sl cmp pr fr vi mt tx የስናን ወረዳ ገ/

sl cmp pr fr vi mt tx የስናን ወረዳ ገ/


Walia Tender

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በምስራቅ ጐጃም የስናን ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ለባለበጀት ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ በመደበኛና በተራድኦ በጀት የተለያዩ

ሎት 1 የጽ/መሣሪያዎች
ሎት 2 ኮምፒውተር ተዛማጅ እቃዎች
ሎት 3 የድምጽና ምስል እቃዎች
ሎት 4 የኤሌክትሪክ እቃዎች
ሎት 5 የሃገር ውስጥ ፈርኒቸር
ሎት 6 የሞተር መለዋወጫ እቃዎች
ሎት 7 ህትመት
ሎት 8 የደንብ ልብስ ስፌት
ሎት 9 የተሽከርካሪ ጐማና ካለመንዳሪ
ሎት 10 ጫማ
ሎት 11 ብትን ጨርቅ
ሎት 12 የተዘጋጁ የሴትና የወንድ አልባሣት
ሎት 13 የስፖርት አልባሣት
ሎት 14 የመኪና መለዋወጫ እቃዎች
ሎት 15 የጽዳት እቃዎች

በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት/ለማሰራት/ ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ፡-

  1. በየዘርፉ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ምዝገባ ያላቸው፣
  3. ከ200 ሺህ ብር በላይ ለሆኑ ግዥዎች የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ከላይ የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚገዙ እቃዎችን እና መጠን ዝርዝር መግለጫ ከሰነዱ ጋር ማግኘት ይቻላል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሎት ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 30 በመክፈል ስናን ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ቁጥር 1 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና/ቢድ ቦንድ/ ለሎት 1 8000 ብር ለሎት 2 6000 ብር ለሎት 3 200 ብር ለሎት 4 ብር 200 ለሎት 5 ብር 1000 ብር ለሎት 6 ብር 4000 ለሎት 7 ብር 100 ለሎት 8 ብር 500 ለሎት 9 ብር 4000 ለሎት 10 ብር 1000 ለሎት 11 ብር 400 ለሎት 12 ብር 1400 ለሎት 13 ብር 300 ለሎት 14 ብር 7000 ለሎት 15 ብር 150 ኦርጅናል በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ለመ/ቤታችን ገንዘብ ያዥ ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራቾች በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅ ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያስያዙበትን ሲፒኦ ወይም ደረሰኝ በተለያዩ ሶስት ፖስታዎች አሽገው ሶስቱንም በአንድ ትልቅ ፖስታ በማድረግ በጥንቃቄ በማሸግ የመ/ቤቱን እና የአቅራቢውን ስምና አድራሻ በመፃፍ በህተምና ፊርማ አስደግፎ ስናን ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጠር 04 ዘወትር በስራ ሰዓትና ቀን ማስገባት አለባቸው፡፡
  9. የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ እስከ 15ኛው ቀን 11፡30 ድረስ በመግዛትና እስከ 16ኛው ቀን ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን እስከ 3፡30 ድረስ ማስገባት አለባቸው፡፡
  10. ጨረታው ላይ ለመገኘት ፍላጐት ያላቸው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት/ባይገኙም/ቢሮ ቁጥር 4 ጨረታው በጋዜጣ በወጣ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 በግልጽ ይከፈታል፡፡
  11. የጨረታ አሸናፊው የአሸነፉባቸውን እቃዎች ሙሉ ወጭ በመሸፈን ስናን ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት አምጥቶ የሚያስረክብ ይሆናል፡፡
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. ተጫራቾች እያንዳንዱን ዋጋ ሲሞሉ ከፍሉድ የፀዳ፣ ስርዝ ድልዝ ካለው ፓራፍና ተነባቢ መሆን አለበት፡፡
  14. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈለጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 4 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 2880 122/ 128 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  15. አሸናፊው ድርጅት በውሉ መሰረት ካላቀረበ የውል ማስከበሪያው ሙሉ ለሙሉ የሚወረስ ይሆናል፡፡
  16. መ/ቤቱ በሎት የሚያወዳድር ይሆናል፡፡

ማሣሰቢያ፡- የጨረታ መክፈቻ ቀን የመንግስት በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይከፈታል፡፡

አድራሻችን ከደ/ማርቆስ ከተማ በ27 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ እንገኛለን፡፡

የስናን ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት

__________________

Posted:በኩር መስከረም 18፣ 2013

Deadline:16ኛው ቀን 3፡30

__________________
© walia tender


Report Page