sl fr tx vi የቆሬ ወረዳ ገ

 sl fr tx vi የቆሬ ወረዳ ገ

Walia Tender

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ 

በምዕራብ አርሲ ዞን  የቆሬ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት በወረዳው ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች 1ኛ ዙር በ2013 የበጀት ዓመት ቀጥሎ የተዘረዘሩት ዕቃዎች ማለትም፣ 

ኤሌክትሮኒክስ
ፈርኒቸር
የፅህፈት መሳሪያዎች
የፅዳት እቃ
የደንብ ልብስ
የተለያዩ የሞተር ሳይክልና የመኪና ጎማዎች 

በግልፅ ጨረታ ህጋዊና አቅም ያላቸው ድርጅቶችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። አጫራቾች ከዚህ በታች የተገለፀውን መሣሪያ/መስፈርት/ በመከተል ይህን ጨረታ እንዲካፈሉ ተጋብዘዋል። 

  1.  ተጫራቶች በጨረታው ለመካፈል በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን (2012/2013) ግብር የከፈሉ እንዲሁም የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው ቫት ከፋይ የሆነ.(TIN Number) ማቅረብ የሚችሉ።
  2. ማንኛውም ተጫራች ወደ ጨረታው ሂደት ከገባ በኋላ በሰነድ ላይ የተገለፁትን ማንኛውም ሁኔታዎች ማሻሻል መቀየር እንዲሁም ሀሳቤን ቀይሪአለሁ ማለት አይችልም፡፡ 
  3. ማንኛውም ዕጩ ተወዳዳሪ የጨረታውን ሂደት ለማስተጓጓል ቢሞከር ከጨረታው ውጭ እንዲሆን ተደርጎ ወደፊት በሚደረገው የመንግስት ግዥ ላይ እንዳይሳተፍ የሚደረግ እና ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ የሚሆን ይሆናል። 
  4. ማንኛውም ተጫራች በመንግስት ግዥ ለመሳተፍ እንዲችል የሚገለፅ ከህጋዊ አካል የተሰጠ እቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለበት። 
  5. ተጫራቾች በሚሰሩበት የንግድ እና በንግድ ፍቃዳቸው ዘርፍ ብቻ ነው መወዳደር የሚችሉት 
  6. ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ የግዥ መደብ ብቻ 5,000 (አምስት ሺ ብር) በባንክ በተመሰከረለት CPO ማቅረብ አለበት። 
  7. ተወዳዳሪ ድርጅቶች የዕቃ ጥራት ደረጃቸው አስቸጋሪ የሆኑ የእቃ አይነቶች መስሪያ ቤታችን ቀድሞ ስላዘጋጀ ለምሳሌ፡- የኮምፒዩተር ወረቀት፣ እስክብሪቶዎች፣ ኬንት፣ ሶፍት፣ ኡሁ፣ ኮምፒዩተር ቀለም ኦርጅናል ተወዳዳሪ ድርጅቶች ይህንን ናሙና መስረት በማድረግ ብቻ የምቀበል መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን። 
  8. እሸናፊ ድርጅት እቃውን ጭነው እስከ መ/ቤታችን ግምጃ ቤት ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለበት።
  9. ተጫራቶች ዕቃው የተሰራበትን የተመረተበትን ሀገርና የጥራት ደረጃ የመስራት አቅሙን እንዲሁም ሞዴሉንና የተመረተበት ዓ.ም መግለፅ አለባቸው። 
  10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኮፒና ኦርጅናል በተለያዩ ፖስታ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ
  11. . ተጫራቾች የጨረታ ዋጋውን መሙላት ያለባቸው በተሸጠላቸው ሰነድ ላይ ብቻ መሆን አለበት። እንዲሁም እያንዳንዱ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት። ስራሳቸው ሰነድ ላይ የሚሞላ ለስራችን አመቺ ስለማይሆን ተቀባይነት የለውም። 
  12. ፅ/ቤታችን የሚጫረታቸው እቃዎች እስከ 20% በመጨመር ወይም በመቀነስ ማዘዝ ይችላል። 
  13. ተጫራቶች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፣ ሙሉ አድራሻቸው፣ ስልክ ቁጥራቸውን፣ በትከከል ፅፈው ማስፈረምና ማህተም ማድረግ አለባቸው። 
  14. ተወዳዳሪዎች የሚሰጡ የጨረታ ዋጋው ጨረታው ከተከፈተ ቀን ጀምሮ ለ60 ቀናት ወይምለሁለት ወር ፀንቶ የሚቆይ መሆን አለበት።
  15. . መ/ቤቱ ጨረታውን ገምግሞ ለማሳለፍ ወይም ውድቅ ለማድረግ የሚጠቀምበት ዘዴ እንደ እቃው አይነት ወይም የሚፈለገው አገልግሎት መሰረት በማድረግ ጥራትን ወይም ዋጋን ከግንዛቤ በማስገባት ተወዳዳሪዎችን አሸናፊ ወይም ውድቅ የሚያደርግ ሲሆን ሁለት እኩል ዋጋ ቢያቀርቡ በብዛት ላሸነፈው የሚሰጥ ይሆናል። 
  16. የሰነዱ ሽያጭ የሚቆይበት ቀን 18/01/2o13 እስከ 6/02/2013 ዓ.ም ሲሆን በ11፡30 ሰዓት ላይ ሳጥኑ ተገዝቶ ጨረታውን የሚከፈተው 7/02/2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቹ ወይም ህጋዊ ወኪሉ በተገኘበት በምዕራብ አርሲ ዞን ቆሬ ወረዳ በገንዘብ ኢኮኖሚ ትብብር ልማት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 01 በይፋ ይከፈታል። 
  17. የጨረታ ሰነዱን ዝርዝር በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ከምዕራብ አርሲ ዞን ቆሬ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ሰነድ ሽያጭ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በም/አ/ዞ/ወረዳ ገ/ኢ/ት/ል/ጽ/ቤት ስባንክ መደበኛ ሂሳብ ቁጥር 1000080903468 የኢትዮጵያ ንግድ ገቢ በማድረግ ስሊፕ በማያያዝ ቢሮ ቁጥር 01 ሰነዱን በመግዛት የሚችል ሲሆን ተወዳዳሪ ድርጅቶች ሰነድ ከገዙበት ቀን ጀምሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በስራ ሰዓት ሽያጭ እስከሚያበቃበት ቀን ድረስ ማስገባት ይችላል።
  18. . የጨረታ ውል ከጨረታ ሰነድ ጋር ስለሚሸጥ በውሉ መሠረት ጨረታውን ያሸነፈው ነጋዴ ለውሉ ተገዥ መሆን አለበት። 
  19. ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። 
  20. አሸናፊ ድርጅቶች ካሸነፉት ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ 10% ውል ማስከበሪያ በባንከ ም/አ/ዞ ቆሬ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ል/ጽ/ቤት መደበኛ ሂሳብ ቁጥር 1000080903468 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገቢ ማድረግ አለበት። 
  • ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 046 246 00 27/28/ ሞባይል 0913-29-27-91/0922-12-72-58/0924-30-01-23 

በምዕራብ አርሲ ዞን የቆሬ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት

__________________

Posted:አዲስ ዘመን መስከረም 10፣2013

Deadline: 6/02/2013 

__________________
© walia tender


Report Page