#ETH

#ETH


*****************************************

በመጅሊስ የተዋቀረው አጣሪ ቡድን ሞጣ ጎብኝቶ ተመለሰ

*****************************************

ታህሳስ 10/2012 ላይ በአማራ ክልል የምስራቅ ጎጃም ዞን በሞጣ ከተማ መስተዳደር በተከሰተው ሙስሊሞችና መስጊዶች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ተከትሎ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ከፍተኛ አመራር የሞጣ ጥቃት እና ሌሎች የመብት ጥሰቶች የሚከታተል አብይ ኮሚቴ ማቋቋሙ ይታወሳል። 

የዚህ አብይ ኮሚቴ ከተሰጡት ኋላፊነቶች አንዱ ጥቃቱን እቦታው ድረስ በመሄድ የጉዳቱን መጠን ማጥናት እንደመሆኑ መጠን 4 አባላት ያሉት ቡድን ወደ ቦታው ተጉዞ ጉዳት የደረሰባቸውን መስጊዶች እና ግለሰቦች እንዲሁም የሚመለከታቸው የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችን አነጋግሮ ተመልሷል። 

ቡድኑ በሞጣ ቆይታው የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ያነጋገረ ሲሆን የጥቃቱን አስከፊነትና ቅንብር ለመታዘብ የቻለ ሲሆን "ተቃጠለ" የተባለውንም የጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያንን ጎብኝቷል።

ከዚህ ባሻገር ከክልሉ ከፍተኛ አመራር ጋር በጉብኝቱ ግኝቶች ጋር በተያያዘ ጥያቄዎችን ያቀረበ ሲሆን ጠቅላይ ም/ቤት በታህሳስ 15 ጋዜጣዊ መግለጫው ያቀረባቸውን ጥያቄዎች በይፋ በደብዳቤ አቅርበዋል። የክልሉ ርእሰ መስተዳደር በአስቸኳይ ስብሰባ ምክንያት ማግኘት ባለመቻላቸው የተቀበሉትን አቶ ዘላለም ልጃለም አሰፋ የርእሰ መስተዳድሩ ፅ/ቤት ሃላፊ እና አቶ ተካ በቀለ የርእሰ መስተዳድሩ የህዝብ ግንኙነት አማካሪና የክልሉ የብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ ጋር ሰፊ ውይይት አድርጓል። በውይይታቸው ወቅትም ጥቃቱ የተደራጀና የተቀናጀ በሚመስል የተካሄደ እንደመሆኑ መጠን መሰል ጥቃቶች እንዳይከሰቱ ዘላቂ መፍትሄ እንዲበጅና ክልሉ ለዜጎች የደህንነት ዋስትና እንዲሰጥ፣ አጥፊዎች ተለይተው ለፍርድ እንዲቀርቡ፣ የሞራልና የፍትህ ጥያቄ እንዲመለሱ፣ ለተጎዱት ንብረቶች ተገቢው ካሳ እንዲከፈል እና እንዲሁም የቆዩ የመብት ጥያቄዎች ለምሳሌ 'በእሁድ በአል ቀን ስራ አትሰሩም' የሚሉ እና ተያያዥ አ—ፍትሃዊ ጫናዎች፣ ሲንከባለሉ የቆዩ የመቃብርና የመድረሳ ጥያቄዎች በአስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።  

በመጨረሻም አመራሮቹ ከላይ ለተዘረዘሩት ጥያቄዎች ክልሉ ማክሰኞ ላይ በሚያደረገው ስብሰባ ተሞርኩዞ ይፋዊ ምላሽ እንደሚሰጡ በመግለፅ ነገሮችን ለማረጋጋት እንደሚሰሩ አረጋግጠው ቡድኑን ሸኝቷል።

የአጣሪ ቡድኑ በዚህ አጋጣሚ ለቡድኑ አስፈላጊውን የፀጥታ ሽፋን (የልዩ ኃይል) በመመደብ እና ገንቢ ውይይት በማድረግ የተባበረውን የክልሉ አመራሮች ለማመስገን ይወዳል።

(Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council)

Report Page