Public

Public

From

ዛሬ ላይ ሆነን ስናይ፣ በኢትዮጵያ በነበረው የለውጥ እንቅስቃሴ የተሳተፉ አካላት ባራመዱት ዓለማ በሶስት ልንከፍላቸው እንገደዳለን፤ የየአካላቱን ጠርዘኞች በመተው ብሰይማቸው፣ ለ-renegotiation፣ real statehood እና the right to statehood የሚታገሉ ነበሩ፡፡ ከዚህ በመነሳት፣ ህወሃት መራሹን መንግስት በጋራ መታገላቸው ታክቲካዊ ህብረት እንኳ አይመስለኝም፤ ታክቲካዊ ነው ካልን መተባበሩ ቢያንስ የታሰበበት መሆኑን ያሳያልና፡፡ በግልፅ ከሚጋጩ ህልሞች የሚገኝ የለውጥ ውጤት የሚያራምዱ አካላት ወይ በደመ ነፍስ ወይ በግጥምጥሞሽ ካልሆነ በአስተውሎት ሆነው አይሻረኩም፡፡ ደግ!!

የህልሞቹ መጋጨት በለውጡ ሂደት ላይ ባሉን የተጣረሱ ግብረመልሶችም በግልፅ እየታየ ነው፡፡ መቼም በዚህ ሁኔታ አስማሚ መልስ መስጠት የሚቻልበትን ተዓምር አልጠቁምም፡፡ ልሂቃኑ የሚገፏቸው ጥያቄዎች መቃረናቸው ብቻ ባልከፋ፤ ጉዳዩን የበለጠ ከባድ የሚያደርገው፣ የየጥያቆዎቻቸው የመጨረሻ ግብ ምን እንደሆነ በግልፅ ሲያስቀምጡ አለመስተዋላቸው ነው፡፡ የሀብት ፈጣሪነት ባህል መጥፋት እና የህዝብ ቁጥር መጨመር ባለችው ውስን ሀብት ላይ የሚፈጥረውን የቁርቃሶ አዙሪት ለመስበሪያ መሳሪየነት፤ መፀዳጃ ቤቱን፣ የእንስሳቱን ማደሪያ እና የራሱን መኝታ በወጉ ያልለየው እና ከማንም በላይ ለፍቶ ከማንም በታች የሚያገኘውን ገበሬ/ አርቢ ለማልማት ነው የሚሉ ሀሳቦች ቢንሰራሸሩ ቢያንስ የሚጋሯቸው ግቦች በተገኙ ነበር፡፡ እነዚህ ሲነሱ አይስተዋልም፡፡ ደግ!!

ታዲያ ይህ ሁሉ መራኮት የየጥያቄዎቹ መልስ ለሚያስገኘው የልሂቃን ጥቅም ብቻ ነው?

የውርደቱን ምንጭ ለማን ተውነው ግን?

Report Page