ETH

ETH

ቲክቫህ ኢትዮጵያ

ቦርዱ በኦነግ አመራር አባላት መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ላይ ውሳኔ ሰጠ!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አመራር አባላት መካከል የተፈጠረ አለመግባባትን አስመልክቶ ውሳኔ አስተላልፏል።

በድርጅቱ ሊቀመንበር ዳውድ ኢብሳና እንዲሁም ምክትል ሊቀ መንበር አራርሶ ቢቂላ የሚመራውና ለሁለት የተከፈሉት ቡድኖች እርስ በእርስ የእግድ ደብዳቤ ተጻጽፈዋል።

ቦርዱ በተሰጠው ስልጣን መሰረትም ፓርቲ አባላት መኻከል አለመግባባት ለመፍታት የባለሞያዎች ኮሚቴ ለማቋቋም ውሳኔ ቢያሳልፍም በእነ አቶ ዳውድ በኩል ባለሞያ ለመመደብ ፍቃደኛ ባለመሆናቸው ምክንያት ቦርዱ በራሱ ጉዳዩን መርምሮ ለመወሰን መገደዱን ገልጿል፡፡ 

ቦርዱ ጉዳዩን በመመርመር ሂደት በሁለቱም ወገን ያሉ የፓርቲው አመራሮች እንዲሁም የፓርቲው ስነስርአት እና ቁጥጥር ኮሚቴንም ጠርቶ አወያይቶ በአመራሮቹ መካከል ያለው አለመግባባት በፓርቲው ውስጥ እንደማይፈታ በማመን ውሳኔ አስተላልፏል።

በዚህም:-

ቦርዱ በድርጅቱ ምክትል ሰብሳቢ አቶ አራርሶ ቢቂላ ፊርማ የተላከለትን የድርጅቱን ሊቀመንበር የታገዱበትን ስብሰባ በሚገልጸው ቃለጉባኤ ላይ ከፓርቲው 8 ሥራ አስፈጻሚ 5ቱ መገኘታቸውን ይገልጻል።

ሆኖም ከፈረሙት መካከል አንዱ በዜግነት ምክንያት ከዚህ ቀደም ከሥራ አሰፈጻሚ የተቀነሱ በመሆናቸው 2/3ተኛ መልአተ ጉባኤ ያልተሟላበት በመሆኑ ከድርጅቱ የስራ አስፈጻሚ የተላከው የሊቀመንበሩ እገዳ ውሳኔ ህጋዊ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ወስኗል፡፡

በአቶ ዳውድ ፊርማ የተከናወነው እና የብሔራዊ ምክር ቤት ውሳኔ ነው ተብሎ ለቦርዱ የቀረበው ወሳኔም የስብሰባው በትክክል መካሄዱን የሚያሳይ ቃለጉባኤ የሌለው፤ በሊቀመንበሩ ፊርማ ብቻ የተላከ ውሳኔ በመሆኑ ህጋዊ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ወስኗል፡፡

የፓርቲው ሊቀመንበርም ሆነ በሊቀመንበሩ ታግደዋል የተባሉት ስራ አስፈጻሚዎች ህጋዊ የድርጅቱ አካላት ሆነው እንዲቀጥሉ ቦርዱ የወሰነ ሲሆን ሁለቱም ቡድኖች በጋራ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያከናውኑና ስብሰባቸውንም በቦርዱ ስበሰባ አዳራሽ እንዲያከናውኑ ወሳኔ አስተላልፏል።

Report Page