ETHIOPIA

ETHIOPIA


የሰሞኑ የዜጎች ግድያ ፦

"...ልክ ፀሎት ይደረግ ተብሎ ፤ በፀሎት ሲጀመር የታጠቁ ኃይሎች መጥተው ኢሰብዓዊ ጭፍጨፋ አደረጉ" - በአማሮ ልዩ ወረዳ ዳኖ ቀበለ የተፈፀመው ጥቃት ዓይን እማኝ

ከቀናት በፊት በደቡብ ክልል አማሮ ልዩ ወረዳ ፣ ዳኖ ቀበሌ ውስጥ ታጣቂዎች ከፈፀሙት ጥቃት የተረፈ አንድ ሰው ስለነበረው ሁኔታ ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ ቃሉን ሰጥቷል።

ጥቃቱ የተፈፀመው ለእርቅ በተሰበሰቡ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ባለስልጣናት ላይ ነው።

በተፈፀመው ጥቃት ከሞቱት መካከል የአማሮ ልዩ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ እንደሚገኙበት መገለፁ ይታወሳል።

ይኸው የአይን እማኝ እንደሚገልፀው ስብሰባው የተጠራው በአማሮ እና ጉጂ ተጎራባች አካባቢዎች የተፈጠረውን ጠብ በሰላም ለመፍታት ነበር።

ስብሰባውን ለማድረግ ፀሎት ተደርጎ እንዳበቃ በተሰብሳቢው ላይ ታጣቂዎች የተኩስ እሩምታ ከፍተው ሰዎችን ገደሉ፣ ቁስለኛ አደረጉ።

የአይን እማኙ ፥ "ልክ ፀሎት ይደረግ ተብሎ በፀሎት ሲከፈት በነበረበት ወቅት ያታጠቀ ኃይል መጥቶ ኢ-ሰብዓዊ በሆነ መልኩ በሰው ላይ ሊፈፀም የማይገባው ነገር ነው ጭፍጨፋ ያደረጉት" ብለዋል።

የደቡብ ክልል መንግስት ከኦሮሚያ ክልል መንግስት ጋር በመተባበር ገዳዮችን ለፍርድ ለማቅረብ እንደሚጥር አሳውቋል።


በኦሮሚያ ክልል እየተፈፀሙ ያሉ ግድያዎች ፦


በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ካለፈው እሁድ ጀምሮ ታጣቂዎች በከፈቱት ጥቃት በርካታ ሰዎች መግደላቸው ፣ መቁሰላቸው እና ማገታቸውን ነዋሪዎችን በማሳወቅ ላይ ይገኛሉ።

አበደንጎሮ በተባለ ወረዳ 20 ሰዎች መገደላቸውን የወረዳው ነዋሪዎች አሳወቀዋል።


ነዋሪዎቹ እንደሚገልፁት ከሆነ ደቢስ በተባለው ቦታ ከተገደሉት ሰዎች መካከል ህፃናት፣ አዛውንቶች እና የሃይማኖት አባቶች ይገኙበታል።


ስለተፈፀመው ጥቃት መንግስት እስካሁን ምላሽ አልሰጠም።


አንድ የአበደንጎሮ ወረዳ ነዋሪ ታጣቂዎቹ ጥቃቱን ያደረዱት አብዛኛው ሰው ቤተክርስቲያን ሲሳለም ነው ብለዋል።


አንድ ሌላ ነዋሪ ደግሞ ታጣቂዎች ነዋሪዎችን ከገደሉ እና ካገቱ በኃላ ፀጥታ ኃይሎች በአካባቢው ሲደርሱ ሸሽተዋል ብለዋል።


በሌላ በኩል ትላንት ሆሮ ጉዱሩ ጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ ሆሮደኢ ቀበሌ ታጣቂዎች ከቀን 10 ሰዓት ጀምሮ ታጣቂዎች ተኩስ ከፍተው እንደነበር ተሰምቷል።


በጥቃት ስለደረሰ ጉዳት አልታወቀም።


የመንግስት አካላት በዜጎች ላይ እየደረሱ ስላሉት ጥቃቶች ምላሽ ለመስጠት አለመፈለጋቸው፣ መረጃዎችን አጣርተው ለመግለፅ አለመፈለጋቸው ፣ የዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅ አለመቻላቸው በርካቶችን እያስቆጣ ነው።


እስካሁን ድረስ መንግስት እየተፈፀመው ስላለው ግድያ ምላሽ አልሰጠም።

Report Page