Hello

Hello


የሰኔ 15ቱን ክስተት በተመለከተ አሁን ያለው የምርመራ ውጤት፦

-በድርጊቱ የሌላ ሶስተኛ ወገን እጅ ሳይኖርበት አይቀርም። በአንድ በኩል የትህነግ/ህውሓት እጅ እንዳለበት ጠቋሚ ምልክቶች እየታዩ ነው! የአማራ ክልል የደህንነት ሀላፊ አቶ የማነ ታደሰ (በተወሰነ በኩል የትግራይ የዘር ሀረግ አለው የሚል ነገርም ሰምቻለሁ ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ ባልሆንም) ድርጊቱ በተፈጸመበት እለት ለረዥም ሰአት በብ/ጄ አሳምነው ቢሮ ውስጥ እንደነበር አሁን በእስር ላይ የሚገኙ ሁለት ተጠርጣሪዎች ምስክርነት ሰጥተዋል። የማነ ታደሰ ለረዥም ግዜ የአማራ ክልል የደህንነት ሰራተኛ በነበረበት ሰአት ከጌታቸው አሰፋ ጋር ጥብቅ ግንኙነት ነበረው። የማነ እንደ ክልሉ የደህንነት ሀላፊነቱ ለነ አሳምነውና ለነ አምባቸው የተለያየ መረጃ እየሰጠ ነበር የሚል መላምት አለ። ለአብነት ያህል ከሰኔ 15ቱ ክስተት ሁለት ቀን ቀደም ብሎ በደመቀ መኮንን መሪነት በአዲስ አበባ የተደረገው ስብሰባ ላይ አምባቸው በመሃል ስልክ ተደወለልኝ ብሎ የወጣ ሲሆን ሲመለስ አሳምነው እዚህ ካለነው 3 ሰዎችና ሌሎች ተጨማሪ ሰዎችን ሊገለን እያሴረ እንደሆነ ከብሄራዊ ደህንነት መረጃ ደርሶኛል ብሎ ክስ አቅርቦ ነበር። በወቅቱ አሳምነው በዚህ ክስ እጅግ ሲበሳጭ ታይቷል። ይህን መረጃ አምባቸው ያገኘው ከብሄራዊ ደህንነት ሳይሆን በየማነ ታደሰ በኩል ነው የሚል ጥርጣሬ አለ። በሌላ በኩል ለአምባቸው ልትገደል ነው የሚል መረጃ ያገኘው ከብሄራዊ ደህንነት አካባቢ ከሆነ ለአሳምነውና ለአምባቸው ለየብቻቸው አንዱ አንዱን ሊገል እያሴረ ነው የሚል መረጃ የሰጠ ሌላ ተጠርጣሪ አካል አለ ማለት ነው። እየደረሱኝ ያሉ መረጃዎችን ነጠብጣብ ሳገናኛቸው የሚታየኝ ምስል የድርጊቱ ጠንሳሽ (master mind) በእነ አሳምነውና አምባቸው መካከል በስራ መካከል ልዩነት እንዳለ የተረዳና እነዚህን ሁለት ቡድኖች እርስበርስ እንዲገዳደሉ ማድረግ እችላለሁ ብሎ በተጠና መንገድ የሰራ ይመስለኛል። የመላምቴ መነሻ አሳምነው እሁድ የእስክንድር ስብሰባ በባህር ዳር እንደሚደረግ እያወቀ ለህልውናዬ አስጊ የሆነ ነገር አጋጥሞኛል ብሎ ካላሰበ በስተቀር ቅዳሜ ምሽት ያን አደረገ የተባለውን ድርጊት ሊፈጽም አይችልም የሚል ነው። ለአምባቸው እነ አሳምነው ሊገሉህ ነው ብሎ መረጃ የሰጠው አካል በተመሳሳይ መልኩ ለአሳምነውም እነ አምባቸው ሊገሉህ ነው የሚል መረጃ ሰጥቶት ሊሆን ይችላል የሚል ጥርጣሬ አለኝ። ከአብይ አህመድ ጋር ባለው የቀረበ ግንኙነት ምክንያት የትግራይን ጥቅም አሳልፈህ ሰጥተሃል በሚል ከነ ጌታቸው አሰፋና ትህነግ ጋር ጥሩ ያልሆነ ግንኙነት የነበረው የጀኔራል ሰአረ በዛው እለት መገደል የድርጊቱ አቀናባሪ ዋና ተጠርጣሪነት ወደ ትህነግ እንዲያዘነብል ያደርገዋል። ከትህነግ ውጭም ሌላ ፌዴራል መንግስቱ አካባቢ ያለ አካልም ድርጊቱን አቀነባብሮት ሊሆን ይችላል የሚለው ጥርጣሬም እንዳለ ሁኖ። በሌላ በኩል እነ አምባቸው ወደ ሰፈርተኝነት አደረጃጀት ገብተው አሳምነውን ከቦታው አንስተው በአለበል ሊተኩት አስበው ስለነበር በዚህም አሳምነው ትእግስቱ እየተሟጠጠ ነበር የሚል ነገርም ሰምቻለሁ። በእኔ እምነት እነ አምባቸው የሚታሙበት የሰፈርተኝነት አሰራር አሳምነውን አደረገ ለተባለው ድርጊት ያበቃዋል የሚል እምነት የለኝም። በርግጥ አባባሽ ተደራቢ ምክንያት ሊሆን ይችል ይሆናል።

በወንጀል ምርመራ ሂደት አንድ መርማሪ ከወንጀሉ ጀርባ ያሉ አካላትን ማንነት ለማወቅ ማድረግ ያለበት ቀዳሚው ተግባር ለምን ድርጊቱ ተፈፀመ? why? የሚለውን ጥያቄ መመለስ ነው። የድርጊቱን motive ማወቅ የአድራጊዎችን ማንነት በቀላሉ ለማወቅ ይረዳል።


ወደ ምርመራው ሂደት ስመለስ ጀኔራል ተፈራ ላይ ሀላፊነቱን በአግባቡ አልተወጣም ከሚል ውጭ ከድርጊቱ ጋር በተያያዘ ይህ ነው የሚባል ተጨባጭ ማስረጃ እስካሁን አልተገኘበትም።

ኮሎኔል አለበል ከህገ ወጥ መሳሪያና ገንዘብ ጋር የተገናኙ ነገሮች እንደቀረቡበት ሰምቻለሁ።ከሰሞኑ የሚለቀቁ የልዩ ሀይል አባላት ሊኖሩ ይችላሉ።

በእኔ እምነት ጀኔራል ተፈራ ሀላፊነትን በአግባቡ ካለመወጣት ከሚለው ውጭ ሌላ ክስ የሚቀርብበት አይመስለኝም። ስለዚህ በቅርቡ የሚፈታ ይመስለኛል

Report Page