Report

Report


እንደርሳቸው ማብራሪያ፤ የወረዳ ማዕከል መሆን አለብን ብለው የጠየቁ የተወሰኑ ሰዎች አሉ፡፡ ወረዳ ሲቋቋም የወረዳ ማዕከል ይኖራል፡፡ በዚህ ሂደት ‹‹አይ እገሌ ሳይሆን እገሌ ነው መሆን ያለበት›› ብለው ያሰቡ ሰዎች ጥያቄውን አንስተዋል፡፡

የህዝቡ ውሳኔ የተወሰነው በወረዳ ደረጃ ነው ያሉት አቶ ጌታቸው ደንጎላት ከብዙ ቀበሌዎች አንዷ ናት፡፡

ቀበሌዎቹ በምክር ቤት ተሰብስበው ማዕከል የቱ ይሁን ብለው ይወስናሉ፡፡ ከመወሰኑ በፊት የእኛ ቀበሌ ነው ማዕከል መሆን ያለበት ያሉ ጥቂት ሰዎች ያደረጉት እንቅስቃሴና ያደረጓቸው በጣም ህገ ወጥና አሳፋሪ ነገሮችም ቢኖሩ ህዝብን ስለማይወክሉ ተነጋግሮ ይወሰናል ብለዋል፡፡

‹‹በአንድ አካባቢ በተፈጠረችና አንዲት ትንሽ መንገድ ላይ በሆነች አጋጣሚ ሰዎች እየተሰቃዩ ነው። የተዘጋ መንገድ መከፈት አለበት፣ የሚያስከፍተውም ሕዝብ ነው›› ያሉት አቶ ጌታቸው፤ እንደ አሰራር መንገድ ተዘግቷል ብለን የኃይል እርምጃ መውሰድ አንፈልግም ብለዋል፡፡

ጌታቸው አይወስንም፣ ደብረጽዮን አይወስንም ሌላ ሰውም አይወስንም፡፡ የወረዳ ማዕከል የት ይሆናል የሚለውን የሚወስነው የወረዳው ሕዝብ እንጂ ከመቀሌ የመጣ ሰው አይደለም፡፡

ጥቂት የሽፍታ እንቅስቃሴ ማድረግ የፈለጉ ሰዎች አሉ፡፡ ችግራቸውን የሚፈታላቸውም ሕዝቡ ነው፡፡ ከእዛ ውጭ የሚሆን ካለ የሚቀጥለው ሂደት ምን ይሆናል የሚለውን አብረን የምናየው ይሆናል ሲሉም አክለዋል፡፡

ሌሎችም ማዕከል መሆን አለብን የሚሉ አሉ፡፡ ስለዚህ ማዕከል የሚመረጠው ለአጠቃላይ ሕብረተሰቡ፣ ለእዛች ወረዳ፣ ለዞኑ፣ ለአካባቢው የትኛው ቢሆን ነው የሚመረጠው በሚል ይሆናል፡፡ በአንዲት መንደር ብቻዋን፣ ጥቂት ሰዎች ተሰብስበው ይህ ካልሆነ የሚሉበት ምክንያት ግን ተገቢ አይደለም፡፡

የህዝብ ውይይት ተደርጓል፡፡ የወረዳን ከተማ ማዕከል ለመጠየቅ ሕዝብ ነው የሚወስነው፡፡ እንጂ ክልልም አይወስንም፣ የዞን አስተዳደርም አይወስንም፡፡

የክልሉ ምክትል ፕሬዚደንት የሚሄዱት ሌላው ሰው የማይመልሰው እርሳቸው ብቻ የሚመልሱት ጉዳይ ሲኖር ብቻ ነው ሲሉም ጠቁመዋል፡፡ በክልል ደረጃ ወረዳ መሆን ያለበት ተብሎ የተወሰነ አለ፡፡ የወረዳ ማዕከል ካልሆንኩ የሚለው ደግሞ ሌላ ርዕስ ነው ብለዋል፡፡

በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ያነጋገርናቸው የአካባቢው ነዋሪዎች፤ ነገሩን ያበላሹት ዞንና ወረዳ ናቸው ፤ ክልሉ ከመወሰኑ በፊት ትክክለኛው የቱ ነው የሚለውን ለማወቅ ወርዶ ሕዝቡን መጠየቅና ማነጋገር ነበረበት ብለዋል፡፡

ጉዳዩ አቶ ጌታቸው እንዳሉት የጥቂቶች ሳይሆን የሕዝቡ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡ ትክክል የሚሆነው ሕብረተሰቡን ማነጋገር፣ በመቀጠልም ትክክለኛ ትግበራ ማድረግ ነው እንጂ ቢሮ ቁጭ ብለው የተወሰኑ ሰዎች ናቸው የጠየቁት ማለት ትክክል አይደለም፤ ወርደው ሕዝቡ የሚለውን ማዳመጥ አለባቸው ብለዋል፡፡

ይህ ሽፍትነት አይደለም ከስድስት ወራት በላይ ቢሮ ተመላልሰን መፍትሄ ባለማግኘታችን ያደረግነው ነው፡፡ መንግስት እንዲያነጋግረን ለማድረግ እንጂ ሌላ ነገር የለውም፣ ሽፍትነትም አይደለም፡፡ ማንንም አልዘረፍንም፣ የትኛውም አካል አልተመታም፣ ምንም አላደረግንም፡፡ ይህ ባደጉ አገራትም የሚደረግ ነው፡፡

ሕዝቡ ከተማ ላይ ተሰብስቦ እያለ ቤት ለቤት እየዞሩ እያባበሉ ናቸው። ይሁንና በዚህ መንገድቸግሩ አይፈታም ያሉት ነዋሪዎቹ፤ የክልል አመራሮች ባሉበት፤ ዞን፣ ወረዳውና ሕዝቡ አንድ ላይ ተነጋግረው ነው መፍትሄ የሚመጣው ሲሉም አክለዋል፡፡


Via EPA

@YeneTube @FikerAssefa

Report Page