test post

test post

ㅤ ㅤ ㅤ ㅤ ㅤ ㅤ ㅤ

መግለጫ! በአገሪቱ እየመጡ ያሉ ለውጦችን ለማደናቀፍ እየተሰሩ ያሉ ሴራዎችን የሚመረምሩ ኮሚቴዎች ተቋቋሙ።

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው ሰኔ16፣ 2010 በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ መሪነት በአገሪቱ የተጀመረውን ለውጥ እውቅና ለመስጠት፣አገራዊ አንድነትን ለመገንባትና የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎችን ለመደገፍ በወጣው ህዝብ ላይ ቦምብ ተወርውሯል፣ ሂደቱ እንዲስተጓጎልም ተደርጓል፡፡

ሰላማዊ ሰልፉን ለማደናቀፍ ቦምብ ከመወርወር ጀምሮ ሂደቱ እንዲስተጓጎል በወቅቱ መብራትና የቴሌኮም ኔትወርክ ማጥፋት፣ የኢኮኖሚ አሻጥር በተደራጀ አኳኋን በመስራት የኑሮ ውድነትን እንዲባባስ እና የተለያዩ ህዝባዊ አገልግሎት እንዲሰጡ የተቋቋሙ ተቋማት አስፈላጊውን አገልግሎት እንዳይሰጡ እየተደረገ መሆኑን ለማረጋገጥ መቻሉንም ጽ/ቤቱ አመልክቷል፡፡

እነዚህን ህገወጥ ተግባራት አጣርቶ ለህግ የሚያቀርብ ከተለያዩ አካላት የተለያዩ ኮሚቴዎች ተቋቁመው ስራቸውን እያከናወኑ መሆኑን ፅ/ቤቱ ገልጿል፡፡

ለተልዕኮው ስኬታማነትም መላው ሰላም ወዳድ ህዝብ ከኮሚቴው ጎን በመቆም ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርግና አጥፊዎችን ለፍርድ ለማቅረብ እንዲተባበር ተጠይቋል፡፡

ውጤቱን ለህዝብ ይፋ እንደሚደረግም ፅ/ቤቱ አመልክቷል፡፡

@FriendsPlus

Report Page