Public

Public

From

ኋላ-ቀርነቱ ራሱን በራሱ የሚመግብ እዳ ነው። የኩራት ምንጭህ እንደሆነ ያሳስብሀል። እንደቡሉኮ ደርበሀው "comfort zone" ሆኖህ ይደላደልብሀል። ባይሆንማ ኖሮ፣ በዚህ ሁሉ የሚጋጩ ህልሞች መካከል ቢያንስ ቢያንስ እኛ በምንደረድራቸው ልዩነቶች ሳይገደብ ሁላችንንም እያዋረደ፣ እያሳመመ፣ እያደነቆረ፣ እየገደለ፣ እያገዳደለ፣ እየበተነን ያለው በኋላ ቀርነታችን የተነሳ እንዳለ እንኳ የዘነጋው ድህነት ነው።

ይህን ብንረዳ፣ የክልል፣ የነጻ መንግስት፣ የእውነተኛ ፌዴራሊዚም፣ የቀደመ ታላቅነት ተረክ አቀንቃኞች ሁሉ ቁጭ ብለን ለመነጋገር እና ገሚሱን ጉልበታችንን በዚህ የጋራ ነገርሳ ላይ ለማድረግ እንፈቅድ ነበር።

አንጠይቅ አልልም።

ክልል ሆንክ እንበል፣ ከዚያስ?! በአንድ ሄክታር ማሳ ላይ የስንዴን ምርት በስንት ኩንታል ልትጨምር ነው? ይህን ካሁኑ ግብህ ካላደረግህ፣ የኢትዮጵያን ገበሬ ነጥቆ ሲበላ እንደኖረው predatory state ልትሆን ነው ማለት ነው። ቀምቶ-በል። ምን አይነት ሀብት እንዴት ልትፈጥር ነው?
ከአንድ ብሄር የወጣ ጨቋኝ ገዥ መደብ የለም አስብለህ ኮራህ፣ ከዚያስ? በአስር አመት ስንት ሚሊዮን ገበሬ ከከብቶቹ ጋር ከመተኛት ልታወጣ ነው። የዚህን ህዝብ ክብር የሚታስመልሰው መብላት መተኛት መታከም ... ስታስችል እንጂ ውርደቱን በመፈክር በመጋረድ አይደለማ። የታለ ታዲያ በየእለቱ ሀሳቢህ ውስጥ የዚህ ፍንጭ?!

አዋራጁን የኢትዮጵያውያን ድህነት ያላገናዘበ፣ አገናዝቦም ለመደራደር ያልፈቀደ የፖለቲካ ሀሳብ አድሀሪ (obsolete) ነው። ድህነትን ቁንጣን በያዘው ጭንቅላት ቴክኒካሊ ሳይሆን የምር የሆነብህ ያክል ካሰብከው፣ የማትነጋገርበት ጥያቄ ያለ አይመስለኝም።

መናጢነቱን አምኖ የተቀበለ አካል፣ አንዲት ጥይት ለመተኮስ አይደፍርም። የድህነት ዘውድ የደፋ፣ በተኮሰ መጠን፣ ዘውዱን በራሱ ላይ ያጠብቃል።

የአንደ ገበሬ ጫማ ማድረግ ባለመቻል በእሾህ መወጋት፣ የአንድ ስራ አጥ አንድ ቀን ፆም ማደር የማያስጨንቀው ፖለቲከኛ፣ ከፈለገው ብሄር፣ ከፈለገው ሀይማኖት ይሁን፣ እሱ እዳ ነው።

Report Page