ስንክሳር_ዘሰኔ

ስንክሳር_ዘሰኔ

ዘ ልዑልⓂ ዲያቆን ዘልዑል ምናሉ

ስንክሳር ዘሰኔ ፲፱

✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ          አሜን


✍"ችግር ለራሳችን እንድንጸልይ ያነቃቃናል፤ ፍቅርደግሞ ለሌሎች ሰዎች እንድንጸልይ ያስገድደናል"         

📚ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ        

 ቀናችንን በጸሎት እንጀምር 


   ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥    

ሰማዕቱ ሐዲስ ጊዮርጊስ   

✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥


❖ ይኸውም ቅዱስ የአባቱ ስም መዛሕዝም ነው፤ ትርጓሜውም ድንገተኛ ማለት ነው። እርሱም እስላም ነበር፣ ከክርስቲያን ወገን የኾነች ሚስት አግብቶ ይህን ቅዱስ እና ሌሎችንም ኹለት ልጆች፣ በአጠቃላይ ሦስት ልጆች ወለደ።

❖ ይህንም ቅዱስ እናቱ ወደ ቤተ ክርስቲያን ስትወስደው ከቅዱስ ቊርባን ሊቀበል ይወድ ነበር፤ እርሷ ግን ከተጠመቀ በቀር መቀበል እንደማይችል ነገረችው፤ ከተረፈ መሥዋዕቱም በሰጠችው ጊዜ ከማር ይልቅ ጣፈጠው።

❖ በዚህም የተነሳ ቊርባን ብቆርብማ ምንኛ ይኾንልኝ አለ፤ ኋላም ትልቅ ሲኾን ክርስቲያን ሚስት አገባና ክራቲያን መኾን እንደሚሻ ነገራት፤ እርሷም ወደ ሌላ አገር ኺዶ እንዲጠመቅ መከረችው፤ ተነስቶም ወደ ሌላ አገር ኼደና ተጠመቀና ስሙን ቀይሮ ጊዮርጊስ አለው።

❖ ከዚያም በኋላ ዜናው ሲሰማበት ተነስቶ ወደሌላ አገር ኼደ፤ በኋላም ጥቂት ጊዜ በኋላ ወደ አገሩ ሲመለስ ክርስቲያን የመኾኑን ነገር እስላሞች በሰሙ ጊዜ ይዘው እጅግ አሠቃዩት፣ ይዘውም ለመኰንኑ ሰጡት፤ መኰንኑም ሲያሠቃየው የመኰንኑ ሚስት ክርስቲያን ነበረችና አታሠቃየው አለችው፤ እርሱም ወደ እሥር ቤት ጣለው።

❖ እስላሞችም የእሥር ቤቱን በር ገልጥለው አካሉ እስኪቆራረጥ ጽኑዕ ግርፋትን ገረፉትና በሞትና በሕይወት መካከል አድርገውት ኼዱ።

❖ ዳግመኛም እኒያ ተንባላት ተሰበሰቡና ሃይማኖቱን እንዲተው ጠየቁት፣ እርሱ ግን በጽኑዕ በታመነ ጊዜ እጅግ ተቆጡና በመርከብ ምሶሶ ላይ አሥረው ሰቅለው እጅግ አሠቃዩት።

❖ አውርደውም በመኰንኑ ትእዛዝ እሥር ቤት አኖሩት፤ ኋላም መልአከ እግዚአብሔር ተገልጦ ሰማዕት እንደሚኾን ነግሮት አጽናንቶት ተሠወረ።

❖ ከዚያም ከእሥር ቤት አወጡትና ወስደው በከበረ በቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ራሱን በሰይፍ ቆረጡ፤ የሰማዕትነትንም አክሊል ተቀበለ። በረከቱም ረድኤቱም ይደርብን፤ በጸሎቱ ይማረን አርሶፎኒስ ጴጥሮስ አስኪርዮን አርጌንዮስና ቢልፍዮስ

❖ ዳግመኛም በውሽባ ቤት ማንደጃ ፊቱን አጠወለጉት እንዲሁም ደግሞ በሚያስጨንቅ ኹኔታ በሠረገላ ውስጥ ቁልቁል አሥረው ሰቀሉት፣ ነፍሱንም በክብር ባለቤት በጌታችን እጅ ሰጠ።

❖ ቀጥለውም ጴጥሮስን አቀረቡት፣ እርሱም ክፉ አማልክትና ለአጋንንት አልሰዋም ባለ ጊዜ እጅግ አሠቃዩት፤ በእንጨትም ዘቅዝቀው ሰቀሉት።

❖ ዳግመኛም ምድርን ቆፍረው ከወገቡ በታች ቀበሩትና በቅሎዎችን በላዩ ላይ ነዱበት፣ ከዚያም አንስተው ወስደው በግንድ አሥረው ጣሉት።

❖ ከዚያም አርጌንዮስን አቀረቡት፤ እርሱንም በጽኑዕ አሠቃዩት፤ ያለ መብልና የለ መጠጥም አሥረው ዘቅዝቀው ሰቀሉት።

❖ ዳግመኛም አስኪርዮንን አቀረቡና አልሠዋም ባላቸው ጊዜ በጽኑኢ ሥቃይ ያሰቃዩት ጀመሩ፣ በትዕግሥቱም ቢያሸንፋቸው በመኰንኑ ትዕዛዝ በረሀብና በጽምዕ እንዲሞት በግንድ ውስት አሥረው በባዶ ቤት አኖሩት።

❖ ደግሞም ዲያቆን ቢልፍዮስን አቀረቡና እጅግ አሠቃዩት፤ በከተማው አደባባይም ጎትቱት፤ እንጨትም ተክለው ቊልቊል ሰቀሉት፤ በአንገቱም ከባድ ደንጊያ አደረጉበት፤ ኋላም ልክ እንደወንድሞቹ በረሀብ እንዲሞት በግንድ አሥረው በባዶ ቤት ጣሉት፤ በየእለቱም ወንድሞች ምእመናን ከውጭ ይጎበኙት ነበር።

📌 ሰኔ 19 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

1. ቅዱስ ጊዮርጊስ ሐዲስ ሰማዕት

3. ቅዱሳን "5ቱ" ጭፍሮች (በብዙ ስቃይ ሰማዕት የሆኑ ባልንጀሮች)

4. አባቶቻችን የደብረ ቁዋዐት ጻድቃን

📌 ወርሐዊ በዓላት

1. ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት

2. ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት

3. አቡነ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ

4. አቡነ ስነ ኢየሱስ

5. አቡነ ዮሴፍ ብርሃነ ዓለም

✍ "ዘአቅረብኩ ማኅሌተ አዘኪርየ አእላፈ እምእለ ተጸምዱከ ዘልፈ ለእለ አነብብ ተወከፍ ዘንዴትየ መጽሐፈ እንተ ረሰይከ እግዚኦ ጸሪቀ መበለት ውኩፈ እም እለ አብኡ ብዑላን ዘተርፈ ነቢያት ቅዱሳን ወሐዋርያት ሰባክያን ሰማዕታት ወጻድቃን ወመላእክት ትጉሃን ዓዲ ወመነኮሳት ሔራን ባርኩ ባርኮ ጉባኤ ዛቲ መካን እስከ አረጋዊ ልሒቅ እምንዑስ ሕጻን ለዘጸሐፎ በክርታስ ወለዘ አጽሐፎ እንዘ ይደርስ ለዘአንበቦ ወለዘተርጐሞ በልሳን ሐዲስ ወለዘሰምዐ ቃሎ በዕዝነ መንፈስ በጸሎተ እሙ ማርያም አራቂተ ኩሉ እምባዕ ስኅቡረ ይምሐረነ ኢየሱስ ክርስቶስ ወይፈኑ ለነ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ እምይእዜ ወእስከ ለዓለም"

✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝

✍"ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን" 📚ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ             

ወስብሐት ለእግዚአብሔር                           

   ይቆየን


   ቻናላችንን ይቀላቀሉን ለሌሎችም ሼር ያድርጉ

https://t.me/Finote_Abew1 https://t.me/Finote_Abew1

🕹 ትምህርቱ እንዴት ነው......የእናተ አስተያየትና ጥያቄ ከዚህ የበለጠ ለመትጋት ይረዳልና መልእክት ይተውሉኝ፤ የተሳተውን፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት ቸሩ መድኃኔዓለም ማስተዋሉን ያድለን፤ በፀሎታቹ አስቡኝ አትርሱኝ የተለያየ ጽሁፍ ያላቹ፣ መተረክ እንችላለን የምትሉ ቻናሉንና ግሩፑን በተለያየ አገልግሎት ማገዝ የምትፈልጉ በውስጥ መስመር አናግሩኝ።

 📩Coment- Telegram ላይ @Kibreleul @Mesikel_bot @Channal_Admin

አዘጋጅ ዲያቆን ዘልዑል ምናሉ

Report Page