GE

GE

Greatful-Ethiopia

ወይዘሮ ኬሪያ ከፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤነታቸው መልቀቃቸውን ገለፁ

የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩት ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም በፈቃዳቸው ስልጣን መልቀቃቸውን ገለፁ፡፡

ወይዘሮ ኬሪያ በመቐለ ለትግራይ ቴሌቪዥን በሰጡት መግለጫ ስልጣናቸውን መልቀቃቸውን አስታውቀዋል፡፡

ከዚህ ቀደም የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤዎች ሀላፊነታቸውን በመልቀቅ ለተተኪው አፈጉባኤ ሲያስረክቡ የቆዩት መልቀቂያቸውን ለምክር ቤቱ በማቅረብ እንደነበር ይታወቃል፡፡ 

ወይዘሮ ኬሪያ ሚያዚያ ወር 2010 ዓመተ ምህረት ላይ ነበር የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ ሆነው የተመረጡት፡፡

ምክር ቤቱ 5ኛ የፓርላማ ዘመን 5ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ 2ኛ መደበኛ ስብሰባውን የፊታችን ረቡዕ እና ሀሙስ ለማካሄድ አባላቱን ጠርቷል፡፡


የፌደሬሽን ምክር ቤት...

ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም በጠሩት የምክር ቤቱ መደበኛ ሰብሰባ ዋዜማ የመልቀቂያ ውሳኔ መስጠታቸው ተገቢነት የሌለውና የብሔር ብሔረሰቦችን ሃላፊነትን ከግምት ያላስገባ መሆኑን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አስታወቀ። 

አፈ-ጉባዔዋ ዛሬ በመገናኛ ብዙሃን ልዩነታቸውን ቢናገሩም ምክር ቤቱ ምንም አይነት የጽሁፍም ሆነ የሃሳብ ልዩነት እንዳልነበራቸው 

ገልጿል።

ጉባዔ ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም ከሃላፊነት መልቀቃቸውን ይፋ ማድረጋቸውን ተከትሎ የምክር ቤቱ ምክትል አፈ-ጉባኤን ጨምሮ የምክር ቤቱ የስራ ሃላፊዎች በጉዳዩ ላይ ከኢዜአ ጋር ቆይታ አድርገዋል።

ምክትል አፈ ጉባኤው አቶ መሃመድ ረሽድ ሀጂ እንዳሉት አንድ የምክር ቤት አባል መልቀቂያ ሲያስገባ የራሱ የሆነ ደንብና ስርዓት ቢኖረውም የአፈ-ጉባዔዋ ውሳኔ ግን ከዚህ ያፈነገጠ እንደሆነ ገልጸዋል። 

እስካለፈው ሐሙስ ድረስ የምክር ቤቱን መደበኛ ስብሰባ ተገኝተዋል፤ በመጪው ሰኔ 3 ቀን 2012 ዓም ደግሞ ራሳቸው በደብዴቤ ስብሰባ መጥራታቸውንና በቀረቡ አጃንዳዎች ላይ ምንም ልዩነት እንዳልነበራቸው ገልጸዋል።

አፈጉባኤዋ ጥያቄዎቸ ቢኖረቸው እንኳን ለምክር ቤቱ ማቅረብ እንደነበረባቸው ገልጸው፤ የምክር ቤቱን መደበኛ ስብሰባ ለማድረግ አስተባባሪ ኮሚቴው ሳያውቅ በሚዲያ መናገራቸው ትክክለኛ ውሳኔ አይደለም ብለዋል።

በአፈጉባኤዋ መልቀቅም በቀጣይ በምክር ቤቱ አጀንዳዎችና መደበኛ ስራውን የሚያስተጓጉል ሂደት እንደሌለ ገልጸው ሁሉም ጉዳዮች በቂ ቅድመ ዝግጅት ስለተደረገባቸው ይካሄዳሉ ብለዋል።

ወይዘሮ ኬሪያ ራሳቸው በጠሩት ስብሰባ ዋዜማ መልቀቃቸው፣ የፓርቲ ወገንተኝነታቸውን ከብሄር ብሄረሰብ ተወካይነታቸውን ያሳነሰ ተገቢነት የሌለው ውሳኔ ነው ሲሉም ተናግረዋል።


@GreatfulEthiopia

"ትክክለኛ የመረጃ ምንጭ"

Report Page