Update

Update


#Tigray

ዛሬ ፋይናሻል ታይምስ "Fighting and food shortages fray hopes for Ethiopia’s ceasefire" በሚል በትግራይ ጉዳይ ሰፋ ያለ ፅሁፍ ይዞ ወጥቷል።

ፅሁፉ የኢትዮጵያ መከላከያ የትግራይ ከተሞችን ከለቀቀ በኃላ ህወሓትም የትግራይ ከተሞችን ከያዛቸው በኃላ ያለውን ሁኔታ የሚዳስስ ነው።

በዚህ ዘገባ ላይ ከዚህ ቀደም በዓለም አቀፍ ሚዲዎች ላይ ያልተሰማ አዲስ መረጃ ተካቶበታል ይኸውም "ህወሓት ሱዳን ውስጥ 30,000 ተዋጊ ኃይል አለኝ" ማለቱ ነው።

ፋይናሻል ታይምስ የአንድ ስማቸው ያልተገለፀ የህወሓት ከፍተኛ ኃላፊ ነገሩኝ ብሎ እንዳስነበበው፥ ህወሓት ተቀዳሚ ስራው በምዕረብ ትግራይ በኩል ያሉ ተቀናቃኞችን ማስወጣት/ምዕራባዊ የትግራይ ቦታዎች መቆጣጠር እንደሆነ ገልጿል።

ቡድኑ ለዚህ ምንም አይነት የወታደራዊ አቅም ችግር እንደሌለበት ለፋይናሻል ታይምስ የገለፀ ሲሆን አሁን ላይ ዋነኛ ዓላማው ትግራይን ከሱዳን ጋር የማያገኛኘውን ኮሪደር ለማስከፈት መሞከርና ማስከፈት ነው ብሏል።

ህወሃት ሱዳን ውስጥ ውጊያውን ለመቀላቀል የሚጠባበቁ 30 ሺ ታጣቂዎች አሉኝ ማለቱን ፋይናሻል ታይምስ አስነብቧል።

አንድ ስማቸውን ያልተገለፀ የሱዳን ባለስልጣን በጉዳዩ ዙሪያ በሰጡት አስተያየት ሀገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ በሚደረገው ጦርነት ለመሳተፍ ፍላጎት እንደሌላት ገልፀዋል።

በዚህ ዘገባ ላይ ስለታጣቂዎቹ ዝርዝር መረጃ አልቀረበም ፣ እንዴትስ ይህን ያህል ቁጥር ያለው ታጣቂ ሱዳን ውስጥ ሊኖረው እንዳለው አላመለከተም።

ከዚህ ቀደም የፌዴራል መንግስት በ" ማይካድራ ጭፍጨፋ" የተሳተፉ በርካታ ታጣቂዎች ከተፈናቀሉ ሰዎች ጋር ተመሳስለው ወደሱዳን ገብተው እንደነበር ክስ ሲያሰማ ነበር።

በወቅቱ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች እና አለም አቀፉ ማህበረሰብ ለጉዳዩ ትኩረት ሳይሰጡት ነው ያለፉት ሲልም ይወቅሳል።

UN በሱዳን ያሉ ተፈናቃዮች የሚበዙት ሴቶች እና ህፃናት ናቸው ቢልም የኢትዮጵያ መንግስት የማይካድራውን ጭፍጨፋ የፈፀሙ ታጣቂዎች ሱዳን እንደገቡ በተደጋጋሚ ገልጿል።

አሁን ህወሓት ሱዳን ውስጥ አለኝ ያላቸው ታጣቂዎች መንግስት ከሚያሰማው ክስ ጋር በቀጥታ ይገናኝ አይገናኝ የታወቀ ነገር የለም። ስለታጣቂዎቹች ዝርዝር መረጃም አይታወቅም።

@tikvhaethiopia

Report Page