COVID19ETHIOPIA

COVID19ETHIOPIA

ታማኝ ዜና

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 30 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!


ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 4,352 የላብራቶሪ ምርመራ ሰላሳ (30) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 731 ደርሷል፡፡

ቫይረሱ የተገኘባቸው 22 ወንድ እና 8 ሴት ሲሆን የዕድሜ ክልላቸው ከ9 እስከ 60 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 15 ሰዎች ከአዲስ አበባ (2 በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያላቸውና 13 ሰዎች የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት የሌላቸው) ፣ 2 ሰዎች ከትግራይ ክልል (የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸውና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያሉ) ፣ 8 ሰዎች ከአማራ ክልል (የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸውና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያሉ) ፣ 1 ሰው ከኦሮሚያ ክልል (ውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት የሌለው) ፣ 3 ሰዎች ከሐረሪ ክልል ( በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያላቸው) እንዲሁም አንድ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያለው ድንበር ተሻጋሪ መኪና አሽከርካሪ ነው።


የዕለቱ ታማሚዎች የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት ፦

• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው - 11

• በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያላቸው - 5

• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት የሌላቸው - 14

ተጨማሪ መረጃ ፦

በትላንትናው ዕለት አስራ አራት (14) ሰዎች ከአዲስ አበባ ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 181 ደርሰዋል።

Report Page