Gg

Gg

® @Tewahedo12

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን †


† ስንክሳር ዘወርኀ ኅዳር ፭ †


=>አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ኅዳር አምስት በዚች ቀን ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዕንጨት መስቀል ላይ ተሰቅሎ ሳለ ጐኑን የወጋ የቅዱስ ለንጊኖስ ራሱ የታየችበት ነው። ይህም ቅዱስ በጌታችን ከአመነ በኋላ በቀጰዶቅያ አገር ወንጌልን የሚሰብክ ሆነ ከሀድያን አይሁድም በላዩ ተነሡበት በመኳንንት ዘንድ በሐሰት ወንጅለው በቀጰዶቅያ አገር ራሱን አስቆረጡት ራሱንም ብቻውን ወደ ኢየሩሳሌም ወሰዱዋት። በኢየሩሳሌም የሚኖሩም አይሁድ በአዩዋት ጊዜ እጅግ ደስ አላቸው ከዚህም በኋላ ከኢየሩሳሌም ከተማ ውጭ በአንድ ኮረብታ ላይ ቀበሩዋት።


ከብዙ ቀኖችም በኋላ እንዲህ ሆነ በቅዱስ ለንጊኖስ ስብከት ያመነች አንዲት ሴት በቀጰዶቅያ አገር ነበረች ራሱን ከቆረጡበት ጊዜ ጀምራ በተቆረጠበት ቦታ በመቆም ስለርሱ ታለቅስ ነበር ክብር ይግባውና በእግዚአብሔርም ፈቃድ የዚያች ሴት ዐይኖቿ ታወሩ።


ከዚህም በኋላ ምናልባት ዐይኖቿ ቢገለጡላት በማሰብ ከከበሩ ቦታዎችና ክብር ይግባውና ከጌታችን መቃብር ለመባረክና ለመለመን ተነሥታ ልጅዋን ይዛ ወደ ኢየሩሳሌም ሔደች። ወደ ኢየሩሳሌምም በደረሰች ጊዜ በዚያ ልጅዋ ሞተ ኀዘንም ተጨመረባት ወደ አገርዋም መርቶ የሚያደርሳት አጣች ስለዚህም የመረረ ልቅሶን አለቀሰች ከኀዘኗም ብዛት የተነሣ ተኛች።


ከዚህም በኋላ ቅዱስ ለንጊኖስን ከሞተው ልጅዋ ጋር በሕልሟ አየችው። ዕገሌ ከሚባልም ቦታ ሒደሽ ራሴን ከዚያ ውሰጂ አላት። ከእንቅልፍዋም በነቃች ጊዜ ስለዚያ ቦታ ጠየቀች ሰዎችም ወደርሱ አደረሱዋት። ያንንም ቦታ በቆፈረች ጊዜ መዓዛው እጅግ ጣፋጭ የሆነ የሽቱ መዓዛ ወጣ። ራሱ ወደአለችበትም ስትደርስ ታላቅ ብርሃን ተገለጠላትና ዐይኖቿም በዚያን ጊዜ ተገለጡላት እግዚአብሔርንም አመሰገነችው።


ከዚህም በኋላ ከልጅዋ ሥጋ ጋር የቅዱስ ለንጊኖስን ራስ ወደ አገርዋ ወሰደቻት። በታላቅ ክብርም በአማረ ቦታ አኖረቻት። 


ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።


            ፨፨፨

   አርኬ

  ሰላም ለለንጊኖስ ዘተከለለ በሮም። ወተቀብረ ውስተ ወግር ዘኢየሩሳሌም። እንዘ ምስሌሁ ኅቡረ ወልዳ ንውም። ከመ ተናገራ ለብእሲት በሕልም። ምስለ ጼና ዕፍረት ርእሱ አስተርአየት ዮም።

   ፨፨፨


=>በዚችም ቀን የሰማዕት ጢሞቴዎስ መታሰቢያ የሠራዊት አለቃ ቴዎድሮስም ከሀገረ ሰጥብ ወደ ሀገረ አስዩጥ ሥጋው የፈለሰበት ቤተ ክርስቲያኑም የከበረችበት ነው። ዳግመኛም ወደ ብሔረ ሕያዋን የገባ የአባ ዮሐኒ መታሰቢያው ነው።


ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።


   ፨፨፨

   አርኬ

  ሰላም ለከ ጢሞቴዎስ ቡሩክ። ሰማዕተ አምላክ። ብእሲ ሰማያዊ ወምድራዊ መልአክ። ኅብአኒ በክነፊከ በዕለተ ምንዳቤ ወሀውክ። እምነ ልሳን ምዑክ ወእምዐይን ድሩክ።

  ሰላም ለፍልስተ ሥጋከ ቴዎድሮስ ማር። አመ ኃሙሱ ለወርኀ ኅዳር። ሶበ በማዕበላ ፈቀደት አጥፍኦታ ለምድር። ሰሚዓ ትእዛዘከ ፈለሰት ባሕር። ቃለ እግዚኡ ከመ ይሰምዕ ገብር።

  ሰላም እብል ለዘኮነ ሱቱፈ። ምስለ እለ ገብሩ ሰብእ ብሔረ ሕያዋን ምዕራፈ። እምሥርዓተ መላእክት ዮሐኒ ምንተኒ ኢያትረፈ። ከመ ሕይወቶሙ ሕይወተ ተጸገወ ዘልፈ። ወከመ ክንፎሙ አብቈለ አከናፈ።

   ፨፨፨


 =>ኅዳር 5 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=

1.ታላቁ ቅዱስ ዮሐኒ (ዘትግራይ)

2.አባ አሞኒ ዘናሕሶ

3.ቅዱስ ለንጊኖስ ሰማዕት

4.ቅዱስ ቴዎድሮስ ሊቀ ሠራዊት

5.ቅዱስ ጢሞቴዎስ ሰማዕት


=>ወርሐዊ በዓላት

1.ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት

2.ቅዱስ ዻውሎስ ብርሃነ ዓለም

3.ቅድስት አውጋንያ (ሰማዕትና ጻድቅ)

4.አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጻድቅ


=>+"+ ወደ ጌታ ኢየሱስ በመጡ ጊዜ ግን እርሱ ፈጽሞ እንደ ሞተ አይተው ጭኑን አልሰበሩም ፤ ነገር ግን ከጭፍሮች አንዱ ጐኑን በጦር ወጋው ፤ ወዲያውም ደምና ውሃ ወጣ። ያየውም መስክሯል ፤ ምስክሩም እውነት ነው ፤ እናንተም ደግሞ ታምኑ ዘንድ እርሱ እውነት እንዲናገር ያውቃል። ይህ የሆነ:- "ከእርሱ አጥንት አይሰበርም" የሚል የመጽሐፍ ቃል እንዲፈጸም ነው። ደግሞም ሌላው መጽሐፍ:- "የወጉትን ያዩታል" ይላል:: +"+ (ዮሐ. 19፥33-37)


                   ፨፨፨፨

ዘአቅረብኩ ማኅሌተ አዘኪርየ አእላፈ። እምእለ ተጸምዱከ ዘልፈ። ለለአነብብ ተወከፍ ዘንዴትየ መጽሐፈ። እንተ ረሰይከ እግዚኦ ጸሪቀ መበለት ውኩፈ። እምእለ አብኡ ብዑላን ዘተርፈ።

ነቢያት ቅዱሳን ወሐዋርያት ሰባኪያን። ሰማዕት ወጻድቃን ወመላእክት ትጉሃን። ደናግል ዓዲ ወመነኰሳት ኄራን። ባርኩ ባርኮ ጉባኤ ዛቲ መካን። እስከ አረጋዊ ልሒቅ ወንኡስ ሕፃን።

ለዘጸሐፎ በክርታስ ወለዘአጽሐፎ እንዘ ይደርስ። ለዘአንበቦ ወለዘተርጐሞ በልሳን ሐዲስ። ወለዘሰምዐ ቃሎ በዕዝነ መንፈስ። በጸሎተ እሙ ማርያም ዐራቂተ ኵሉ እምባእስ። ኅቡረ ይምሐረነ ኢየሱስ ክርስቶስ።

                   ፨፨፨፨


 ( ጌታ ሆይ ከብልጽግናቸው ብዛት የተነሳ ብዙ መባ ካገቡት ይልቅ የደሀዪቱን አነስተኛ መባ እንደተቀበልህ ለሁል ጊዜ የሚያገለግሉህ አእላፍ መላእክትን እያሳሰብሁ በችግሬ ጊዜ የማቀርብልህን ምስጋና ተቀበል።

እናንተም ቅዱሳን ነቢያት የወንጌል ሰባኪያን ሐዋርያት ሰማዕታትና ጻድቃን ትጉሃን መላእክት ፍጹማን ደናግል እንዲሁም ደጋጎች መነኰሳት ሆይ ልጅ አዋቂ ሳይለይ የምንሰበሰብበትን የጉባኤ ቦታ ባርኩ።

ይህን መጽሐፍ ወረቀት አዘጋጅቶ ብራና ደምጦ የጻፈውና ያጻፈውም ከግዕዝ ወደ አማርኛ የተረጐመውን ቃለ ንባቡን በእርጋታ መንፈስ እና በተመስጦ ሕሊና ያዳመጠ በደለኛን ሁሉ የምታስምር የጌታ እናቱ በማርያም ጸሎት ኢየሱስ ክርስቶስ በአንድነት ይማረን።)


 ወስብሐት ለእግዚአብሔር 

 ወለወላዲቱ ድንግል

 ወለመስቀሉ ክቡር አሜን።

Report Page