pr የቤ/ጉ/ክ/መ/ጤና ጥበቃ ቢሮ
Walia Tenderየጨረታ ማስታወቂያ
የቤ/ጉ/ክ/መ/ጤና ጥበቃ ቢሮ የጤናው ዘርፍ የትራንስፎርሜሽን እቅድ ለማሳካት የጤና ኤክስቴንሽን ባለሞያዎች እውቀትና ክህሎት ለማሻሻል ሲባል የሁለተኛ ትውልድ የገጠር ጤና ኤክስቴንሽን አተገባበር መመሪያ |seconde generation 18 Package and drug hand book Final second Generation implementation guideline በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከተጫራቾች ማሳተም ይፈልጋል ።
በዚሁ መሠረት በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
- በዘርፍ ፈቃድ ኖራቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ፈቃዳቸውን ዋናውን ፎቶ ኮፒ በማድረግ ማቅረብ የሚችሉ ፣
- የአቅራቢዎች ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፣
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /tin number/፣ቫት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ CPO 10,000.00 ማስያዝ የሚችል።
- የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሠነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ / ብር በመክፈል ከቤ/ጉ/ክ/መ/ጤና ጥበቃ ቢሮ ቁጥር 502 በመውሰድ መወዳደር ይችላሉ።
- የመወዳደሪያ ዋጋ መሞላት ያለበት በኢትዮጵያ ብር መሆን አለበት፣
- ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋተመስርቶ ዋጋማቅረብ አይቻልም፣
- ተጫራቾች አሸናፊ የሆኑባቸውን ህትመቶች ሙሉ በሙሉ በጨረታ ሠነዱ ላይ በተያዘው ስፔስፊኬሽን (specification) መሠረት ማቅረብ የሚችል ፣
- የጨረታው አሸናፊ የሆነው ድርጅት ዕቃውን በራሱ ወጪ ቤ/ጉ/ክ/መ/ጤናጥበቃቢሮድረስማምጣትይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ለ15 የስራ ቀናት የጨረታ ሠነድ በመግዛት በሰም በታሸገ ፖስታ ውስጥ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በ 16ኛው ቀን ከሰዓት በ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ስለሚከፈት ከቤጉ/ክ/መ/ጤና ጥበቃ ቢሮ ቁጥር 502 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት መሆኑን እናስታውቃለን። ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም የጨረታው ሠነድ አይስተጓጐልም።
- የጨረታው መዝጊያእናመክፈቻ ቀናት ቅዳሜናእሁድወይም በበዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀናት ይሆናል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስተጨማሪ ማብራሪያ፡-ካስፈለግዎ በስልክቁጥር 0577750839 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥት ጤና ጥበቃ ቢሮ
__________________
Posted:አዲስ ዘመን መስከረም 10፣2013
Deadline:በ16ኛው ቀን በ 8፡00
__________________
© walia tender