S@

S@

Ƴ๏ni🔟😘✌ Ƴ๏.

➺ይድረስ በጣም ለምወድሽና ለማፈቅርሽ ለዉዷ ፍቅረኛዬ እማ ዛሬ አንቺ የሌለሽበት አዲስአበባ መጥቼ በጣም ከፋኝ በጣም የሌለ ደበሮኛል እማ አየሽ አንቺን ገና ስትሄጂ እዚህ መምጣት አስጠላኝ አንቺን ብቻ ብዬኮ ነበር የምመጣው ታድያ ዛሬ የለሽ እንዴት ልሁን ወለዴ እንዴት ሆድ ባሰኝ አቃተኝ✌↩ ፍቅር በጣም ደክሞኛል ከመብራት ሀይል መገናኛ በእግሬ ሄጄ ተመለስኩ አንድ ቦታ መቀመጥ አስጠልቶኝ ዉዴ ያላንቺ ምንም ነገር አይሆንልኝም ተቂ የለ ፍቅር አሁን ላይ ፍቅር

ልቤ አንቺን ብቻ ይሻል✌😭😭😭😭

እማ↪ስለታማኝነትሽ አከብርሻለሁ↪እወድሻለሁ↪አፈቅርሻለሁ 

ከናታን ላንቺ ለዉዷ ፍቅረኛዬ እማ እግዚአብሔር ከክፉ ነገር ይጠብቅሽ


ጥቅምት 2/2/2016 ዓ.ም fri 12:23 am

ሰላም የኔ ዉድ ከ11:00 ሌሊት ከነቃሁ ጀምሮ ሳስብሽ ነበር እማ አዳርሽ

እንዴት ነበር ? እማ የምር እኔ እንደማስብሽ ከእንቅልፍሽ ስትነቂ አንቺም

ታስቢኛለሽ እእ ዉዴ የምር እንደኔ ሁሌም ታስቢኛለሽ እማ ማርያምን ገና ስነቃ ጀምሮ እያሰብኩሽ ነበር ማሬ በጣም ናፍቀሽኛል ከፍቶኛል በጣም!

እማ እኔ በጣም ከፍቶኛል በጣም የምር እንዴት ካንቺ ተለይቼ ልቻለዉ..

↕የምር እማ አንቺ ግን የምር ጨካኝ ነሽ እንዴት በኔ ላይ ይሄን ያህል ጨከንሽብኝ የምር አቃተኝኮ ፍቅር እማ አንቺ ግን አስችሎሽ ነዉ የምር

ላንቺ ይሄን ያህል ቀላል ነዉ ማሬ የምር አስቻለሽ እኔኮ እየተጎዳሁ ነዉ

↕ትናንት ስዞር የተገናኘንበት ቦታዎች ሁሉ እንደአጋጣሚ ሄጄ ያላንቺ

አንቺ የሌለሽበት አዲስአበባ አስጠላኝ ወደ መጣሁበት መመለስ አማረ

ኝ የምር እኔኮ አዲስአበባ ስመጣ አንድ እና አንድ አንቺን ብቻ ብዬ ነበር

የምመጣሁ አሁን ታድያ በምን ሰበብ እመጣለሁ ሁለተኛ አልመለስም

የምር ከፍቶኛል ገና ስመጣ እየደበረኝ ነዉ የመጣሁት የምር ደስተኛ

ብዙም ደስተኛ አልነበርኩም ↪ናፍቀሽኛል↩↪እወድሻለሁ↩ናታን

ከናታን ላንቺ ለዉዷ ፍቅረኛዬ ባለሽበት↩↪አፈቅርሻለሁ ❤)


ጥቅምት 3/2016 ዓ.ም ቅዳሜ 4:05 am

➺ሰላም እማ እንዴት አደርሽ እየተመለስኩ ነዉ አሁን አዋሽን አለፍኩ እስከ 5:30 ደርሳለዉ ብዬ አስባለሁ እማ በጣም ከባድ ነዉ የመር ከፋኝ እኔንጃ ምን እንደምልሽ አላቅም ሁሉም ነገር ከአቅሜ በላይ ሆነብኝ የምር ከፍቶኛል ..😂😂😂

➺እማ በቃ ስገባ እፅፍልሻለሁ አሁን አልተመቸኝም በቃ ሁሉንም ነገር ቤት ስገባ እፅፍልሻለሁ መልካም ቀን👆

3/2/2016 ዓ.ም sat 10:05 am ዉዴ ሌሊት ከአዲስአበባ አበባ የወጣው አሁን ገና ምሳ በላዉ ቁርም አልበላሁም ፆምኩልሽ በቅዳሜ ምድር እና በጣም ከባድ ነዉ ስልኬም እያስቸገረኝ ብዙም አልፃፍኩልሽም ሰሞኑን ምክንያቱም ስልኬ stack እያረገ ፅፌ ፅፌ ያጠፋብኛል በጣም ተናድጃለሁ በጣም ከፍቶኛል በስልክ ጉዳይ ከፋኝ

መቼም የሆነ ቀን እኔም ደና ስልክ እገዛ ይሆናል አስከዛዉ ድረስ ስልክ

ሲደወልም ቢሆን ማንሳት አያቅታትም👆😘

3/2/2016 ዓ.ም ቅዳሜ 11:30am እማ እኔ ካንቺጋ ብዙ አልሜ ብዙ ነገርም አቅጄ ነበር ሁሌም ቢሆን ነገዬ የተሻለ እንዲሆን ነበር ምኞቴ እማ የምር ወደፊት ካሁኑ የቀለጠ ፍቅር ይኖረናል ብዬ አስባለሁ 👆 እማ

መቼም እንደማትለይኝና ምንም አይነት መከራ ቢገጥምሽም እንደማንለ

ያይ ቃል እንድትገቢልኝ እፈልጋለሁ የምር ስልክ ስተደዉይልኝ የምጠይቅሽ የመጀመሪያ ንግግሬ ነዉ ቃል እንድትገቢልኝ እፈልጋለሁ

3/2/2016 ዓ.ም ቅዳሜ 2:52 pm

➺እማ እንዴት አመሸሽልኝ የኔ ዉድ ነገኮ 2 ወር ይሞላሻል ቃል የተገባል

ኝኮ እስከ 2 ወር ነበር ከዛ ቡኋላ በቀን ሳልደዉልልህ አላድርም ተብዬ ነበር ነገር ግን እንደሄጅሽ ቶሎ ስራ ስላልጀመርሽ በጣም አሞሽ እንደነበ

ር ሰምቻለሁ ስለዚ ስለዚ አሁንም አንድ ወይ ሁለት ወር ሊያስፈልግሽ ነዉ ይከብዳል በጣም ያማል ይሄ ሁለት ወር እራሱ እንዴት እንዳለቀልኝ

እኔና እግዚአብሔር ነን የምናቀዉ የምር በጣም ከባድ ነበር በጣም ዉዴ

እግዚአብሔር ሲፈቅድ ነዉ ሁሉም ነገር የሚሆነዉ የኔ ጣፋጭ ብቻ ታማኝ ሁኚልም መቼም እና በምንም አይነት ፈተና ዉስጥ ብትሆኚም ለራስሽ ክብር ተጨነቂ መቼም ቢሆን ከዛ ሁሉ መከራ እና ፈተና ያወጣሽ 

እግዚአብሔርም ጥሎ አይጥልሽም ይጠብቅሻል☝➺ናታን💝3:00p


ጥቅምት 10/2016 ዓ.ም ቅዳሜ 2:41 pm

የኔ ፍቅር በጣም ናፍቀሽኛል አንቺን ሳላስብ አንድም ያለፈች ደቂቃ የለችም የምር ከቃል በላይ አፈቅርሻለሁ እግዚአብሔር ባለሽበት በሰላም ይጠብቅሽ ያበርታሽ በልብሽ ያለዉን ፍቅር ያፅናልሽ👆


ህይወትማ *

ህይወትማ እንዲ ናት ቀኝ የሌላት ግራ፣

ሞልታ የማትሞላ የምኞት ተራራ፣

ጥጋብ ያላደላት የርሀብ ጎተራ፣

ፍሬ የሌለባት የምድር አዝመራ፣

ህይወት በረዶናት ሲላት ትቀልጣልች፣

ዶፏን ታዘንብና ጎርፏን ትሰዳለች፣

እኔማ ሳስባት ታስገርመኛለች፣

ከሌለው ለይ ነፍጋ ላለው ትሞላላች፣

ሟችን ካ'ፈር ከታ ገዳይ ታኖራለች፣

ለጋሽን ደብቃ ሌባ ታነግሳለች፣

እውነትን ወህኒ ሀሰትን ነፃ አውጪ፣

የመኖርን ተስፋ ባለመኖር ቋጪ፣

ህይወት ተቆጪ ናት ቁጣዋ የከፋ፣

ቁም ስቅል ምታሳይ ደካማን ነፍስ ገርፋ፣

መምህር ናት አሉ ጎድታ ምታስተምር፣

ዲግሪ የማትሸልም የጎንዮሽ ችግር፣

ቀዳዳዋ ብዙ ማምለጫ የሌላት፣

ቀኝ የሌላት ግራ ህይወት እንደዚ ናት፣


1⃣ ሰዉ የተመኘዉን ባያገኝም

   ፈጣሪ የፃፈለትን ግን አያጣም


2⃣ ጠንካራ ሰዉ ሁን ማለት

   አትዉደቅ ማለት አይደለም 

   ወድቀህ መነሳት ልመድ እንጅ !


3⃣ ከጀርባህ የሚያወሩትን አንተ

   ከፊታቸዉ ስለሆንክ ነዉ

   ስለዚህ አንተ መራመድህን ቀጥል


4⃣ አንዳዴ በሰዎች ህይወት

   ዉስጥ ጣልቃ አለ መግባት በራሱ 

ሰዎችን መርዳት ነዉ


5⃣ ትልቅ የሚያስብልህ እድሜህ

   ሳይሆን አስተሳሰብህ ነዉ

ስለእንባ 😢😢😢😢✔ማልቀስ💔💔💔💔💔💔😂😂😂😂

እንባ አምላክ አለው። እንባ ሲወርድ ውኃ ነው፤ ሲመለስ ግን እሳት ነው። እንባ ሲወርድ ይበርዳል ያረፈበትን ግን ያቃጥለዋልና ሰዎች ሲያለቅሱብህ ፍራ፤ ፍርዱን አትችለውምና።


ህይወትን በቀናት!


➫በደስታም ይሁን በሃዘን ቀናት ያልፋሉ ፣ ይሄዳሉ ። ህይወትም በእነዚህ አላፊ ቀናት ውስጥ የምታልፍ ክስተት ነች ። ዛሬን ባንደሰት ፣ ዛሬን ባንረካ ፣ ያሰብነውን ነገር ባናደርግ ፣ ባቀድነው ልክ ባናሳልፋ ከህይወታችን እየቀነስን ፣ ከመኖራችን እያጎደልን እንሔዳለን ። የምንኖራት ቀን ገና የምትመጣ አይደለችም ፤ የምንደሰትባት ቀን ገና ያልተፈጠረች አይደለችም ፤ የእራሳችንን ሰላም የምናገኝበት ፣ የምናረጋግጥበት ጊዜ ገና የሚመጣ አይደለም ። ህይወት በእያንዳንዱ ቀናት የምትኖር ፣ የምትደምቅ ፣ የምታስደስት ፣ ሰላምን የምትፈጥር ነች ። የተሻለ ጊዜ ይመጣል ዛሬ ግን እጅጉን የተሻለና ምርጡ ቀን ነው ። ዛሬን እየሸሹ ነገን መናፈቅ ብክነት ነው ። "በህይወቴ ደስተኛ ነኝ ፣ ስኬታማ ነኝ ፣ ህይወቴ ሙሉ ነው ።" የሚል ሰው ዛሬን የሚኖር እንጂ በነገ ተስፋ ዛሬውን የሚገፋ አይደለም ።


😒😏ይቺ አለም በአስመሳዮች የተሞላች ነች ለአንተ ሁሌም መልካም የሚመስሉክ ሰዎች አንድ ቀን መጥፎና እርባና ቢስ መሆናቸውን ስትረዳ ዳግም አይናቸውን እንኳን ለማየት ፍፁም ያስጠሉካል ይህም የሚሆነው ከበቂ በላይ ስታምናቸው ስለነበረ ነው።


   ━━━━🥀⊱✿⊰🥀━━━━━


።።።።።።ሣቄ ካልገባቸው።።።።።።።


የህመሜን ጫና በሳቄ በሸፈንኩ

ደስተኛ ለመምሰል ከደስተኞች በዋልኩ

በሰባራው ልቤ ድጋሚ በወደድኩ

ተከፍቶ የማያውቅ ደስተኛ ነው ተባልኩ

  

 ይሁን ይሙላላቸው

ሰባራን ጠግኖ አዲስ ካስመሰለ

ጥርስን በመሳቁ የደስታ ካስባለ

ታሞ መደበቁ ተድላ ከተባለ

እንዳፋቸው ሆኖ ባይከፋኝ ምናለ


ግና ሳይሆን ቀርቶ

ሳቄን ላጥፋውና ህመሜን አውጥቼ

እምባን እያስበለጥኩ መጫወቴን ትቼ

የመከፋቴን ጥግ ባዘን አሳይቼ

ከሰዎች መዋሉን ማመኑን ፈርቼ

አዝኗል እንዲሉ

   ልተዋቸው እንዴ ሁሉንም ገፍቼ


   ወይ እንዲገባቸው

የህመሜ ክብደት ገኖ ካልታያቸው

የልቤ ስብራት ካላስጨነቃቸው

ሁሉን እንደቻልኩት ሳቄ ካልገባቸው

ወይም እንዲረዱኝ ሞቼ ልለያቸው።


    ━━━━🥀⊱✿⊰🥀━━━━━

   ..ይነበብ ✋

ህይወት አዙሪት ናት!

መጀመሪያዋና መጨረሻዋ አንድ ነው።

በለቅሶ ትጀምራለህ፤ በጭንቀት ትጨርሳለህ።

በሰው እቅፍ ትጀምራለህ፤ በሰው

ሸክም ትጨርሳለህ። ……

ህይወት_አዙሪት_ናት!


ረጅም ርቀት የተጓዝክ ቢመስልህ፤ የምትጨርሰው ከጀመርክበት ነው ። ራቁትህን ትወለዳለህ፤ እርቃንህን ወደ መቃብር ትወርዳለህ። 

በጥርስ አልባው ድድህ እየጋጥክ ትጀምራለህ፤ ጥርሱን በረገፈው ድድህ እያልጎጠጎጥክ ትጨርሳለህ ። 


ዘመንም ተምኔታዊ ነው። መስከረም፣ ጥቅምት ብሎ ያስጀምርህና መስከረም ብሎ ይመጣብሀል። ሰኞ፣ ማክሰኞ ብለህ ተጉዘህ እንደገና ሰኞ ትላለህ ።


ህይወት አዙሪት ናት። መጀመሪያህ መጨረሻህ ነው። የጀመርክበትን አትናቀው፤ ትጨርስበታለህና። 


ተራ ሰው ሆነህ ትጀምራለህ። ተምረህ ዕውቀት ብትጨምር ፣ነገ ህዝብ ብትበታትን፣ተሹመህ በህዝብ ላይ ብትሰለጥን፣ ክቡረ ክቡራን ሆነህ የወርቅ ካባ ብትለብስ፤ የምትጨርሰው እንደ ተራ ሰው አፈር ለብሰህ ነው ።


ባለማወቅ ትጀምራለህ፤ በመዘንጋት ትጨርሳለህ። ዕውቀት አላመጣህምና ዕውቀትም ይዘህ አትሔድም። 


በለቅሶ ትጀምራለህ፤ በጭንቅት ትጨርሳለህ። በሰው እቅፍ ትጀምራለህ፤ በሰው ሸክም ትጨርሳለህ ። 


ህይወት መጀመሪያዋና መጨረሻዋ አንድ ነው። ርቀህ የሔድክ ቢመስልህም ትልቅ ክብ ሰርተህ ትመለሳለህ ።.....


ብትታመን ምን ታጣለህ?

፨፨፨፨፨/////////፨፨፨፨፨

ብትታመን ምን ታጣለህ?

ባትታመንስ ምን ታገኛለህ?

አብዛኛው ሰው የእራሱን ጥቅም አሳልፎ መስጠት አይፈልግም፤ ለዛም ሲል ይዋሻል፤ ይክዳል፤ ቃሉን ያጥፋል፤ ያስመስላል፤ ተንኮልን ይሰራል። እራስን መውደድ በዚህ መልኩ ቢሆን ከውስጥ የሚሰማው እርካታ ይናገር ነበር። ነገር ግን አይደለም።

አዎ! በውሸት ውስጥ እርካታ የለም፤

በክህደት ውስጥ ደስታ የለም፤

ባለመታመን ውስጥ እረፍት የለም፤

በተንኮል ውስጥ ሰላም የለም።

አንዳንድ ጊዜያዊ ስሜቶች ላልተገባ ምላሽ ሊዳርጉን ይችላሉ፤ ፅንፍ የወጣ እራስ ወዳድነትም የሌላውን መብትና ጥቅም በመርገጥ የሚመጣን ጥቅም በማሯሯጥ የሚታወቅ ነው። መብቱን የምንጋፋው ሰው እንዲሁ የኛን መብታ ቢጋፋ የሚሰማንን ስሜት መቃኘቱ ተገቢ ነው።

አዎ! ጀግናዬ..! ብትታመን ምን ታጣለህ?

ለእራስህ፣ ለቃልህ፣ ለህሊናህ ብትታመን ምን ይጎድልሃል?

ቁሳዊ ጥቅም፣ ገንዘብ፣ ንብረት፣ ከሃዲ፣ ውሸታም ሰው ልታጣ ትችላለህ። እራስህን ግን መቼም አታጣም። በማንኛውም ሁኔታ ያለህ አመኔታ ለእራስህ ነው። ጊዜያዊ ጥቅም ብታጣም ዘላቂው ሰላምህ፣ እረፍትህ አብሮህ ይቆያል። 

በብዙ ታምኖ በትቂቱ እንዳለመታመን ምን አስነዋሪና አስከፊ ነገር አለ?

እምነት ከቤተሰብ ይመጣል፤ ከወዳጅ፣ ከዘመድ ይመጣል፤ ከህይወት አጋር ይመጣል፤ ከፍ ሲልም በሃገር ደረጃ ይሰጣል። እርከኖቹ ቢለያዩም ታማኝነትን ለማሳየት ሁሉም በቂ ናቸው። በጥቁቱ ያልታመነ በብዙም አይታመንም። ለቤተሰቡ ያልሆነ ለሃገሩ አይጠቅምም፤ ለፍቅሩ ያልታመነ እንዴት የሀገር አደራ ሊወጣ ይችላል?

አዎ! ባለመታመንህ ምን ታገኛለህ?

በማጭበርበርህ፣ በመወስለትህ፣ በማስመሰልህ፣ በመዋሸትህ ምን ታተርፋለህ?

እውቅና፣ ዝና፣ ነገ የሚጠፋ ክብር፣ ንብረት፣ ገንዘብ። ነገር ግን በምትኩ እራስህን እንደምታጣ እወቅ። የገባሀው ቃል፣ እውነታውን የሚያውቀው እዝነ ልቦናህ ረፍት እንደማይሰጥህ፣ ሰላም እንደሚያሳጣህ፣ ለአዕምሮህም ጭንቀትን እንደሚያተርፍልህ ተገንዘብ። ትልቁን አገኛለሁ ብለህ በገንዘብ፣ በግዢ የማታገኘውን ወድ የሰውነት፣ የአንተነት ስጦታህን፣ ሰላምህን፣ ደስታህን፣ እረፍትህን እንዳታጣ ተጠንቀቅ።

አዎ! ለህሊናህ ታመን፤ ቃልህን አክብር!

ባለመታመንህ ከምታጣው፣ በመታመንህ የምታገኘው ወድ በረከት ያሳስብህ። ክህደት እንዲያወርድህ፣ ውሸትም እንዲያዋርድህ አትፍቀድ፤

መታመን እንዲያነሳህ፣ እውነተኝነትም እዲያስከብርህ አድርግ።


ውብ ምሽት ይሁንልን!

...✍️...ሰላም ጀግናዬ...✍️...


ዓለም ላይ ችግር የሌለበት አንድም ሰው የለም ይነስም ይብዛም ሁሉም የራሱ ችግር አለበት። ነገር ግን አንዳንድ ሰዎች ላይ ችግር አብሯቸው እንደሆነ በግልፅ ይታያል አንዳንድ ሰዎች ጋር ደሞ በፍፁም የችግር ወይም የድክመት ምልክት አይታይባቸውም። ለዚህም ትልቁ ምክንያት ችግራቸውን የተቆጣጠሩበት መንገድ ነው። ዛሬ ያልመራኸው ችግር ነገ ወደ ፈለገው መንገድ ይመራሃል ወደ መጥፎ ወደ ማፈልገው ህይወት ይወስድሃል ወደ ገደል ወደ ጨለማ ያስገባካል። እናም እልሃለው ችግርክ ላይ ድክመትክ ላይ ስልጣን ያዝበት የዛኔ ድራሽዓባቱ ይጠፋል እሱ ሳይሆን አንተ ተቆጣጠረው ወደ ፈለገው ሳይሆን ወደ ፈለከው መንገድ ምራው ቀስ በቀስም ቢሆን ለችግርህ መፍትሄ ያለው ከሆን መፍትሄ ስጠው መፍትሔ የማይኖረው ከሆነ ደሞ አምነህ ተቀበለው እና ጣፋጭ ህይወትህን አጣፍጠህ ኑረው


--🌹🌹የናፈቅሽኝ እለት 🌹🌹--


ንፍቅ ያልሽኝ እለት ትገኛለሽ ብዬ

  በፍለጋ ጉዞ ምድርን አካልዬ

ስማስን በዱሩ፣

 ሳስስ በባህሩ.........

በሜዳ ገደሉ

ሲመሽ እየነጋ ሲነጋ ቢመሽም

ያለሽበት የለም አንቺ አልተገኘሽም

 አየሽ.........

እንደ ዘዶ ስሳብ ...እንደጥጨል

ስዘል...እንደ አሞራ ስበር

❤ልቤ ውስጥ እዳለሽ ልብ አላልኩም ነበር።


ልብ በል!

አሁን ያለህበት ሁኔታ አንተን አይወስንህም ወይ አንቺን አይወስንም ፤ አሁን ያለህ ነገር የዛሬ አምስት አመት ጀምሮ ታስባቸው የነበሩ ታረጋቸው የነበሩ ነገሮች ውጤት ነው ። 


አሁን በተደጋጋሚ የምታስበው ፣ የምትሰራው ፣ የምታደርገው ነገር ደግሞ ቀጣይ 5 ዓመትህን ይወስናል ስለዚህ በተደጋጋሚ ስለምታስበው ፣ ስለምትሰራው ፣ ስለምታደርገው ነገር ወስን !


ለእህቴ 

"እርጎ ውስጥ እደገባችዋ ዝንብ ህይወትሽ በጠጪው እጅ አይወሰን"


✍. አንቺ ሴት ነሽ የእናትሽ ልጅ ሴት ! ዓለም ላይ ቀድመሽ ሰልጥኚባት እንጂ ዓለም ቀድማ

እድትሰለጥንብሽ አትፍቀጂላት!!. ዓለም ሰርተሻት ወይም ሰርታሽ እድትተላለፉ አማራጭ

ተሰጥቶሻል. . ! ምርጫሽ ሁለቱም ይሁን. . !

 አልፎ አልፎ ትስራሽ አልፎ አልፎም 

ስርያት. 


✍. ውበትሽ ብቻውን በገንዘብ የሚሽጥ ፣ የሚለወጥ የአደባባይ ርካሽ እቃ ነው እንጅ አንድ ወንድን የራስ ብቻ አድርጎ ለመያዝ ውበት ብቻውን በቂና ዋጋ ያለው አይደለም ! ልብ -በይ ! ከውበት ጋር ግን ታማኝነት፣ የፍቅር ልብ ፣ ሃቀኝነት ፣ ትግስት ፣ እምነት እና ሰብዓዊ እውቀትሽ የምታውቂባቸው ልዮ መገለጫሽ ይሁን !!

 

✍. አንች ልትይዥው ያልቻልሽውን ነገር ሌሎች እንዲይዙልሽ አታስገድጃቸው። ልታደርጊው የምትፈልጊውንም ነገሮች ከመናገርሽ በፊት ደግመሽ አስቢበት !!! ማድርግ እንደምትችይ እርግጠኛ ከሆንሽ ዝም ብለሽ የማድርግ ልምድ ይኑርሽ ።


✍. ምታልሚው ህልም ይኑርሽ ህልሞችሽ ካለሽበት ብቃት የላቀ ይሁን ከዛን ህልሞችን እመኛቸው ! ዘለዓለማዊ በር የተደበቀው እነርሱ

ውስጥ ነውና !


✍. በተስፋና ምኞቶችሽ ጥልቀት ውስጥ ዝምተኛ ዕውቀት ይገኛልና ፈልጊያቸው ! አዎ አንቺ

ያቺ ሴት ነሽ ተስፋሽን ምታትሚ ፣ ምኞትሽን ምትቀርጪ!


✍. ፀሃይ የቱንም ያህል ቃጠሎዋ ቢበረታብሽ

ጥላውን ሌላው እዲይዝልሽ አትጠብቂ . . .

መከላከያዋን አንቺው ስሪና አንቺው ወደተመረጠ

ው ሰላም ግቢ!


✍. አንቺ በዓመት አንድ ቀን ተሰጥቶሽ ቀንሽ

የሚባልልሽ በዓል አይደለሽም እነዚህ እንደ ህፃን ከረሜላ ሰጥተው ፖለቲካቸውን ለሚያሸበርቁ ሰዎች አሻንጉሊት ለመሆን አትፈቀጂላቸው. !

ላንቺ ሁሉም ቀን ቀንሽ ነው!


✍. አቋምሽ ባህሩ ዳርቻ ከመድረሱ በፊት በየመ ውረጃው ማዕዘናቱን በየመጠምዘዣው ላይ ኃይሉ እየቀነሰ የሚንቀራፈፍ ዝርግ ወንዝ ዓይነት አይሁን


አስተውይ ! ጨዋነትሽና መተናነስሽ ከክፉ ዓይን የም

ትከላከይበት ጋሻሽ ነውና ሆሌም ያንቺ አለቃ አርጊያቸው. . !


✍. እራስሽን ገንዘብና ገንዘብ ሊገዛቸው ስለሚች ለው ነገር እያሰብሽ ማንነትሽን ለጫረታ አታቅርቢ ውስጥሽን ገንዘብና ወዳጆቹ በማይገዛቸው

ነገሮች ሙይው ! ያኔ ቁስ ባርያሽ ይሆናል አንቺ

አለቃው !


✍. ሰው ካለው ከተፈጥሮው አመለካክቱ በስተቀር የተቀሩት ድርሻዎቹ በጊዜና በቦታ ተጽኖ ተለዋዋጭ ረጋፊ በመሆናቸው። ለምርጫሽ መመኪያና መለኪያዎች ሊሆኑ አይገቡም።


✍.አንቺ ውብ ነሽ ምክንያቱም ሴት ነሽ

✍.አንቺ ብልህ ነሽ ምክንያቱም ሴት ነሽ

✍. አንንቺ ሴት ነሽ ያውም ጀግና ሴት

✍.ምንም ማረግ ትችያለሽ ዓለም ያላንቺ ጨረቃ ያኮረፈቻት ፀሃይ የተቀየመቻት ጨለማ ናት 

✍.ሁሉም ቀን ቀንሽ ነው 

✍. አንቺነትሽ ይለምልም ሊነካሽ ያሰበ እሱነቱ የተናቀ ይሁን

.....የልቤ.ላይ.ንግስት..... 



አርቆ አሳቢ ነሽ አውቃለሁ ስላንቺ

አስተዋይ እንደሆንሽ ደካማን አበርቺ

የቆንጆዎች ቆንጆ የውቦችም ውብ ነሽ

ፍፁም ሰው አክባሪ ትሁት ቅን ልብ ያለሽ


አፍንጫሽ ሰልካካ ከንፈርሽ ኢነጆሪ

የማትጠልቂ ፀሐይ የልቤን ጨለማ የምታበሪ

አንገትሽ መለሎ ፀጉርሽ ዘነፍናፋ

ምናለ ላንቺ የዘነበልሽ ለሌላው ቢያካፋ


ደግና ታጋሽ ነሽ ማራኪ ገፅ ያለሽ

ከመልክም መልክ ያለሽ

ከፀባይም ጥሩውን ያደለሽ

በሀብትሽ ማትኩራሪ ለሁሉም እኩልነሽ

ትንሹም ትልቁም ሁሉም የሚወድሽ

እኔማ አውቃለሁ እንደማልመጥንሽ

ስታዝኚ አዝናለሁ እጅጉን ሲከፋሽ


አስከፊ መልክ ያለኝ በጣም አስቀያሚ 

ላንቺ የማልገባ የፍቅርሽ ታማሚ

አንቺ ማለት ለኔ የልቤ ብርሀን ነሽ

የመኖሬ ምክንያት የደስታ ምንጬ ነሽ


አይበቃኝም ከቶ ቃላት ብደረድር

አንቺን አይገልፅልኝ አይሆነኝ ምስክር

ምን ብዬ ልግለፅሽ እስትንፋስ ህይወቴ

ደስተኛ የሆንኩበት አንቺ ነሽ ምክንያቴ


ልቤን ወሰድሽብኝ ገና ያየሁሽ ለት

ምን ልበልሽ በቃ አንቺ የልቤ ንግስት 

ልቤ ከነፈልሽ ባንቺ ፍቅርማ

አንቺ የኔ የበላይ የማንነቴ አርማ

አንቺ ልዕልት ነሽ እኔ ደሞ አሽከርሽ

ላንቺ የማልገባ ታማኝ ስለ ፍቅርሽ


.....✍ናታን


.....🙏እንዴት አረፈዳችሁ🙏......


.........​ህይወት

    እስኪያልፍ እሚያልፍ አይመስልም…ሁሉም እስኪሄድ እሚሄድ አይመስልም…ሲመሽ እሚነጋ አይመስልም…ስንጠግብ እሚርበን አይመስለንም…


   ግን ወዳጄ…ሁሉም ይቀያየረል… ለምን ሆነ አትበል… ከሆነው ጋር መኖርን ግን ተማር… ደስታ ምርጫ ነው… ደስታ እሚስጥህን ነገር ስትመርጥም ተጠንቀቅ…አንዳንዶች ጊዚያዊ ናቸው…እሚወቅስህን አትጥላ… እንዴትም ብትኖር ከወቀሳ አትድንም እና … በህይወትህ ሁሌም ቀጥሎ ያሉት ነገሮች ይከሰታሉ…


    …አረሳህም ያለህ ሊረሳህ ይችላል…

    … አልተውህም ያለህ ይተውሀል…

    … የመረከው ይረግምሀል…

    … ያሳከው ያስለቅስሀል…

    … ወዳጄ ያለከው ጠላትህን ይሆናል…



   እናም… ተመስገን ብለህ ማለፍን ተማር… ከሚመስሉህ ጋር ጊዜህን አሳልፍ… ለዋጋ ብለህ ነገሮችን አታድርግ… ከሚቀያየሩ ስሜቶች ጋር አትቀያየር… የተቀረውን ለፈጣሪ ተወው።


💚💛❤️አይደል እንዴ💚💛❤️

💚💛❤️ውብ ቀን💚💛❤️

━━━━━━━━ ❈ ━━━━━━━━

     ​••● እንዴት ላውራሽ ? ●​••


ባንቺ ናፍቆትማ ሸፈተና ልቤ

እዛ እዚህ ተበታትኖ የኔማ ሀሳቤ 

ቁንጅና ውበትሽ ሳቅሽ ተጨምሮ

ጨዋታ አዋቂነትሽ እሱም ተደምሮ

አስጨናቂው ዝምታሽ ባንድ ላይ አብሮ

በፍቅርሽ ማበዴ ነው እኔማ ዘንድሮ


          ወይ ዘንድሮ 🤭...

     ንገራት ይሉኛል ቃላት አገጣጥመህ

   እኔኮ ከልቤ እወድሻለሁ ብለህ

  መች ሚነገር ሆነና የኔ መውደድ በቀላል 

   ፍቅር ለመናገር በጣሙን ይከብዳል


           ግና...

አውራኝ ስትይኝ እንዴት ላውራሽ ውዴ

አፌ እየተሳሰረ እየተሸበረ ሆዴ

ልቤ እየመታ ማውራት እችላለሁ እንዴ?


          ስሚኝማ ውዴ...

     እኔ አንቺን መውደዴ 

    ችግር አለው እንዴ?

  ኧረ ችግር የለውም ፍቅርህን አምናለሁ

   ብለሽ ካሰብሽማ ነይ እጠብቅሻለሁ 

     ከልቤ እወድሻለሁ 😘

━━━━━━✦✗✦━━━━━━━


ጥቅምት 12/2016 ዓ.ም ሰኞ 4:00 am

የኔ ከፋኝ አንቺን አጥቼ ምን ደስተኛ ልሆን አልቻልኩም አቃተኝ።


ጥቅምት 12/2016 ዓ.ም ሰኞ 4:00 pm👇👇

✔ይድረስ ላንቺ ለዉዷ ፍቅረኛዬ እማ እንዴት ነሽልኝ ደና አመሸሽልኝ ዉዴ በዚች ስልክ በጣም ብዙ ደብዳቤዎችን ፅፌልሻለሁ ነገር ግን ወዴ

አሁን እምቢ አለኝ አንዴ ከዘጋ በጣም ይቆያል ለመሙላት ዉዴ በጣም እያስቸገረኝ ነዉ ላንቺ ብዙ ደብዳቤዎችን የፃፍኩልሽ በዙሁ ስልክ ነበር

ነገር ከዚህ ቡኋላ በቀን ሶስት አራት ጊዜ አይደለም ቶሎ ቶሎ ላልፅፍልሽ እችላለሁ ምክንያቱም ስልኩ እያስቸገረኝ ነዉ እስካሁንም ዉዴ ብዙ ጊዜ ፅፌልሽ አጥፍቶብኛል አንቺ ግን የምር አስቻለሽ የምር

ከኔ ርቀሽ መኖሩን ለመድሽዉ የምር አስቻለሽ ያ ሁሉ ፍቅራችን በቃ ስልክ እንኳን አትደዉይም የምር ለመደወል ስላልተመቸሽ ነዉ ፍቅር ለኔ

መደወል ባትችይ እንኳን ጓደኛሽ ቤቲጋ ደዉለሽ ያለሽበትን ሁኔታ አታሳዉቂኝም የምር ግን ታቂ የለ ባንቺ እንደማልችል እ ፍቅር አንቺ እኔን ታቂኛለሽ አይደል ባንቺ እንደማልችል እያወቅሽ ዉዴ የምር ይሄን ያህል የጨከንሽብኝ እንደምወድሽ ስላወቅሽ ነዉ አይደል እኔ ከብዶኛል በጣም የምር አልቻልኩም ዉዴ አሁን ደሞ የምናወራበት ሰዓት ደረሰ 4:10 ቢበዛ 10 ደቂቃ ነበር የምጠብቅሽ 4-4:10 ነበር የምጠብቅሽ አሁን ግን የለሽም ማለቴ አንቺ ለኔ እንጂ እኔ ላንቺ መደወል አልችልም በጣም ከፍቶኛል ይሄን ሳስብ የሌለ ይከፋኛል 💔💔💔💔💔💔

ደም ዛሬም አዲስ ፎቶ ተልኮላቸዋል imo pp ላይ አርገዉታል ለነሱማ ይላካል ፎቶ ለኔ እንጂ አምሮብሻል ደስ ብሎኛል እኔ ግን ትተሽኝ ከሄድሽ ቀን ጀምሮ አንድም ቀን ስቄ አላቅም እንኳን ፎቶ ልነሳ ይቅርና ደስታ ከራቀኝ ቆየሁ የምር እማ አልቻልኩም መጥፎ ነገር ዉስጥ እንዳልገባ እግዚአብሔር ይጠብቀኝ እንጂ የምር በጣም ከባድ ነዉ☝☝

✔እማ ግን እንዴት ጨከንሽብኝ እንዴት አስቻለሽ እማ የምር ቻልሽዉ

እኔ ግን አልቻልኩም ከብዶኛል ልቤ ተሰበረ የምር💔

✔የኔ ዉድ ዝምታሽ ያማል የምር እንዴት አስቻለሽ እኮ እንዴት💔 ላንቺ ያለኝን ፍቅር እያወቅሽ እንዴት እማ እንዴት ቻልሽዉ☝☝☝

✔እማ የእውነት ግን በጣም ጨካኝ ሆነሻል በጣም እንዴት በኔ ላይ እማ ይሄ ሁሉ ጭካኔ ከየት አመጣሽ ቢያመኝም እጠብቅሻለሁ☝

  ከናታን ላንቺ ለዉዷ ፍቅረኛዬ 

ስለታማኝነትሽ✔አከብርሻለሁ↔እወድሻለሁ↔አፈቅርሻለሁ 💔


    ጥቅምት 12-2016 ዓ.ም ሰኞ 9:00pm👇❤💔

✔ዉዴ በጣም ከፋኝ አምባዬ መጣ አንድም ይሄን ያህል ተጨክኚብኛለሽ ብዬ አስቤ አላቅም ልቤ ተሰበረ💔ዉስጤም በጣም ተጎዳ አለሜ ነበርሽ ዉስጤ ተጎዳ የምር አልቻልኩም አቃተኝ ወይ እማ አላሳዝንሽም ግን በፍቅርሽ እንዲ ስሰቃይ የምር ግን ያ ፍቅር በልብሽ አለ ወይስ ጠፋ ከፋኝ💔💔💔

✔10:27 pm እማ የምር ያማል በጣም ከፋኝ በጣም በጣም ከፋኝ አልቻልኩም አቃተኝ ሙሉ ልቤን ሰጥቼሽ ነበረ ልቤ ተሰበረ ለምን እማ ለምን ምን በደልኩሽ ይሄን ያህል 💔💔💔

✔እማ ናፍቆትሽ አመመኝ ከፋኝ ሶስተ ወር ድረስ ለመቸቆየት እየሞከርኩ ነበር ዛሬ ግን በጣም ከፋኝ አይኖቼ በእምባ ተሞሉ ከበደኝ ምን ላድርግ አቃተኝ በጣም ከፍቶኛል በጣም ዉስጤ ተረብሿል💔

✔እማ እንዴት ልቻለዉ እኮ እንዴት ቢያንስ ሁለት ወር ነበር ያለሽኝ ሁለት እንደምንም በስቃን በናፍቆትሽ እየተቃጠልኩ አንድ በአንድ ቀኑን እየቆጠርኩ አለቀ ቢዘባ ሶስት ወር ይሁን እስከ ህዳር 4 እንደምንም ለመቻል እሞክራለሁ ግን የዛሬዋ ቀን የበለጠ ከበደችኝ በጣም ከፋኝ ልቤ ክፉኛ ተሰበረ አልቻልኩም ያላንቺ ህይወት አስጠላችኝ💔

✔ዉዴ ተከፋሁ አዘንኩ ዉስጤ የሚያዉቀ አንድ እግዚአብሔር ብቻ ነዉ አለሜ ነበርሽ አንቺ ጥለሽኝ ስትሄጂ ከምር ህይወት ጨለመችብኝ የምር ሰማይ የተደፋብኝ ያህል ጨነቀኝ ማርያምን ከፋኝ↔

✔ዉዴ እኔ በዚህ ሰዓት በጣም ከፍቶኛል በጣም ማርያምን አልዋሽሽም በጣም ከፍቶኛል በጣም በጣም በጣም ከፍቶኛል አቃተኝ አልቻልኩም በጣም ነዉ የከፋኝ በጣም የምር ሁሌም ይከፋኛል ነገር ግን እማ አልቻልኩም በጣም አሞኛል በጣም በጣም ናፍቆትሽ ህመም ሆኖብኛል እማ አሞኛል ከፋኝ በጣም ከፋኝ ዉዴ እኔ ልሞትብሽ ነዉ

✔እማ ልቤን ሰጥቼሽ ለምን ለምን እማ😢😢😢😂 የኔ መከፋት ላንቺ

ምን ይጠቅምሻል እማ እኔ ከፍቶኛል በጣም በጣም በጣም ከፍቶኛል እኔ ምን ብበድልሽ ነዉ ይሄን ያህል ምን አጠፋሁ ይሄን ያህል የምቀጣዉ ምን አረኩሽ እማ ምን አጠፋሁ ቆይ ምን በደልኩ💔💔💔

   <<ከናታን ላንቺ ለዉዷ ፍቅረኛዬ እወድሻለሁ ↔እጠብቅሻለሁ💔

      እማ አደራ ምንም ቢከፋሽ እራስሽን ጠብቂልኝ😢😂😢😂


    <<ጥቅምት 13/2016 ዓ.ም ማክሰኞ 1:30 pm >>

✔ይድረስ በጣም ለምወድሽ ለዉዷ ፍቅሰኛዬ ለs እማ እንዴት አመሸሽልኝ ዉዴ በጣም ናፍቀሽኛል በጣም እኔ አላቅም ግን በጣም ከምልሽ በላይ ከብዶኛል ከሄድሽኮ 2ወር ከ10 ቀን ሆነሽ እደውልልሀለሁ ብለሽ ጠፋሽ ምን ገጠመሽ እማ እንዴት ረሳሽኝ እማ ናፍቀሽኛል💔↔

. . . #ፍቅር_ማለት . . . 


     ❤️ፍፃሜው የሚያምር ቅርብ ማንነት ግልፅነት ሚያስተምር .. .. .. ርህራሄ እና ለሰው ማዘንን በልብ የሚያኖር💗 ከፈጣሪ የሚገኝ ፀጋ ነው።💖

 ❤️ፍቅር የሚመሠረተው . . . አንድ ነፍስ በሁለት. . . አካል ሲኖር💕 ነው፡፡

💓 ምንጊዜም በቂ ነገር አሟጠን የማናገኝበት ነገር ፍቅር ነው፡፡

💖 እውነተኛ ፍቅርን አግኝተህ ከተንከባከበው . . . እራስህን በምድር ላይ ካሉ ጥቂት እድለኞች💗 መሀል አንዱ ነህ፡፡

 ❤️ፍቅር የተለየ ቀን ልዩ ቦታና ድርጊት አይፈልግም . . .

✔እማ ልቤ ተሰበረ በጣም ከፋኝ አንቺን ማዉራት ፈለኩ አንቺን መስማት ስለፍቅራችን ማዉራት ናፈቀኝ ብቻ ግን በጣም ከበደኝ የምር ዉስጤ በጣም ተከፋቷል ነገሮች ኸነ እንዳጠበኳቸዉ ሆኑብኝ በጣም ከፋኝ ምን ላድርግ እማ ጨነቀኝ የምር በጣም በጣም ከፋኝ ምን ልሁን 

በጣም ከፋኝ ሁለነገሬ ነበርሽኮ ያላንቺ የዉስጤን የሚያዉቅልኝ የለም በህይወቴ እንዳንቺ ቦታ የሰጠሁት ሰዉ የለም ማርያምን ማንም የለም

✔የኔ ፍቅር በዚህ ዘመን ታማኝ መሆን በጣም ከባድ ነዉ ሰማዕትነት ነዉ ታማኝ መሆን እኔ ግን አንቺን የመሰለች ታማኝ ሴት አግኝቻለሁ እማ የኔ ታማኝ በጣም ነዉ የማምንሽ እኔ ላንቺ ታማኝ ነኝ ካንቺ ወዲያ አይደለም ልቤ ሊመኝ ይቅርና አይኔም አያይም እማ እወድሻለሁ ናላንቺ ሴት አላስብም ከነ ላንቺ ታማኝ ነኝ እጠብቅሻለሁ እታመንልሻለሁም የኔ ዉድ አንቺን ደሞ ከራሴ በላይ አምንሻለሁ አደራ እራስሽን ጠብቂልኝ 

✔የኔ ፍቅር እራስሽን ጠብቂልኝ ምንም ቢከፋሽ ምንም አይነት ከባድ ፈተና ቢገጥምሽም በክብርሽ እንዳትደራደሪ ክብርሽን ለማንም አሳልፈሽ እንዳትሰጪ↔አደራ እራስሽን ጠብቂልኝ እግዚአብሔር ይጠብቅሽ ናታን


      <<ጥቅምት 14/2016 ዓ.ም ረቡዕ 7:00 am >>

ይድረስ በጣም ለመሰወድሽና ለማፈቅርሽ ለዉዷ ፍቅረኛዬ ለs የኔ ዉድ እንዴት ዋልሽልኝ እማ በጣም ናፍቀሽኛል በጣም አረ አቃተኝ የኔ ፍቅር 

አልቻልኩም በጣም ከብዶኛል በጣም አንቺ ግን እንዴት አስቻለሽ እማ ግን ለምን??? ለምን ይሄን ያህል ጨከንሽብኝ ከዛሬ ነገ ትደዉያለሽ ብዬ ሁሌም በተስፋ እየጠበኩሽ ነዉ ሁሉተ ወር ከአስር ቀን ሆነሽ ከሄድሽ ግን ይሄን ያህል ጨካኝ አትመስሊኝም የምር ግን ይሄን ያህል ምን አጠፋሁ ምን በደልኩሽ ለምን ታፈቅሪኝ ነበር አይደል ታድያ ለምን ይሄን ያህል ጨከንሽብኝ ከፋኝ የምር ከፋኝ😢😢😢😢

Report Page