#ETH

#ETH


የመከላከያ የደንብ ልብስ ወደ አገር ውስጥ መግባት ሊጀምር ነው

የአገር መከላከያ ሠራዊት አዲስ የደንብ ልብስ በአንድ ወር ውስጥ የመጀመሪያው ጭነት ወደ አገር ውስጥ እንደሚገባና ከሦስት ወራት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ እንደሚረከብ አስታወቀ።

አምስት ወራት በፈጀ ሒደት ዓለማቀፍ ጨረታ በማውጣትና ከ 15 የማያንሱ ድርጅቶችን በማወዳደር የተዘጋጀው የደንብ ልብስ፣ የምድር እና የአየር ኃይልን የውጊያ እና የክብረ በዓላት ልብሶችን ከነመጫሚያው ያሟላ ነው። 

ጨረታውን ያሸነፈው የቻይና ድርጅትም ከመከላከያ ጋር ውል በማሰር ልብሶቹን ማዘጋጀት የጀመረ ሲሆን፣ የመከላከያ ሚኒስቴርም የምርት ሒደቱን በቅርብ እየተከታተለ እንደሆነና የደንብ ልብሶቹን ለማዘጋጀት ጥቅም ላይ የዋለው ጨርቅ ከዚህ ቀደም ከነበረው ጥራት ከፍ ያለ መሆኑን የተናገሩት የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጀር ጄነራል መሐመድ ተሰማ ልብሶቹ ተሠርተው በሚጠናቀቁበት ጊዜም ወደ አገር ውስጥ ከሚገቡ ምርቶች ላይ ናሙና ተወስዶ የጥራት ፍተሻ እንደሚደረግበት ተናግረዋል።

ሜጀር ጄነራል መሐመድ ጨምረው፣ ኤታማጆር ሹሙ እና ምክትል ኤታማጆር ሹሙ በተደጋጋሚ ለብሰውት የሚታዩት የውጊያ ልብስ አዲሱ ዲዛይን መሆኑን አረጋግጠዋል።

 እንደ ሜጀር ጄነራል መሐመድ ገለጻም ልብሱ በተደጋጋሚ ተለብሶ እና ተሞክሮ ጥራቱ ሊረጋገጥ ከመጫሉ ባሻገር በምርት ሒደት ከኹለት ጊዜ በላይ ባለሞያዎች እየተላኩ ናሙና በመውሰድ እና በዓለማቀፍ ላቦራቶሪ በማስገምገም ጥራቱን መከታተላቸውንም አብራርተዋል፡፡

ሜጀር ጄነራል መሐመድ እንዳሉት፣ የሠራዊቱ የደንብ ልብስ ከሚቀየርባቸው ምክንያቶች መካከል ልብሱ ለሕገወጥ ተግባር ሲባል በተለያዩ ሰዎች እጅ በመግባቱ ነው። አክለውም የደንብ ልብሱ የሚቀየርበት መመሪያ የሚዘጋጅ ሲሆን፣ አወጋገዱ ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ እንደሚሆንም ተናግረዋል።

Report Page