ETHIOPIA

ETHIOPIA


#ETHIOPIA

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከአፍሪካ ህብረት ቋሚ መልክተኞች ኮሚቴ ቢሮ አባላት፣ከአምስቱ ቀጣናዊ የአፍሪካ አምባሳደሮች ዲኖች፣ ከአጠቃላይ የአፍሪካ አምባሳደሮች ዲን እንዲሁም የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀ-መንበርን ካካተተ የልዑካን ቡድን ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

በወቅቱም ቡድኑን በመወከል በኢትዮጵያ የሴኔጋል አምባሳደር ባስተላለፉት መልዕክት የኢትዮጵያ ሉዑላዊነት እና የግዛት አንድነት በተመለከተ የአፍሪካ አምባሳደሮች የማይናወጥ አቋም እንዳላቸው አስረድተዋል፡፡ አያይዘውም በህዝብ ከተመረጠው እና ቅቡልነት ካገኘው የኢትዮጵያ መንግስት ጎን እንደሚቆሙኑ እና  አጋርነታቸው የጸና መሆኑን አሳውቀዋል፡፡

በሌላ በኩል የቪዬና ኮንቬንሽን እና የተቀባይ አገር ስምምነትን መነሻ በማድረግ፤ የአስቸካይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም ጋር ተያይዞ እንዲስተካከሉ የሚፈልጓቸውን ጉዳዮች አንስተዋል፡፡ 

በመቀጠልም ኢትዮጵያ ያጋጠማትን ችግር ለመፍታት አቅሙ እንዳላት እንደማይጠራጠሩና የአፍሪካ ህብረት ልዩ መልዕክተኛ የሆኑት የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ ሰላማዊ መፍትሄ ለማፈላለግ ለሚያደርጉት ጥረት የአፍሪካ አምባሳደሮች ሙሉ ድጋፍ እንደማይለያቸው ገልጸዋል፡፡

አቶ ደመቀ በበኩላቸው ኢትዮጵያ አሁን በገጠማት አስቸጋሪ ሁኔታ፤ በፓን አፍሪካዊነት መርህ አፍሪካውን ወንድሞች እና እህቶች ላሳዩት አጋርነት የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ልዩ አክብሮት ያላቸው መሆኑን ገልጸው፤ ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ 

በመቀጠልም አሉ የሚባሉ የአገራችንን መሠረታዊ ችግሮችን ለመፍታት መንግስት በአገር ደረጃ ሁሉን አቀፍ ውይይት ለመጀመር ዝግጅት እያጠናቀቀ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያውያን ያጋጠማቸውን ፈተና በጋራ ለመሻገር በአንድነት እየተረባረቡ መሆኑንም በዝርዝር አብራርተዋል፡፡ 

ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸምና የዲፕሎማቲክ መብቶችን አጠባበቅ አስመልክቶ ለቀረበው ጥያቄ ፤ አዋጁ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡን ጨምሮ የሁሉንም ደህንነት ለማስጠበቅ የወጣ መሆኑና በአፈጻጸም ወቅት የተፈጠሩ ችግሮችን ለማረም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት የማጣራት ሥራ ተሰርቶ መፍትሄ እንደሚሰጠው አረጋግጠዋል፡፡ በቀጣይም በዚሁ መልክ ይበልጥ ተቀራርቦ መረጃዎችን ለመለዋወጥ ለችግሮቹ መፍትሄ ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸውላቸዋል፡፡

አምባሳደሮቹም ለተደረገላቸው ገለጻ አመስግነው፤ በቀጣይም በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተመሳሳይ መድረክ ተዘጋጅቶ ለመገናኘት ፍላጎታቸውን ገልጸዋል፡፡

በመቀጠልም አሉ የሚባሉ የአገራችንን መሠረታዊ ችግሮችን ለመፍታት መንግስት በአገር ደረጃ ሁሉን አቀፍ ውይይት ለመጀመር ዝግጅት እያጠናቀቀ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያውያን ያጋጠማቸውን ፈተና በጋራ ለመሻገር በአንድነት እየተረባረቡ መሆኑንም በዝርዝር አብራርተዋል፡፡ 

ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸምና የዲፕሎማቲክ መብቶችን አጠባበቅ አስመልክቶ ለቀረበው ጥያቄ ፤ አዋጁ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡን ጨምሮ የሁሉንም ደህንነት ለማስጠበቅ የወጣ መሆኑና በአፈጻጸም ወቅት የተፈጠሩ ችግሮችን ለማረም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት የማጣራት ሥራ ተሰርቶ መፍትሄ እንደሚሰጠው አረአምባሳደሮች በቀጣይም በዚሁ መልክ ይበልጥ ተቀራርቦ መረጃዎችን ለመለዋወጥ ለችግሮቹ መፍትሄ ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸውላቸዋል፡፡

አምባሳደሮቹም ለተደረገላቸው ገለጻ አመስግነው ፤ በቀጣይም በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተመሳሳይ መድረክ ተዘጋጅቶ ለመገናኘት ፍላጎታቸውን ገልጸዋል፡፡

ምንጭ፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

@tikvahethiopia

Report Page