#SRS

#SRS


«የሲዳማን ክልልነት አውጇል፤ የሚቀረው የመንግሥት ድርሻ ነው»-ኤጄቶ

የሲዳማ ወጣቶች ክልላዊ መንግሥት ለመመሥረት የሚያስፈልጋቸውን ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን አስታወቁ። የሲዳማ ወጣቶች፣ ያገር ሽማግሌዎች እና በርካታ ታዳሚዎች የሲዳማ ክልል በሚመሰረትበት ሁኔታ ላይ ውይይት አድርገዋል። የኤጄቶ ተወካይ የሆነው ወጣት ጌታሁን ደጉዬ «ኤጄቶ የሲዳማን ክልልነት አውጇል፤ ቀሪው ሥራ የመንግሥት ነው» ሲል ተናግሯል።

ዛሬ እሁድ ማለዳ በሀዋሳ ሀይቅ ዳርቻ በሚገኘውና ጉዱማሌ ተብሎ በሚጠራው ባህላዊ የመሰባሰቢያ ስፍራ ላይ የተገኙት የሲዳማ የአገር ሽማግሌዎች ውይይቱን የጀመሩት በባህላዊ ጸሎትና ምርቃት ነው።

የአገር ሽማግሌዎቹ እና ወጣቶቹ በባህላዊ ስፍራው በሚገኙት የዋርካ ዛፍ ጥላዎች ስር የተሰባሰቡት በብሄሩ አጠራር አፊኒ በሚባለው የምክክር ልማድ መሰረት ነው።

ሁለቱ ወገኖች በምክክራቸው ውጥረት ባንዣበበት የክልል መዋቅር ጥያቄ ዙሪያ ሀሳብ ተለዋውጠዋል ፣ በመጨረሻም የጋራ ያሉትንም አቋም አንጸባርቀዋል።

ለሲዳማ ህዝብ የራስ መስተዳድር እንደሚታገል የሚገልጸውና ኤጄቶ የተባለው የወጣቶች ቡድን ተወካይ ጌታሁን ደጉዬ ኤጄቶ «ድርሻውን ጨርሷል፤ ክልልነቱን አውጇል። የሚቀረው የመንግሥት ድርሻ ነው» ሲል ተናግሯል።

የሲዳማ ዞን ሕዝበ ውሳኔ እንዲካሔድ ከጠየቀ በመጪው ሐምሌ 11 ቀን 2011 ዓ.ም. አንድ አመት ይሞላዋል። ክልሉን የሚያስተዳድረው ደኢሕዴን የሲዳማን ጨምሮ ክልል ለመሆን በቀረቡ ጥያቄዎች ላይ ውይይት እያደረገ ይገኛል።

በመክክሩ ላይ የተሳተፉ የአገረ ሽማግሌቸ ተወካይ ኤጄቶ የተባለው የወጣቶች ቡድን ያቀረበውን ክልል የመሆን ወሳኔ መቀበላቸውን ገልጸዋል።

በምክክሩ ማጠቃለያ ላይ ተጨማሪም የፌደራሉንና በቀጣይ የሲዳማ የሆናል ተበሎ የታሰበውን ሰንደቅ ዓላማዎች ግራና ቀኝ የመሰቀል ሰነ ስረዓት ተከናወኗል ።  

በዛሬው ባህላዊ ምክክር ላይ በቡዙ ሺህዎች የሚቆጠሩ ወጣቶችና የሲዳማ የአገር ሽማግሌዎች የተገኙ ቢሆንም ከዞንም ሆነ ከክልል የተወከሉ የመስተዳድር ሃላፊዎች ግን በስፈራው አልነበሩም።

Via #DW

@tsegabwolde @tikvahethiopia

Report Page