FAQ

FAQ


ሰዎች በብዛት የሚጠይቁን ጥያቄ ና የኛ መልሶች
ሰዎች በብዛት የሚጠይቁን ጥያቄ ና የኛ መልሶች

ዋልያ ቴንደር ምንድን ነው?

ዋልያ ቴንደር መንግስታዊ የሆኑና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የሚያወጡአቸውን የጨረታ ማስታወቂያዎች ፣የቢዝነስ ወሬዎችእንዲሁም የንግድ ህጎች በየእለቱ ከተለያዩ ጋዜጣዎችና ምንጮች በመሰብሰብ በየእለቱ ኢንተርኔትን በመጠቀም በዌብሳይት ፣ኢሜል ና ቴሌግራም የዋልያ ቴንደር አባል ለሆኑ የንግድ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች የሚያደርስ በibex procurement solutions p.l.c የተቋቋመ ድርጅት ነው

ጨረታ ማስታወቂያዎችን እንዴት ነው የምታገኙት ወይም ከምን አይነት ምንጮች?

የጨረታ ማስታወቂያዎችን የምናገኘው በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ከሚታተሙ ጋዜጣዎች፣የተለያዩ የብሮድካስት ምንጮች፣ እንዲሁም ከተለያዩ መንግስታዊም የሆኑ ና ያልሆኑ ተቋማት ና ድርጅቶች ባለን ግንኙነት መሰረት ቀጥታ ወደ'ኛ ከሚልኳቸው ጨረታዎች ነው

እንዴት ነው በቴሌግራም መመዝገብ የምችለው በነጻ መሞከር ይቻላል?

አዎ ለማንኛውም ድርጅት ወይም ግለሰብ ለአንድ ሳምንት ና ከዛ በላይ ነጻ የሙከራ ጊዜ እንሰጣለን
ለመመዝገብም ብዙ አማራጮች አመቻችተናል
በመጀመሪያ አዲስ ከሆኑ ቴሌግራም ሰርች ማድረጊያው ላይ @waliatenderbot ብለው ይጻፉ ወይም ይህንን ሊንክ ይጫኑ
ከመረጡት በሃላ start በማለት የሚጠይቅዎትን መረጃ ያስገቡለት ከጥቂት ደቂቃዎች በሃላ የዋልያ ቴንደር አድሚኖች በዚሁ ሊንክ ወይም በኢንቦክስ 'ጨረታዎች በዘርፍ' የሚል የቴሌግራፍ ሊንክ ይልኩልዎታል ይህም ሊንክ ለአንድ ሳምንት በነጻ ሁሉንም ዘርፎች ያለገደብ እንዲከታተሉ ያስችልዎታል

ሁለተኛ የመመዝገቢያ አማራጭ 0919415260 ወይም 0942125616 በስልክዎ ሴብ ካደረጉ በሃላ 'free' ብለው በቴሌግራም ይላኩ ከደቂቃዎች በሃላ ጨረታዎችን የያዘው ሊንክ እንደዚሁ ይላክልዎታል።

አጠቃቀሙ እንዴት ነው?

አጠቃቀሙ እጅግ ቀላል ነው ለዚሁም ነው ቴሌግራምን በአብዛኛው የምንመርጠው።
ምዝገባዎትን ካጠናቀቁ በሃላ በሚላክልዎት ሊንክ ላይ Instant view
የሚለውን ወይም ፎቶውን ሲጫኑ 'ጨረዎች በዘርፍ ' ወደሚል የቴሌግራፍ ገጽ ይወስድዎታል ለምሳሌ በኮንስትራክሽን ብቻ የሚወጡ ጨረታዎችን ለመመልከት ከፈለጉ 'ኮንስትራክሽን ና ማሽነሪ' ምድብ የሚለው ይጫኑ ወዲያው አዳዲስ ጨረታዎች [New] ከፊት አድርጎ ከ2011 አ.ም ጀምሮ የወጡ ጨረታዎችን ያመጣልዎታል
ሁሉም ጨረታዎች በምድቡ ውስጥ የሚያሳዩት አርእስቶችን ነው ፥ አርስቶቹ ጨረታው የወጣበት ቀንና ጋዜጣ (posted date) እና ጨረታው የሚዘጋበት ቀን (deadline) ይዘዋል። የሚፈልጉትን አርእስት ሲነኩት ሙሉ የጨረታውን መረጃ ወደያዘው ገጽ ይመራዎታል።
በየሰአቱ ወይም በየእለቱ 'ሁሉም' በሚለው ዘርፍ ና በየ ምድቦቹ አዳዲስ ጨረታዎች ይጨመራሉ ከእርስዎ የሚጠበቀው አንድ ግዜ የተላከልዎት ሊንክ ላይ በየእለቱ ወይም በየሰአቱ መክፈት ብቻ ለው እዛው 'update' ይደረጋሉ
በተጨማሪም 'update' መደረጉን የምናሳስብበት ግሩፕ አለ ማንኛው ሰው መቀላቀል ይችላል
@waliatendergroup


ለምን በቴሌግራም?

ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች ጨረታዎችን በቀላል መንገድ ና በብዙ አማራጭ እንዲከታተሉ ለማድረግ የተሻለ አማራጭ ለማድረግ ከማሰብና ቴሌግራም ለእንደዚህ አይነት የመረጃ ልውውጦች ደህንነቱ የተጠበቀ ና ተመራጭ ስለሆነም ነው

ለአንድ ሳምንት ነጻ የሙከራ ጊዜ ካበቃ በሃላስ?

ለአንድ ሳምንት ነጻ የሙከራ ጊዜ ካበቃ በሃላ የተመዘገቡበት ቦት(Bot) ባን (Ban) ያደርገዎታል ወይንም ጨረታዎችን ለመክፈት ሲሞክሩ የሙከራ ጊዜዎ እንዳበቃ የሚጠቅስ መልእክት ብቻ ነው የሚመጣው

የሙከራ ጊዜየን ጨርሼ በቋሚነት ለመመዝገብ ምንድን ነው የማደርገው?

የሙከራ ጊዜዎን ካጠናቀቁ በሃላ ቋሚ ደንበኛ ለመሆን ከፈለጉ
በዋልያ ቴንደር ደንብ ና ግዴታዎች ከተስማሙ ቋሚ ደንበኛ ለመሆን የሚያስችልዎትን የአገልግሎት ክፍያ አማራጭ (package ) ይመርጣሉ
ለምሳሌ በBasic package የ3 ወር 500 ብር ፣የ 6ወር 900 ብር ፣ወይም የአመት 1200ብር የአገልግሎት ክፍያ ከፍለው እንዳጠናቀቁ ከሙሉዋስትና ጋር ያለምንም ስጋት ጨረታዎችን የሚከታተሉበት ሊንክ (ሌላ) ይላክልዎታል።

ክፍያ እንዴት ነው መክፈል የምችለው?

በኢንቦክስ ላይ የምንልክልዎት የባንክ መረጃ ይኖራል( በደንብ ና ግዴታዎቻችን ከተስማሙ በሃላ)
በመረጡት በባንክ ትራንስፈር አሊያም በሞባይል/ኢንተርኔት ባንኪንግ እንዲሁም አዲስ አበባ ላሉ ደንበኞች የማርኬቲንግ ሰራተኞቻችንን ቢሮዎ(ያሉበት ) ድረስ በመላክ እንቀበላለን

ተጨማሪ ጥያቄ ወይም አስተያየት ካለዎት @taduad ይጻፉልን ወይም በ0919415260 በመደወል ያሳውቁን
ዋልያ ቴንደር

Report Page