ethiopia

ethiopia


ETHIOPIA

የትግራይ ክልልና እና የፌደራል መንግሥት ከየት ወዴት?

በትግራይ ክልል ገዥ ፓርቲ ሕወሓትና በማዕከላዊው መንግሥት መካከል ያለው ቁርሾ ወደ ተኩስ ልውውጥ አምርቷል። አልፎም ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይወታደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ትዕዛዝ ሰጥተዋል።

ለመሆኑ የሕወሓትና የፌዴራል መንግሥቱ ቁርሾ የጀመረው እንዴትና መቼ ነው?

ሰኔ 6፣ 2010 ዓ.ም. - ሕወሓት የፌዴራል መንግሥት ከኤርትራ መንግሥት ጋር ሰላም ለመፍጠር ማቀዱን የሚተች መግለጫ አወጣ። መግለጫው በያኔው ኢሕአዴግ ውስጥ ያሉ 36 ሕግ መወሰኛና 180 የምክር ቤት አባላት አስቿኳይ ስብሰባ እንዲያደርጉ ጥሪ አቀረበ። የስብሰባው ዋነኛ ዓላማ የባድመ ጉዳይ ነበር።

ጥቅምት 5፣ 2012 ዓ.ም. - ሕወሓት ኢሕአዴግ ከስሞ እንደ አንደ ፓርቲ ሊዋቀር መሆኑን ተቃወመ። በወቅቱ ድርጅቱ በምክንያትነት ያቀረበው አንድ ውህድ ፓርቲ መዋቀሩ ለአንድነት አደጋ ነው የሚል ነበር። ሕወሓት የኢሕአዴግን መክሰም በመቃወም የአዲሱ ፓርቲ [ብልፅግና ፓርቲ] አካል እንደማይሆን አሳወቀ።

ጥቅምት 9፣ 2012 ዓ.ም. - የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ የኢህአዴግ መሥራች የሆነው ሕወሓት አዲስ ውህድ ፓርቲ ማዋቀር አያስፈልግም ማለቱን ተቹ።

ጥቅምት 29፣ 2012 ዓ.ም. - ኢሕአዴግ ከስሞ አንድ ዉህድ ፓርቲ እንዲቋቋም ተወሰነ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወቅቱ በትዊተር ገፃቸው "የኢሕዴግ አባላት አንድ ፓርቲ ለማዋቀር ያደርግነው ስብሰባ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል። አንድ ወጥ ፓርቲ መዋቀሩ የፌዴራል ሥርዓቱን ያጠናክረዋል፤ ድምፅ ለሌላቸውም ድምፅ ይሆናል" ሲሉ ፅፈው ነበር።

ኅዳር 7፣ 2012 ዓ.ም. - ሕወሓት፤ ኢሕአዴግ ሙስናን በመታገል ሰበብ የትግራይ ሰዎችን ዒላማ እያደረገ ነው ሲል ተቸ።

ኅዳር 10፣ 2012 ዓ.ም. - ሕወሓት፤ ኢሕአዴግ አባል ፓርቲዎችን ለማዋቀር የሚያስችል ሥልጣን የለውም አለ። "የኢሕአዴግ ሥራ አስፈፃሚ አንድ ፓርቲ ማወቀር ላይ ሳይወያይ ውሳኔ ወስኗል፤ ይህ ደግሞ ሕጋዊ አይደለም" በማለት በኢሕአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ እንደማይገኝ አስታወቀ።

ኅዳር 11፣ 2012 ዓ.ም. - የኢሕአዴግ ምክር ቤት ፓርቲው ከስሞ ብልፅግና ፓርቲ እንዲቋቋም ያለተቃውሞ ወሰነ። ሕወሓት በስብሰባው ላይ አልተገኘም ነበር።

ኅዳር 16፣ 2012 ዓ.ም. - ሕወሓት፤ ኢሕአዴግ አባላቱን በአንድ ፓርቲ ጥላ ሥር ማዋቀር የሻተው በርካታ ሕዝብ ያላቸው ክልሎችን ለመጥቀም ነው ሲል ወነጀለ። "ውሳኔው እኩልነት ላይ የተመሠረተ አንድነት አያመጣም። ጨቋኝ መሪና ተጨቋኝ ሕዝብ ይፈጥራል እንጂ" ብሎ ነበር ሕወሓት በወቅቱ።

ኅዳር 23፣ 2012 ዓ.ም. - ሕወሓት "ሕገ መንግሥቱንና ፌዴራል ሥርዓቱን የሚታደግ ብሔራዊ መድረክ" የተሰኘ መድረክ በማዘጋጀት የብልፅግናን መዋቀር ተቃወመ። በወቅቱ የሕወሓት ምክትል ኃላፊ የነበሩት ደብረፂዮን ገብረሚካኤል "ሕገ መንግሥቱ በግለፅ እየተጣሰ ነው፤ ሰላም እየራቀ ነው፤ የዜጎች ደህንነት አደጋ ላይ ወድቋል፤ ከቆየ መሰደድና የንብረት ውድመት ተስፋፍቷል" ሲሉ ተደምጠዋል።

ኅዳር 29፣ 2012 ዓ.ም. - የትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ [ትሕዴን] ከሕወሓት ጋር መዋሃዱን ይፋ አደረገ። የፓርቲው ሊቀ መንበር ተስፋዬ መኮንን "አሁን ያለውን የኢትዮጵያዊ ሁኔታ በማየት ፓርቲያችን ከስሞ ከሕወሓት ጋር ለመዋሃድ ወስነናል" ብለው ነበር።

ታኅሣሥ 7፣ 2012 ዓ.ም. - ሕወሓት፤ ብልፅግና ፓርቲ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ስላልተመዘገበ ሕጋዊ ፓርቲ አይደለም ሲል ኮነነ። የሕወሓት ከፍተኛ አመራር የሆኑት ጌታቸው ረዳ "ብልፅግና ሃሰት ነው። ግልፅ የሆነ ራዕይና አቅጣጫ የለውም" ሲሉ ተደመጡ።

ታኅሣሥ 20፣ 2012 ዓ.ም.- ኢሕአዴግን የመሠረቱት ሶስቱ ፓርቲዎች [ብአዴን፣ ኦህዴድና ደህዴን] ክደውናል ሲል ሕወሓት ወቀሰ።

ግንቦት 29፣ 2012 ዓ.ም. - ሕወሓት ብልፅግና ሕጋዊ አይደለም በማለት ፓርቲውን እንደማይቀላቀል አሳወቀ። ሕወሓት በወቅቱ ባወጣው መግለጫ "ኢሕአዴግ በመሥራች አባላቱ ክህደት ምክንያት ከስሟል። ምክር ቤታችን ይህን ድርጊት ይቃወማል" ብሎ ነበር።

ጥር 13፣ 2012 ዓ.ም. - ጠ/ሚ አብይ አሕመድ የሕወሓት አባላትን ዒላማ እያደረጉ ነው ሲል ሕወሓትን ወቀሱ። በወቅቱ ጠ/ሚ አቢይ፤ ፈትለወርቅ ገብረእግዚያአብሔርን ከሥልጣናቸው ማንሳታቸውን ተከትሎ ነው ሕወሓት ይህን መግለጫ ያወጣው።

ጥር 16፣ 2012 ዓ.ም. - የአማራ ክልል፤ ሕወሓት በጥምቀት በዓል ወቅት "የሽብር ድርጊት ለመፈፀም" ቡድኖች ልኳል ሲል የትግራይ ክልል ገዥ ፓርቲን ወቀሰ። "ሽብር አድራሾች" በቁጥጥር ሥር መዋላቸውንም አሳወቀ።

ጥር 25፣ 2012 ዓ.ም. - ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ ፓርላማ ቀርበው ሚኒስቴሮችን በብሔራቸው ምክንያት እንዳላባረሩ ተናገሩ። ካቢኔያቸውን የማዋቀር ሥልጣን እንዳላቸውም ተናገሩ። የትግራይ ሕዝብ የፈለገው መንግሥት አካል መሆን ይችላል ሲሉም ተናገሩ።

ጥር 26፣ 2012 ዓ. ም. - ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለሕወሓትና ለብልፅግና ንብረት አከፋፈለ። ይህ የሆነው ሕወሓት ለቦርዱ ደብዳቤ ከፃፈ በኋላ ነው።

የካቲት 1፣ 2012 ዓ.ም. - የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ሕወሓት የሰላም ሂደቱን እያደናቀፈ ነው ሲሉ ወቀሱ። የኤርትራው ማስታወቂያ ሚኒስቴር የማነ ገብረመስቀልም ይህን የሚያንፀባርቅ ፅሑፍ ፃፉ።

ሚያዝያ 27፣ 2012 ዓ.ም. - ሕወሓት ክልላዊ ምርጫ እንደሚያደርግ አስታወቀ።

ጳጉሜ 4፣ 2012 ዓ.ም. - የትግራይ ክልል ምርጫ አካሄደ።

መስከረም 1፣ 2013 ዓ.ም. - ሕወሓት ክልላዊውን ምርጫ ማሸነፉን ይፋ አደረገ። በክልሉ ምርጫ ኮሚሽን መሠረት ሕወሓት ከ2.6 ሚሊዮን መራጮች 98.2 በመቶ ድምፅ በማግኘት ነው ያሸነፈው።

መስከረም 26፣ 2013 ዓ.ም. - የሕወሓት አባል የሆኑ የመንግሥት ሠራተኞች ወደ ትግራይ ክልል እንዲመለሱ ትዕዛዝ አስተላለፈ። መስከረም 25 የተደረገው የፓርላማ መክፈቻም ህገ ወጥ ሲል ፈረጀ።

ጥቅምት 14፣ 2013 ዓ.ም. - የፌዴራል መንግሥት ወታደራዊ የሥልጣን ሹም ሽር ሊያደርግ ነው መባሉን ተከትሎ የትግራይ ክልል ማዕከላዊው መንግሥት ይህን ማድረግ የሚያስችል ሥልጣን የለውም አለ።

ጥቅምት 18፣ 2013 ዓ.ም. - አንድ ነባር ወታደራዊ መኮንን ወደ መቀለ እንዳይገቡ ሕወሓት አገደ። አልፎም የሰሜን ዕዝን ለመምራት አዲስ የተሾሙት ሜጀር ጄነራል በላይ ስዩም ወደ ክልሉ መግባት እንደማይችሉ አሳወቀ።

ጥቅምት 22፣ 2013 ዓ.ም. - የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሕወሓትን እርምጃ ተከትሎ መሰል እርምጃዎችን እንደማይታገስ አስታወቀ።

ትናንት ምሽት የትግራይ ክልል መንግስትና የፌደራል መንግስቱ ግልፅ ግጭት ውስጥ ገቡ።

Via BBC
BMMTimes

Report Page