GE

GE

Greatful-Ethiopia

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከመደመር መፅሐፍ ሽያጭ የተሰበሰበውን ከ110 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ለትምህርት ቤት ማሰሪያ እንዲውል አበረከቱ።


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከመደመር መፅሐፍ ሽያጭ የተሰበሰበውን ከ110 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ለትምህርት ቤት ማሰሪያ ይሆን ዘንድ ለቀዳማዊት እመቤት ፅ/ቤት አስረክበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመደመር መፅሐፍን ገቢ በመላው አገሪቱ ለትምህርት ቤቶች ማሰሪያ እንደሚውል ቃል በገቡት መሰረት ነው እስካሁን ከመፅሀፉ ሽያጭ የተሰበሰበውን ከ110 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ለቀዳማዊት እመቤት ፅ/ቤት ዛሬ ያስረከቡት።

በየክልሎቹ መደመር መፅሐፍ ተሸጦ የተሰበሰበው ገንዘብም ተመልሶ ለየክልሎቹ ትምህርት ቤት ግንባታ የሚውል እንደሆነም ተገልጿል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመደመር መፅሐፍ የኢትዮጵያን መወቅራዊም ሆነ ሰው ሰራሽ ሳንካዎችን በመፍታት ሀገሪቱን ወደ ብልፅግና ለመውሰድ ያለመ በመሆኑ በአገሪቱ ያለውን የትምህርት ቤት ችግር ለመፍታት አስተዋፅኦ በማድረጋቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል።

የተገኘው ገንዘብ የቀዳማዊት እመቤት ፅ/ቤት ቀደም ሲል በሁሉም ክልሎች ከእርዳታ ሰጪ አካላት ጋር በመተባበር እያስገነቧቸው ካሉ 20 ትምህርት ላይ ተጨማሪ ትምህርት ቤቶችን ለማስገንባት እንደሚያስችልም ተገልጿል።

የቀዳማዊት እመቤት ፅ/ቤት እያስገነባቸው ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ሰባቱ ተጠናቀው የተመረቁ ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ ግንባታቸው ከ90 በመቶ በላይ መድረሱም ነው የተገለፀው። 


ምንጭ ©EBC በአስማማው አየነው

Report Page