Update

Update

🇲 🇴 🇸 🇮

ኮኬይንን በሆዱ ይዞ ወደ ታይላንድ ለማስገባት የሞከረው ኬንያዊ በቁጥጥር ሥር ዋለ


ኮኬይን የተባለውን አደንዛዥ እፅ በክኒን መልክ ሆዱ ውስጥ ይዞ ወደ ታይላንድ ሊገባ የሞከረው ኬንያዊ ባንኮክ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ በቁጥጥር ሥር ውሏል።


ግሌን ቺባሴሎው ኦኮው የተባለው ኬንያዊው በቁጥጥር ሥር የዋለው፣ በራጅ በተደረገበት ምርመራ 68 የኮኬይን ክኒኖችን ሆዱ ውስጥ ይዞ በመገኘቱ ነው።


የኮኬይን ክኒኖቹ 1 ነጥብ 2 ኪሎ ግራም እንደሚመዝኑ የታይላንድ የመድኃኒት ባለሥልጣን ገልጿል።


ኬንያዊው ሰኞ ዕለት ወደ ባንኮክ ያመራው ከኢትዮጵያ ተነስቶ መሆኑን ኤ.ኤፍ.ፒ ዘግቧል።


ከኬንያዊው ጋር በቁጥጥር ሥር የዋለ አንድ ናይጄሪያዊ የወንጀሉ ዋና አቀነባባሪ እንደሆነና ኬንያዊውንም በሥራው ላይ ያሰማራው እሱ መሆኑን የታይላንድ ብሔራዊ ጋዜጣ ዘግቧል።


ምንጭ፦ ቢቢሲ

@zenabisrat @zenabisrat

Report Page