GE

GE

Greatful-Ethiopia

◉ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሰጡት ማብራሪያ፦

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የኮቪድ ጫናን ተቋቁሞ በ6% እንደሚያድግ የገለጹ ሲሆን ይህንንም IMF ኢትዮጵያ በዚህ አመት 3% አወንታዊ እድገት እንደሚኖራት አምኗል ሲሉ ገልጸዋል፡፡ ለዚህም ምክንያት የሆኑ ሦስት ምክንያቶችን ጠቅሰዋል እነዚህም፡-

• ባለፉት 10 ወራት ንግድ ባንክ በአስቀማጭ (Saving ) የተሰበሰበ 87% ቢሊዮን ብር ማስቀመጥ ተችሏል፡፡ በዚህም 17.4% እድገት ተመዝግቧል፡፡

• 138 ቢሊዮን ብር የተመለሰ ብድር ይህም ካለፈው ዓመት 14% እድገት አሳይቷል፡፡

• ከባንኮች የተሰጠ ብድር 221 ቢሊዮን ብድር ተሰጥቷል ይህም 24% እድገት አሳይቷል

• የተበላሸ ብድር በግል ባንኮች 3.4% ሲሆን ካለፈው ዓመት 4% ቅናሽ አሳይቷል፡፡ በንግድ ባንክ 2% የተበላሸ ብድር የተመዘገበ ሲሆን 43% የተበላሸ በድር ተስተካክሏል፡፡ ከፍተኛው የተበላሸ ብድር የነበረው ልማት ባንክ 34% የነበረ ሲሆን ባለፉት አስር ወራት 13% ቅናስፀሽ አሳይቷል፡፡


ባለፉት አስር ወራት፦

•  48 ቢሊዮን ብር ለባንኮች ፈሰስ ተደርጓል፡፡

• 78 ቢሊዮን ብር እዳ ተሰርዟል፡

• ኤክስፓርት 13% አድጓል፡፡

•  የአበባ ኤክስፓርት 440 ሚሊዮን ዶላር ገቢ በማስገኘት 84% እድገት አሳይቷል፡፡


በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው ሴክተሮች አንዱ ቱሪዝምና የአገልግሎት ዘርፉ ሰሆን ይኸው ዘርፍ ግን ከኮቪድ በኀላ የምትጎበኝ ሀገር መሆኗ በመገለጹ ዝግጅቶቻችንን ማጠንከር ያስፈልጋል ሲሉ ገልጸዋል፡፡


◉ ምርጫን አስመልክቶ!

•  ብልጽግና ኮሮና ምርጫን ለማካሄድ ቁርጠኛ አቋም ነበረው ምርጫም የሚያስፈራው ፓርቲ አይደለም ሲሉ ምርጫን አስመልክቶ ለቀረበላቸው ጥያቄ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ በዚህ አቋማቸውም ከምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ጋርም እስከ አለመግባባት የደረሰ ጠንከር ያለ ክርክር ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡ 

•  ሆኖም ምርጫውን በሚመለከት የተጠናው ጥናት ኃሳባቸውን እንዳስቀየራቸው ጠቅሰው ጠ/ሚኒስትሩ ምርጫ ቦርድ የያዘውን ጠንከር ያለ አቋም አድንቀዋል፡፡ ወ/ት ብርትኳን ሚዴቅሳንም ለማንም ጫና እና ቁጣ ሸብረክ የማይሉ ሴት ሲሉ አሞካሽተዋል፡፡

•  ምርጫና ችግኝ መትከልን በማነጻጸር ለሚቀርቡ ጥያቄዎች ምላሽ ሲሰጡም ምርጫን ማካሄድ የማይቻለው ምርጫውን እንዲያስፈጽም ስልጣን የተሰጠው አካል ምርጫውን ለማካሄድ የዝግጅት ጊዜ ፈልጋለው ሥላለ ነው፡፡ ችግኝ መትከል ስንፈልግ ጠዋት ስንፈልግ ማታ የምንተክለው ነው ሲሉ በንጽጽር መልሰዋል፡፡


◉ እንቦጭን በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲያብራሩ አረሙን ለማጥፋት ከአጭር ጊዜ መፍትሄ ይልቅ በረጅም ጊዜ እና በዘላቂ መፍትሄ ላይ ማተኮር እንደሚገባ ገልፀዋል።

• የፌደራል መንግስት እንቦጭን ለመከላከል የሚረዳ፣ ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የሚጠይቅ የተሻለ ማሽን ከአውሮፓ ለመግዛት በመደራደር ላይ መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታውቀዋል።

• በማሽን እና በሰው ሀይል የሚደረግ እንቦጭን የመከላከል ሂደት ጊዜያዊ መፍትሄ ብቻ የሚያመጣ በመሆኑ በዘላቂነት የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ላይ በማተኮር መፍትሄ ማምጣት ይቻላል።

• ዘንድሮ የሚተከሉት 5 ቢሊዮን ችግኞች እንቦጭን በዘላቂነት ለማጥፋት ዋነኛ መፍትሄ መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

• የአጭር ጊዜ የመከላከያ መንገዱ በሰው ሀይል እና በማሽን በመታገዝ ለማሶገድ መሞከር ነው፤ ነገር ግን ይህኛው መንገድ ዘላቂ መፍትሄ አያመጣም። የረጅም ጊዜ የመከላከያ መንገዱ ደግሞ የአካባቢ ጥበቃ ስራ መስራት ነው። 

•  የጉና ተራራ ጣናን እና ተከዜን የሚመግቡ ወንዞች መነሻ ነው፤ በተራራው ዙሪያ የሚገኙ አርሶ አደሮች፣ ተራራው የነበረውን ደን እያጣ በመምጣቱ ምክንያት በተለይ በፎገራ አካባቢ ያሉ አርሶ አደሮች በጎርፍ ይጠቃሉ፣ ለም መሬታቸው እና የተጠቀሙት ማዳበሪያ ታጥቦ ተወስዶ ለጣና ሀይቅ እንቦጭ ምግብ ይሆናል።

• የክልሉ መንግስት ችግሩን አስመልክቶ በማሽኖች እና በሰው ሀይል እንቦጭን ለመከላከል ከሚያደርገው ጥረት ባሻገር በጉዳዩ ላይ እየመከረም ይገኛል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

ምንጭ ፦ #ETV

@GREATFULETHIOPIA

"ትክክለኛ የመረጃ ምንጭ"

Report Page