GE

GE

Greatful-Ethiopia

ጠ/ሚ ዐቢይ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ነው!

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአባላቱ በተነሱላቸው ሃገራዊና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ነው ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ያለው፦

ከሃገራዊ ለውጡ፣ በድንበር አካባቢ የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል እየተሰሩ ባሉ ስራዎች ዙሪያ፣ ከሃገራዊ ምርጫና ተያያዥ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ እንዲሁም ከግብርና እና ከግብአት አቅርቦት ጋር የተያያዙ ጥያቄዎች ተነስተዋል።


ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኮሮና ወረርሽኝን አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ፡-

•የኮሮና ወረርሽኝ በዓለም ብቻ ሳይሆን በአፍሪካም በከፍተኛ ፍጥነት እየተዛመተ በርካቶችን እየያዘ፣ እየገደለም ይገኛል።

•ወረርሽኙ በዓለማችን ከ7 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን የያዘ ሲሆን ከ400 ሺህ በላይ የሚሆኑትንም ሕይወት አሳጥቷል።

•በምስራቅ አፍሪካ እና በአገራችንም ከሌላው አንፃር ቁጥሩ ያነሰ ቢመስልም ከለት ወደለት ወረርሽኙ እየጨመረ ይገኛል።

•በአገራችን ከሌላ አገራት አንፃር ሰፋ ያለ የሕዝብ ቁጥር ቢኖርም በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር ግን ከሌሎች አገራት ሲነፃፀር ዝቅተኛ ይመስላል። 

•ወረርሽኙ በአገራችን 2020 ሰዎችን የያዘ ሲሆን የ27 ሰዎችን ህይወትም ቀጥፏል፤ በወርሽኙ በአዲስ አበባ በስፋት የተሰራጨ ሲሆን በክልሎችም ዳር እስከ ዳር እየተስፋፋ ይገኛል።

•ወረርሽኙ ያደጉ የዓለም አገራትንም ጭምር በሰብአዊ ቀውስ፣ በኢኮኖሚ እና በሌሎች ዘርፎችም ክፉኛ የፈተነ በሽታነው።

•በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት 1.6 ሚሊዮን ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ተፈናቅለዋል፤ ከ60 ሚሊዮን ያላነሰ ሕዝብ ለድህነት ተጋልጧል።


የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በወቅታዊ፣ አገራዊ ጉዳዮች ላይ የተለያዩ ጥያቄዎች እያነሱ ነው። 


•በድንበር አካባቢ የኮሮና ወረርሽኝን ለመቆጣጠር ምን ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል?

•አገራዊ ለውጡ፣ እንደ ሁለተኛ ዜጎች ይታዩ በነበሩ ክልሎች በምን ደረጃ ላይ ይገኛል?

•በግብርና ላይ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት፣ አርሶአደሩ ያሉበትን የምርት ማሳደጊያ ግብአት ችግሮች ለመፍታት ምን ምን ስራዎች እየተሰሩ ነው?

•ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት ሲደረግ ቢቆይም ለማካሄድ አለመቻሉ ይታወቃል፤ የተለያዩ ተቃዋሚ ፓርቲዎችም ኢ-ሕገመንግስታዊ አቅጣጫዎችን እንደሚከተሉ በይፋ እያስታወቁ ነው፤ ይህን አስመልክቶ መንግስት ምን አቋም ይዞ እየሰራ ይገኛል?

•በክልሎች ለኮሮና የምርመራ እና ለይቶ ማቆያዎች እጥረት ይታያል፤ ለዚህም መንግስት ማብራሪያ ቢሰጥ 

የሚሉ ጥያቄዎችን አንስተው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ምላሽ መስጠት ጀምረዋል።


@GreatfulEthiopia

"ትክክለኛ የመረጃ ምንጭ"

Report Page