ot ዓባይ ኢንሹራንስ

ot ዓባይ ኢንሹራንስ


Walia Tender

ዓባይ ኢንሹራንስ አ.ማ.

የጥበቃ ሥራ አገልግሎት ለማግኘት የወጣ ጨረታ

የጨረታ ቁጥር ዓኢ/002/2013

ዓባይ ኢንሹራንስ አ.ማ. ለዋናዉ መ/ቤት ህንፃ እና በተለያዩ የትራፊክ አደጋ ምክንያት አደጋ ለደረሰባቸዉ ተሸከርካሪዎች ማቆያ ቦታ የጥበቃ አገልግሎት ለማግኘት በመስኩ የስራ ፈቃድ ያላቸዉን ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ አገልግሎት ለማግኘት ይፈልጋል::

በመሆኑም በዘርፉ ህጋዊ የሥራ ፈቃድ ያላችሁ ድርጅቶች በጨረታዉ እንድትሳተፉ እንጋብዛለን፡፡

ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸዉ ነገሮች

  1. በመስኩ የታደሰ ህጋዊ የሥራ ፈቃድ ያላቸው፣ በሚመለከተው መ/ቤት የተመዘገቡበት የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ ከፖሊስ የተሰጠ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ያላቸው እና በመስኩ ያላቸውን የስራ ልምድ ማስረጃ እንዲሁም ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ እና የግብር መለያ ቁጥርና ተያያዥ ሰነዶች ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  2.  ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ የዘመኑ የታደስ የንግድ ፈቃድ፤ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፤የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው:: እነዚህ ሰነዶች በቴክኒካል ኘሮፖዛል ፖስታ ውስጥ ታሽገው መቅረብ ይኖርባቸዋል::
  3.  ተጫራቾች ለጨረታው የተዘጋጀውን ሰነድ ከነመመሪያው የማይመለስ ብር 200 (መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከኩባንያው ዋና መ/ ቤት 4ኛ ፎቅ ከሚገኘው ሃብት አስተዳደር ቢሮ መውሰድ ይችላሉ::
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ይሆን ዘንድ የጨረታውን 2 በመቶ (2%) በባንክ ክፍያ ማዘዣ(ሲ.ፒ.ኦ) ወይም የባንክ ዋስትና ማረጋገጫ ደብዳቤ በቴክኒካል ኘሮፖዛል ፖስታ ውስጥ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል::
  5. ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ሃሳባቸውን ቴክኒካል ሰነድ ዋና እና ኮፒ እንዲሁም ፋይናንሻል ዋና እና ኮፒ በማዘጋጀት በግልፅ ከፋፍለው በተለያየ ፖስታ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
  6.  ጨረታው ከመስከረም 10 ቀን 2013 ዓ.ም እሰከ መስከረም 25 ቀን 2013 ከቀኑ 8፡00 ድረስ ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በእለቱ መስከረም 25 ቀን 2013 ከሰዓት 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻዉ በተገኙበት ይከፈታል:: ነገር ግን በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ለጥንቃቄ ሲባል ተጫራጮች በጨረታዉ ላይ ሳይገኙ ጨረታዉ ሊከፈት ይችላል።
  7. አሸናፊው ተጫራች ከኩባንያው ጋር የስራ አፈፃፀም ውል ይዋዋላል::
  8.  ኩባንያው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  9.  ለተጨማሪ ማብራርያ በስልክ ቁጥር 251-11-5-53 58 08 ወይም 011-6-72-50-09 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ::

ዓባይ ኢንሹራንስ አ.ማ.

ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 03 የቤት ቁጥር 377 አትላስ ሆቴል አካባቢ

ሀብት አስተዳደር መምሪያ 4ኛ ፎቅ 405 ቢሮ ቁጥር

ስልክ: 251-11-5-53-58-08 /251-6-72-50-09/

ፖ.ሳ.ቁ. 5879

 አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

__________________

Posted:ሪፖርተር መስከረም 10፣2013

Deadline:መስከረም 25 ቀን 2013

__________________
© walia tender


Report Page