Fg

Fg

KIDUS YEMIRU & GOITOM HAILE


''አዎ እኔ እግር ኳስ ተጫዋች ነኝ ለዛውም ጥቁር እግር ከኳስ ተጫዋች'' ካሊዱ ኩሊባሊ!!!!!


አንዳንዴ ሰዎች በቃለ-መጠይቅ ወቅት ይሄን ጥያቄ ሲጠይቁኝ ለመመለስ ብዙ ጊዜ ይከብደኛል፡፡ ምን ይሉኛል ኩሊ ደጋፊዎች በሜዳ ውስጥ የዘረኝነት ጥቃት ሲያደርሱብክ ምን ይሰማካል? ይረብሽካል? ምንስ መደረግ አለበት?


እንደኔ ሰዎች እኔ ባለፈኩበት መንገድ ካላለፉ ሊረዱት አይችሉም፡፡ በጣም የሚያስጠላ ነገር ነው ከዛም ባለፈ ደግሞ ለማውራትም የሚከብድ ነገር ነው፡፡ አሁን ላይ ግን ሁሉም ሰው እንዲያውቅልኝ እፈልጋለሁ ምክንያቱም ማስተላለፍ የምፈልገው ጠቃሚ መልዕክት አለኝ በተለይ ደግሞ ለህፃናት ይላል ካሊዱ ኩሊባሊ፡፡


ግን በመጀመርያ ስለ ጥላቻ ማውራት እፈልጋለው። ለመጀመሪያ ጊዜ የዘረኝነት ጥቃት የደረሰብኝ በባለፈው የውድድር ዓመት ላዚዮን በሴሪያው ስንገጥም ነበር፡፡ በእያንዳንዱ ቅፅበት ኳሷ እኔ እግር ስትሆን ደጋፊዎች ይጮሁብኝ ነበር፡፡ ግን እርግጠኛ አልነበርኩም ይሄ ነገር እየተፈጠረ ስለመሆኑ በዚህ ዘመን ላይ እናም ኳሷ ወደ ውጪ ስትወጣ ወደ ቡድን አጋሮቼ በመሄድ እኔ ላይ ብቻ ነው ይሄን ነገር እያረጉ ያሉት? ብዬ ጠየኳቸው፡፡


ጨዋታው ቀጠለ የላዝዮ ደጋፊዎች ኳሷን በነካኋት ቁጥር ይባስ ብለው የዝንጀሮ ጩሀት ማሰማት ጀመሩ፡፡በዚህ ሰዓት ምን ማረግ እንዳለበኝ ሁሉ ማሰብ አቃተኝ፡፡ ሜዳ ለቅቄ ለመውጣት አሰቡክ የጉዳዩን አሳሳቢነት ለማሳወቅ ነገር ግን ለራሴ አንድ ነገር ነገርኩት ይሄን ካረኩ የላዚዮ ደጋፊዎች የሚፈልጉትን እንደማረግ ተሰማኝ፡፡ በተደጋጋሚ ግን ወደ ጭንቅላቴ አንድ ነገር ይመጣል ይሄን ነገር ለምን ማረግ እንደተፈለገ? ጥቁር ስለሆንኩኝ ነው? ጥቁር መሆን አለማችን ላይ የጤነኛ ሰው ምልክት አይደለም? የሚሉ ነገሮች ይመላለሱብኝ ጀመር፡፡


ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ የዕለቱ ዳኛ ኢራቲ ጨዋታውን አቋረጡት እና ወደ እኔ እየሮጠ መጣ፡፡ ካሊዱ ካንተ ጎን ነኝ አታስብ ጨዋታውን መቀጠል ካልፈለክ ንገረኝ አቋርጠዋለሁ አለኝ፡፡ ይሄ ለኔ ትልቅ ነገር ነበር ነገር ግን ጨዋታውን ጨርሼ መውጣት እንደምፈልግ ነገርኩት፡፡ ከዛም እስታዲየም ውስጥ ላሉ ሰዎች በሙሉ በድምፅ ማጉያ ነገሩ እንዲቆም ተነገረ እና ጨዋታው ቀጠለ፡፡ከሶስት ደቂቃዎች በኋላ ጨዋታው ተጀመረ የዘረኝነት ጥቃቱ እና ጨህቱ ግን አሁንም ሊቆም አልቻለም፡፡


የመጨረሻው ፊሽካ ከተነፋች በኋላ ወደ መልበሻ ክፍል ነበር ወድያው የገባሁት በጣም ተናድጄ ስለነበር፡፡ ወድያው ግን ተመለስኩ አንድ ነገር አስታውሼ ወደ ሜዳ ስገባ ለጨዋታ ይጄው የወጣሁት ህፃን ልጅ ከጨዋታ በኋላ ማልያዬን እንደሰጠው ጠይቆኝ ነበር፡፡ ወድያው ከመልበሻ ክፍል ተመልሼ ልጁን ነበር የፈለኩት ጥጉን ይዞ ቆሞ አገኘሁት እና ማልያዬን ሰጠሁት፡፡ ህፃኑን ልጅ እንዳገኘሁት መጀመሪያ ያለኝ ነገር በጣም ነበር ያስደነገጠኝ፡፡ ''በጨዋታ ወቅት ስለተፈጠረው ነገር በጣም ይቅርታ አለኝ'' ፡፡ ከምንም በላይ የልጁ ነገር ነበር ውስጤ የቀረው ህፃኑ ልጅ ይቅርታ እየጠየቀኝ የነበረው ምን ያህሎቻችን በእኔ እድሜ ልንለው የማንችለውን ነገር ነበር፡፡ ለልጁም ምንም ማለት እንዳልሆነ እና አመስግኜው ተለያየን፡፡


የህፃናት አቅም ይሄን ያህል ነው፡፡ ዓለማችን በአሁን ሰዓት እያጣችው ያለችው ይህን የይቅርታ መንፈስ ነው፡፡ ይሄ የዘረኝነት ጥቃት እኔ ላይ ብቻ ያለ ነገር አይደለም እንዲሁም ደግሞ በቆዳችን መጥቆር የሚፈጠር ነገር አይደለም ፡፡ ለምሳሌ እሰማለው ደጋፊዎች የቡድን ጓደኞቼን የሚጠሩበት መንገድ ሰርብያዊ ተጫዋቾችን ዘላኖች እያሉ ይሰድቧቸዋል ሌላው ቢቀር እንደ ሎሬንዞ ኢንሴኒ ያሉ ጣልያናዊያንን የናፓሊ ቆሻሻዎች በማለት አፀያፊ ስዶቦችን ሲሳደቡ እሰማለሁ፡፡


ከዚህ የተሸሉ ነገሮችን ማረግ አለብን : እንደዚህ አይነት የዘረኝነት ጥቃቶቸ ሲደርሱ ክለቦች መግለጫ ያወጣሉ ከዛ ግን ድርጊቱ ተመልሶ ሲፈፀም ይስተዋላል፡፡ እንግሊዝን ብናይ ነገሮች እንዴት እንደተለወጡ እዩ ጥቃት አድራጊው ከተለየ ዳግመኛ ወደ እስታዲየም እንዳይገባ ነው የሚያረጉት ይሄን ነገር አንድ ቀን የጣልያን እግር ኳስ ፈዴሬሽን ተግባራዊ እንደሚያደርገው ተስፋ አለኝ፡፡


አንድ ነገር ግን ሁሌም ያሳስበኛል ይሄን ስለሚያረጉ ሰዎች እሱም እንዴት ነው ሰዎችን ልንቀይራቸው የምንችለው? እንዴትስ ነው ልቦናቸው ሊነፃ የሚችለው? የሚሉት ነገሮች እንደ እኔ የዚህን ምላሽ አላውቀውም ዝም ብይ ታሪኬን ብቻ ልነግራችሁ ነው የምችለው ይላል የናፖሊው የመሀል ተከላካይ ካሊዱ ኩሊባሊ፡፡


ኩሊባሊ አምና ክለቡ ናፖሊ ኢንተር ሚላንን ሲገጥም በድጋሚ የዘረኝነት ጥቃት ሲደርስበት የዓለም መገናኛ ብዙሃን ሰፊ ሽፋን ሰጥተውት ነበር። ነገር ግን ጉዳዪ እስካሁን ድረስ እልባት ሳያገኝ ይባስኑ በቅርቡ በተጀመረው የአዉሮፓ ሊጎች የዉድድር ዓመት በርከት ያሉ ጥቃቶችን እየሰማን እንገኛለን። 


በመጨረሻም ካሊዶ ኩሊባሊ ንግግሩን ሲጨርስ አዎ እኔ እግር ኳስ ተጫዋች ነኝ ለዛውም ጥቁር እግር ኳስ ተጫዋች በማለት ለዘረኝነት ጥቃት ቦታ እንደማይሰጥ ተናግሯል።

Report Page