sl tx ot በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አስ
Walia Tenderየግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አስተዳደር ጽ/ቤት የ2013 ዓ.ም ለ1ኛ ዙር
አላቂ እና ቋሚ የቢሮ እቃዎች (stationary)
የጽዳት እቃዎች ፤
የደንብ ልብስ ግዥ ፤የደንብ ልብስ ስፌት ፤
ልዩ ልዩ መሳሪያዎችንና እቃዎችን
በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ አቅራቢ ድርጅቶች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ተጫራቾች የተዘመኑን የመንግስት ግብር የ2012 ዓ.ም የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው መሆን አለባቸው::
- የቫት ተመዝጋቢና ህጋዊ የማቅረቢያ ሰርተፍኬት ያላቸው መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነድ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ክፍል 6 ውስጥ የተገለጹትን እቃዎች ዝርዝር ዋጋቸውን ስታሽገ ኤንቨሎፕ ቂ/ክ/ከተማ ወረዳ 4 ፋይናንስ ጽ/ቤት ለዚህ የተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው::
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 6000.00 (ስድስት ሺ) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት እቃ ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ናሙና የማስገባት ግዴታ አለባቸው::
- አሸናፊ ድርጅቶች በናሙናው መሰረት ደረጃውን የጠበቀ እቃ የማስገባት ግዴታ አለባቸው፡፡
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ በዚያኑ ቀን 3፡30 በፋ/ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡ 11ኛው ቀን በአል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ጨረታው ይከፈታል፡፡
- መቅረብ ያለባቸው መረጃዎች ኦሪጅናልና ኮፒ ሲሆን ሁለቱም ለየብቻቸው መታሸግ አለባቸው :: ነገር ግን ጨረታው ሲከፈት የሚከፈተው ኮፒው በመሆኑ ሲፒኦ (CPO) እና ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች በሙሉ ኮፒው ውስጥ መደረግ አለባቸው፡፡ በሁለቱም ኤንቨሎፕ ላይ የድርጅቱ ማህተም መደረግ አለበት፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉሰትን እቃ ዋጋ ድምር 10% የውል ማስከበርያ ከውል በፊት ማስያዝ አለባቸው :: የእያንዳንዱ እቃ ዋጋ ቫትን ያካተተ (ቫት ተጨምሮበት) መቅረብ አለበት፡፡ ይህንን ያላደረጉ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ ይሆናሉ፡፡
- ተጫራቾች ለሚኖራቸው ጥያቄዎች ወይንም መረጃ ማግኘት ለሚፈልጉ ስልክ ቀጥር 0118883069 መጠቀም ይችላሉ፡፡
አድራሻችን ከዲናፖል ሆተል ጀርባ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 አስተዳደር ጽ/ቤት
ማሳሰቢያ፡- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በቂርቆስ ክፍስ ከተማ የወረዳ 4 አስተዳደር ጽ/ቤት
__________________
Posted:አዲስ ዘመን መስከረም 9፣2013
Deadline:በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00
__________________
© walia tender