usd ሐበሻ ሲሚንቶ
Walia Tenderያገለገሉ የስካፍ ሆልዲንግ እና
ክላፖች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ ሐበሻ ሲሚንቶ አ. ማ የጨረታ ቁጥር
HCSC-02/ Scafolding/2020
ኩባንያችን ለግንባታ ሥራ የተጠቀመባቸውን ስካፍሆልዲንግ እና ክላፖችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ማንኛውም በጨረታ ለመካፈል የሚፈልግ ተጫራች ስለ ጨረታው እና የዕቃውን ዝርዝር እና ተያያዥ መመሪያዎችን የያዘውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00( ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከድርጅታችን ዋናው መስሪያ ቤት ጎተራ ወሎ ሰፈር ወንጌላዊት ህንጻ ፊት ለፊት ከሚገኘው ካስማ ህንጻ 8 ተኛ ፎቅ ግዢና አቅርቦት መምሪያ ቀርቦ ሰነዱን በመውሰድ በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ቢድ ቦንድ ብር 100,000.00( አንድ መቶ ሺህ ብር ብቻ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ሰነድ በድርጅታችን ስም በማዘጋጀት ከጨረታ ሰነዱ ጋር መቅረብ አለበት::
ተጫራቾች ለጨረታ የቀረቡት ስካፍሆልዲንግ እና ክላፖቹን ያሉበትን ሁኔታ ሆለታ ፋብሪካው ቅጥር ግቢ ድረስ በመሄድ መመልከት የምትችሉና የምትገዙትን የአንድ ኪሎ ግራም ስካፍሆልዲን ከነክላምፑ የምትገዙበት ዋጋ ማንኛውንም ታክስ ሳያካትት/አካቶ መሆኑን በግልጽ በማስቀመጥ የምትጫረቱበትን ዋጋ ከጨረታ ማስከበሪያው ጋር በፖስታ በማሸግ ጎተራ አካባቢ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት እስከ ነሐሴ 22 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው ነሐሴ 22 ቀን 2012 ዓ. ም ከጠዋቱ 4 ፡00 ተዘግቶ በዕለቱ 4 ፡30 ከላይ በተገለጸው አድራሻ በዋናው መስሪያ ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ሐበሻ ሲሚንቶ አ. ማ
ስልክ ቁጥር 011-4163273
__________________
Posted: ሪፖርተር ነሀሴ 6 ቀን 2012
Deadline: August 28, 2020
__________________
© walia tender