዘን ዘወትር በሥራ ሰዓት በአካል ቀርበው መመልከት ይችላሉ::
- ተጫራቾች ለመጫረት ከሚያቀርቡት ዋጋ 5% የጨረታ ዋስትና ማስከበሪበያ (Bid Bond) በባንክ ክፍያ ትዕዛዝ ቼክ (CPO) ወይም በካሽ በመ/ቤቱ ትክክለኛ ስም ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ እስከ ጨረታው መዝጊያ ነሐሴ 13 ቀን 2012 ዓ. ም. ከቀኑ 11 ሰዓት ድረስ የመስሪያ ቤቱ ገንዘብ ሴት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው::
- ጨረታውን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ነሐሴ 14 ቀን 2012 ዓ. ም. 4 ፡30 ሰዓት ይከፈታል::
- የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ለአሸናፊዎች ከሚከፍሉት ዋጋ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊዎች የጨረታው ውጤት እንደታወቀ በ3 የሥራ ቀን ውስጥ ያስያዙትን የጨረታ ዋስትና (CPO) ወይም በካሽ ለተጫራቹ ይመለስለታል::
- መስሪያ ቤቱ ጨረታውን የተሻለ መንገድ ካገኝ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ መሆኑን ያሳውቃል::
የመ/ ቤቱ አድራሻ
ቃሊቲ ከማሰልጠኛ አደባባይ ወደ ሃና ማርያም ሲሄዱ 3 ዐዐ ሜትር ርቀት ላይ በስተግራ በካዲስኮ ቀለም ፋብሪካ 400 ሜትር በቀጥታ አዲሱ አስፋልት መንገድ ወደ ውስጥ ገባ ብሎ ጨርቃ ጨርቅ ኢንስቲትዩት መሥሪያ ቤት ፊት ለፊት ሲሆን የስልክ ቁጥር
0114-39-16-06/391600 እና 0911 92 69 00 ፣ 0912 12 52 00 -
__________________
Posted:ሪፖርተር ነሀሴ 6 ቀን 2012
Deadline: August 19, 2020
__________________
© walia tender