Selfie

Selfie

Selam_et

በሰሜናዊ ናይጄሪያ የሚገኝ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሞት ምክንያት የሆነው ተሰብስበው እራሳቸውን ፎቶ ሲያነሱበት የነበረው ድልድይ ተደርምሶ እንደሆነ 'ፐንች' የተሰኘው ጋዜጣ ዘግቧል።

ቡዋቺ በምትባለው የናይጄሪያ ግዛት ውስጥ በሚገኘው የአቡባካር ታፋዋ ባላዋ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ተማሪ የሆኑት ወጣቶች የሞቱት በዩኒቨርሲቲው ውስጥ የመማሪያ ክፍሎችንና የተማሪዎቹን መኖሪያ የሚያገናኛው ከብረት የተሰራ ድልድይ ሰኞ እለት በመፍረሱ ነው።

የዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዝዳንት ሙሃመድ አብዱልአዚዝ ስለአደጋው ሲናገሩ "ተማሪዎቹ ከባድ ዝናብ ከጣለ በኋላ በድልድዩ በኩል ሲያቋርጡ አካባቢው ለፎቶ አመቺ ነው በማለት በሞባይሎቻቸው ፎቶ መነሳት ጀመሩ" ብለዋል

ከዚያም ከ10 እና ከ15 ሰው በላይ መያዝ በማይችለው የመተላለፊያ ድልድይ ላይ ከ30 በላይ ተማሪዎች ተሰብስበው ፎቷቸውን በማንሳት ላይ ሳሉ ነው አደጋው የደረሰው ይላሉ ምክትል ፕሬዝዳንቱ።

"ድልድዩ ሲሰራ ከባድ ጭነት እንዲሸከም ሳይሆን ተማሪዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ አቋርጠው ከአንደኛው ህንጻ ወደሌላኛው እንዲሸጋገሩበት ብቻ ነበር" ሲሉ ለድልድዩ መደርመስ መሸከም ከሚችለው በላይ ሰው ስለተሰበሰበ መሆኑን ተናግረዋል- ምክትል ፕሬዝዳንቱ።

ስለአደጋው የወጡ አንዳንድ ዘገባዎች ከሞቱት ሦስት ተማሪዎች በተጨማሪ የተወሰኑ ተማሪዎች እንዳልተገኙ ቢያመለክቱም ምክትል ፕሬዝዳንቱ ግን ሐሰት መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህ በተማሪዎቹ ላይ በደረሰው አደጋ ምክንያት ማክሰኞ ዕለት የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ እንዳደረጉና ወደ አንደኛው የዩኒቨርሲቲው ግቢ የሚያስገቡ መንገዶችን በመዝጋት ሠራተኞች ወደ ውስጥ እንዳይገቡ አግደው እንደነበር ተገልጿል።

ሻሎም!

@selam_et

Report Page