TEST

TEST

@ethiotribune

የሃገሪቱ ይፋዊ መግለጫ እንደሚያሳየው ሱዳን በከፍተኛ ጎርፍ ተመትታለች።

የሃገሪቱ ይፋዊ መግለጫ እንደሚያሳየው ሱዳን በከፍተኛ ጎርፍ ተመትታለች።

በአደጋው ምክንያትም 62 ሰዎች ሕይወታቸውን እንዳጡ መግለጫው ይፋ አድርጓል። በሕዝባዊ ተቃውሞ ስትናጥ የከረመችው ሱዳን ከሃምሌ ወር መግቢያ ጀምሮ ደግሞ ከፍተኛ ዝናብ የሃገሪቱ ሌላኛው ፈተና ሆኖ ቆይቷል።

ከባድ ዝናቡ ባስከተለው ጎርፍ 15 የሱዳን ግዛቶች የከፋ ጉዳት ደርሶባቸዋል። በደቡባዊ የሃገሪቱ ክፍል የምትገኘው የነጭ አባይ ግዛት ደግሞ ከፍተኛውን ጉዳት በማስተናገድ ቀዳሚ ነች።

በእነዚህ 15 ግዛቶች 200 ሺህ የሚጠጋ ህዝብ በተፈጠረው የጎርፍ መጥለቅለቅ ጉዳት ደርሶበታል ነው የተባለው።

በጉዳዩ ላይ ሃሳቡን የሰነዘረው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 37 ሺህ ቤቶች በተፈጠረው የጎርፍ መጥለቅለቅ ከመውደማቸው በተጨማሪ በቀጣዮቹ ጊዜያትም የጎርፍ አደጋ ሊከሰት እንደሚችል ስጋቱን ገልጿል።

የሱዳን ዝናባማው ወቅት እስከ ጥቅምት ወር የሚቀጥል መሆኑ ደግሞ ሌላኛው ስጋት ነው።

ካለፈው ታህሳስ ወር ጀምሮ በሕዝባዊ ተቃውሞ ስትናጥ የቆየችው ሱዳን አንጻራዊ ሰላም ያመጣ ሽግግር ብታደርግም የወደቀውን ምጣኔ ኃብቷን ለመታደግ ከ8 ቢሊዮን ዶላር በላይ ድጋፍ ያሰፈልጋታል ተብሏል።

እንደዚህ አይነት የተፈጥሮ አደጋዎች መከሰታቸው ደግሞ ለሃገሪቱ ተጨማሪ ችግር በመውለድ ሱዳን ከችግር የምትወጣበትን ጊዜ ያራዝመዋል የሚሉ አስተያየቶች በብዛት እንዲስተናገዱ አድርጓል።

Report Page