GE

GE


የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የሕዳሴ ግድብ የውኃ ሙሌት ሥራ እንዲፋጠን አሳሰበ!

ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ከሕዝብ የተሰበሰበው ገንዘብ 13 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ ደርሷል፡፡ አሁንም ሕዝቡ እያደገ ያለውን ተሳትፎ እንዲቀጥል የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ብሔራዊ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ጠይቋል። 

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ከዚህ ቀደም በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ውይይት አድርጎ ነበር፤ ዛሬ ደግሞ ምክር ቤቱ የአቋም መግለጫ አውጥቷል፡፡ 

በመግለጫውም ኢትዮጵያ ተፈጥሯዊ በውኃዋ የመጠቀም መብት ሰላላት በዚህ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ እንደማይደራደር አስታውቋል፡፡ 

ከምንጊዜውም በላይ የቴክኒክ ጉዳዩን በማፋጠን የውኃ ሙሌት እንዲፋጠን ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣም ጥሪ አቅርበዋል። የፖለቲካ ፓርቲዎች ለግድቡ መጠናቀቅ በአንድነት ድጋፍ እንደሚያደርጉም ተመላክቷል፡፡

የአፍሪካ ጉዳይ በአፍሪካውያን መፈታት ስላለበት ግብፅም ትሁን ሱዳን ለማንኛውም ጥያቄያቸው ኢትዮጵያን በቅድሚያ ማነጋገር ከዚያ ሲያልፍም የአፍሪካ ኅብረትን እንደ አማራጭ መወሰድ እንዳለባቸው የጋራ ምክር ቤቱ አስታውቋል፡፡ 

ግንቦት19/2012ዓ.ም በነበረው ውይይት የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ አንድ ሚሊዮን 485 ሺህ ብር በቦንድ ግዥና በስጦታ ማበርከቱ ይታወሳል፡፡


@GreatfulEthiopia

  "ትክክለኛ የመረጃ ምንጭ"

Report Page