Sport
ETHIO ሪፖርተርየአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ሁለተኛ ዙር የምድብ ጨዋታዎች ትናንት ምሽት በተለያዩ ከተሞች ተካሄደዋል፡፡
በምድብ አንድ ከሜዳው ውጭ ከሎኮሞቲቭ ሞስኮ የተጫወተው ባየር ሙኒክ 2 ለ 1 ሲያሸንፍ አትሌቲኮ ማድሪድ ሳልዝበርግን 3 ለ 2 አሸንፏል፡፡
በምድብ ሁለት የተደረጉ ጨዋታዎች ደግሞ በአቻ ውጤት ተጠናቀዋል፡፡
ሻካታር ከኢንተር ሚላን ያለምንም ጎል እንዲሁም ቦሩሲያ ሞንቼግላድባህ ከሪያል ማድሪድ 2 አቻ ጨዋታቸውን አጠናቀዋል፡፡
በምድብ ሶስት ፖርቶ ኦሊምፒያኮስን 2 ለ 0 እንዲሁም ማንቼስተር ሲቲ ከሜዳው ውጭ ማርሴይን 3 ለ 0 ማሸነፍ ችለዋል፡፡
በምድብ አራት ደግሞ አታላንታ ከአያክስ ያደረጉት ጨዋታ ሁለት አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል፡፡
በሜዳው ሚዲቲላንድን ያስተናገደው ሊቨርፑል ደግሞ 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡
ከምድብ አምስት እስከ ስምንት በሚገኙ ቡድኖች መካከል የሚደረጉ ጨዋታዎች ደግሞ ዛሬ ምሽት ይደረጋሉ፡፡
ዛሬ የሚደረጉ የአውሮፓ ሻምፕዮንስ ሊግ መርሃ ግብሮች፦
⏰ 2:55
ባሳክሼር Vs ፒኤስ ጂ
ኬራስኖዳር Vs ቼልሲ
⏰ 5:00
ጁቬንቱስ Vs ባርሴሎና
ማን ዩናይትድ Vs RB ሌፕዚሽ
ክለብ ብሩጅ Vs ላዚዮ
ዶርትሙንድ Vs ዜኒት
ሴቪያ Vs ሬኔስ
ፈረንስቫሮስ Vs ዳይናሞ ኬቭ
Via: Elias