sl bu tx vi የቂልጡ ካራ ወረዳ ገ
Walia Tenderየጨረታ ማስታወቂያ
በምዕራብ ወለጋ ዞን የቂልጡ ካራ ወረዳ ገ/ኢ/ትብብር ጽ/ቤት ለ2013 ዓም የበጀት ዘመን በሥሩ ላሉት መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- የጽህፈት መሣሪያዎች/አላቂ ዕቃዎች/
- የፅዳት ዕቃዎች
- የተለያዩ የኤሌከትሮኒክስ ዕቃዎች
- የግንባታ ዕቃዎች
- የቴከኒክና ሙያ ሥልጠና መሣሪያዎች
- የደንብ ልብስና ጫማ
- የመኪናና የሞተር ሳይክል ጎማዎች ፣
በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል
- በዘርፉ ሕጋዊና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው
- የቫት ተመዝጋቢና ቲን (Tin)ቁጥር ያለውና የ2012 ዓ.ም ግብር የከፈለበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
- በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ተመዝጋቢና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
- ማንኛውም ተጫራች 5000.00 ( አምስት ሺህ ብ ር) በባንክ በተመሰከረ ቼክ (ሲፒኦ) ከጨረታው ሠነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል ሲሆን ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ይመለስላቸዋል
- ግዥው ሲፈፀም with Waldig (2 %) ለመክፈል ፈቃደኛ የሆነ
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 ሁለት መቶ ብር በመክፈል በቂልጡ ካራ ወረዳ ገ/ኢ/ትብብር ጽ/ቤት ከግዥና ፋይናንስ ሥራ ሂደት መግዛት ይችላሉ::
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ዝርዝር ሰነድ በትክክል በመሙላት የተለያዩ ደጋፊ ማስረጃዎች ጋር አያይዞ ኦሪጅናሉንና ኮፒውን በሰም በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለበት
- አሸናፊው ያሸነፈውን ዕቃ ጥራቱን የጠበቀና ኦሪጅናል ዕቃ ማቅረብ አለበት፤ኦሪጅናል ያልሆነና ያልታዘዘ ዕቃ ካቀረበ የመቀየርና የመመለስ ግዴታ አለበት
- የዕቃው ማስረከቢያ ቦታ ቂልጡ ካራ ወረዳ ገ/ኢ/ትብብር ጽ/ቤት ሆኖጠቅላላ ወጪው የአሸናፊው ግዴታ ነው
- የዕቃው ብዛት ሊጨምርም ሊቀንስም ይችላል
- ጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራት በመንግሥት መመሪያና ደንብ መሠረት ይሳተፋሉ
- ጨረታው አየር ላይ የሚቆየው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ 15 የሥራ ቀናት ሲሆን በ25//12/2012 ዒ. ም 10 ፡00 ሰዓት ድረስ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በቢሮ ቁጥር 4 ( አራት) ማስገባት ይኖርባቸዋል በዕለቱ 10 ፡00 ሰዓት ሳጥኑ ይታሸጋል በነጋታው በ26/12/2012 ዓ. ም ከጠዋቱ 4 ፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቂልጡ ካራ ወረዳ ገ/ኢ/ትብብር ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 4 (አራት) ይከፈታል። ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም በዕለቱ ፖስታው ይከፈታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
መረጃ ስልክ ቁጥር ፦0927505024/0935086 718/0934418675
በምዕራብ ወለጋ ዞን
/ የቂልጡ ካራ ወረዳ ገ/ ኢ/ ትብብር ጽ/ ቤት
__________________
Posted: አዲስ ዘመን ነሀሴ 5 ቀን 2012
Deadline: August 31, 2020
__________________
© walia tender