sl fr tx የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ፋ
Walia Tenderየጨረታ ማስታወቂያ
የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለሴ/መ/ቤቶች አገ/ት የሚውል
ኤሌክትሮኒክስ ፣
ፈርኒቸር ዕቃዎች ፣
ደንብ ልብስ፣
የጽ/መሳሪያ እና
የጽዳት ዕቃዎች ግዥ
በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል::
በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ይችላል::
- ተጫራቾች በተሰማሩበት የሥራ መስክ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የሥራ ፍቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው
- ተጫራቾች የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል
- ተጫራቾች የዕቃዎቹን ሙሉ ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ በግዥ ኬዝ ቲም የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 08 በመቅረብ የማይመለስ ለእያንዳንዱ ሰነድ ብር 100/አንድ መቶ ብር በመግዛት መወዳደር ይችላል::
- ተጫራቾች የጨረታ ዋጋቸውን ሞልተው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ሁለት ኮፒ እና አንድ ኦርጅናል በአንድ ፖስታ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል ::
- ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት በኋላ ባለው የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሠዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 10,000/አስር ሺ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል ::
ማሳሰቢያ፤ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 047 3360124
የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
__________________
Posted:አዲስ ዘመን መስከረም 9፣2013
Deadline:ለ21 ተከታታይ ቀናት
__________________
© walia tender