har ብርሃን ባንክ
Walia Tenderብርሃን ባንክ አማ ከባለእዳዎቹ ላይ ለሚፈልገው ገንዘብ በዋስትና የያዛቸውን እና ከዚህ በታች የተመለከቱትን ንብረትቶች በአዋጅ ቁጥር 97/1990 እና በተሻሻለው 216/92 ለባንኮች በተሰጠው ስልጣን መሠረት ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል :: ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች በመገንዘብ ማክበር ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋውን የ1/4 (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ(ሲፒኦ) በብርሃን ባንክ አማ ስም ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ::
- የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን እንዳሸነፈ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ ንብረቱን መረከብ አለበት:: በእነዚህ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል:: በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ይመለስላቸዋል::
- የፋብሪካው ጨረታ ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ ይከናወናል::
- የጨረታ አሸናፊው በሚገዛው ንብረት ላይ የሚፈለግ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ግብር፣ ታክስ፣ የስም ማዘዋወሪያ ክፍያዎች እና የሊዝ ክፍያዎች ይመለከተዋል::
- መያዣ ሰጪዎች ሐራጁ በሚከናወንበት ቦታ ቀንና ሰዓት መገኘት ይችላሉ:: ባይገኙ ግን ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል::
- ለጨረታ የቀረቡትን ንብረቶች በስራ ሰዓት ኘሮግራም አስይዞ ለመጐብኘት ይቻላል::
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው::
ፋብሪካ
ተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥሮች 0116631225 እና 0116185683 በመደወል መጠየቅ ይቻላል::
__________________
Posted:ሪፖርተር መስከረም 24፣ 2013
Deadline:ጥቅምት25 ቀን 2013
__________________
© walia tender