#ETH

#ETH


በምርጫ ስለሚወዳደሩ የመንግሥት ሰራተኞች አዲሱ የምርጫ እና የፓለቲካ ፓርቲዎች አዋጅ ምን ይላል?

በግልም ሆነ የፖለቲካ ፓርቲ አባል በመሆን በምርጫ ለመወዳደር የሚፈልጉ የመንግሰት ሰራተኞችን በተመለከተ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ ምግባር አዋጅ ቁ. 1162/2011 አንቀጽ 33 በሁለት ይከፍላቸዋል፤

1) በግል ወይም የፖለቲካ ፓርቲ እጩ ተወዳዳሪ ሆነው ከቀረቡ የያዙትን የመንግሥት ሥራ ለመልቀቅ የሚገደዱ የመንግስት ሰራተኞች፡

1.1. ዳኞች፣ ዓቃቤ ሕጎች፣ ወታደሮች፣ የፖሊስ እና ሌሎች የጸጥታ ኃይል አባላት፣ የደህንነት ሰራተኞች፣ እና የቦርዱ ሰራተኞች በግል ወይም የፖለቲካ ፓርቲ እጩ ተወዳዳሪ ሆነው ከቀረቡ የያዙትን የመንግሥት ሥራ መልቀቅ አለባቸው፡፡

1.2. ዳኞች፣ ዐቃቤ ሕጎች፣ ወታደሮች፣ ፖሊስ እና ሌሎች የጸጥታ ኃይል አባላት፣ የደህንነት ሰራተኞች እና የቦርዱ ሰራተኞች በምርጫ ውድድር ጊዜ ማንኛውንም ተወዳዳሪ ለማስመረጥ በመደገፍ፣ በመናገር፣ በመፃፍና በመሳሰሉት ተሳታፊ መሆን የለባቸውም፡፡

2) የያዙትን የመንግስት ሥራ ሳይለቁ በግል ወይም የፖለቲካ ፓርቲ እጩ ተወዳዳሪ ሆነው መቅረብ ስለሚችሉ የመንግስት ሰራተኞች

2.1. ከላይ በተራ ቁጥር 1 ስር ከተመለከቱት ውጪ ያለ ማንኛውም የመንግስት ሠራተኛ የመንግሰት ስራውን እንደያዘ በግሉ ወይም የፖለቲካ ፓርቲ አባል በመሆን ለምርጫ መወዳደር ይችላል፡፡

2.2. አንድ የመንግሥት ሰራተኛ ለምርጫ ተወዳዳሪ ሆኖ ሲቀርብ የምርጫ ቅስቀሳ በሚካሄድበት ወቅት እና ምርጫው በሚከናወንበት ጊዜ ያለደመወዝ ፈቃድ እንዲሰጠው ይደረጋል፡፡

2.3. በምርጫ የሚወዳደር የመንግስት ሰራተኛ በሁሉም ደረጃ ለሚገኙ ምክር ቤቶች ምርጫ እንቅስቃሴ በሚሳተፍበት ጊዜ በማንኛውም የቀጣሪው የመንግሥት መስሪያ ቤት ንብረት መገልገል አይፈቀድለትም፡፡               ምንጭ፥ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ!

Report Page