sl tx ትምህርት ሚኒስቴር

sl tx ትምህርት ሚኒስቴር

Walia Tender

የጨረታ ማስታወቂያ 

ትምህርት ሚኒስቴር ከዚህ በታች የተገለፁትን የፅዳት እቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈለጋል፡፡


  1.  ተጫራቾች የታሸገ የጨረታ ሰነድ ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡ 
  2. ጨረታው ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ሲሆን ሥርዓቱም በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር አዋጅና መመሪያ መሠረት ነው፡፡ 
  3. ፍላጐት ያላቸው ተጫራቾች በተራ ቁጥር 7 የተገለጹትን ሰነዶች በመያዝ በአማርኛ የተዘጋጀ የጨረታ ሰነዶችን ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ ብር 50 /ሃምሣ ብር/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000003784828 ገቢ በማድረግ ፋይናንስ አስተዳደር ቢሮ አሮጌው ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ ገቢ ያደረጋችሁበትን በማሳየት ደረሰኝ በመያዝ ከግዥ አገልግሎትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  4. ጨረታው የሚከፈተው የት/ሚኒስቴር አራት ኪሎ ዋና መስሪያ ቤት ግዥ አገልግሎትና አስተዳደር ዳይሬከቶሬት ቢሮ ቁጥር አሮጌው ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ ነው። 
  5. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከላይ በሠንጠረዥ የተገለፀው የገንዘብ መጠን ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  6. . ተጫራቾች የመወዳዳሪያ ሃሳብ የሚያቀርቡት ስተሸጠላቸው ጨረታ ሰነድ ምእራፍ 1 ክፍል 4 የተመለከቱትን ሠነዶች ቅፆች በመሙላት ይሆናል፡፡ ዝርዝር ፍላጐት መግለጫውን ከጨረታ ሠነዱ ጋር ተያይዞ ቀርቧል፡፡ 
  7. ተጫራቾች የሚከተሉትን ማስረጃዎች አሟልተው ማቅረብ አለባቸው:: ይህን ያላሟሉ ተጫራቾች ከውድድሩ ውጭ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ወይም በዘርፉ - የግብር ግዴታ ለመወጣት ከሀገር ውስጥ ገቢ ወይም ከሚመለከታቸው አካላት የተሰጠ የጽሑፍ ማስረጃ - የተፈታከስቫት/ ሠርተፍኬት የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ዌብ ሳይት ላይ የተመዘገበ 
  8. የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈፀም ቃል የሚገቡበት ቅጽ ተሞልቶ የተጫራቹ ድርጅት ፊርማና ማህተም የተደረገበት 
  9. መሥሪያ ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው። 

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-TeL:0118722896 መጠየቅ ይችላሉ፡፡ 

ትምህርት ሚኒስቴር 

አዲስ አበባ

__________________

Posted:አዲስ ዘመን መስከረም 7፣2013

Deadline: የተለያየ

__________________
© walia tender

Report Page