#ETH

#ETH


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ኢዴፓ/ አመራር ውዝግብ ዙሪያ ሲቀርብለት ለቆየው አቤቱታ ውሳኔ ሰጠ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ/ ኢዴፓ/ ባለፉት ሁለት አመታት የቆውን የፓርቲው አመራር ምርጫ እና ተያያዥ ውዝግብ መርምሮ ውሳኔ ሰጥቷል።

ኢዴፓ ( እነ አቶ አዳነ ታደሰ ) በ25/02/2012 በተጻፈ ደብዳቤ የኢዴፓ አመራር ምርጫ እና የፓርቲው ምክር ቤት ስብሰባን አስመልክቶ ለቦርዱ ዝርዝር አቤቱታ ያቀረበ ሲሆን አቤቱታውም፥ ኢዴፓ ሐምሌ 06 ቀን 2011 ዓ.ም አስቸኳይ ፓርቲው ምክር ቤት ስብሰባ ማድረጉን በዚህ ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎች ማሳለፉን እና ያሳለፈው ውሳኔ በቦርዱ እውቅና እንዲያገኝ ቢጠይቅም በቦርዱ እውቅና እንዳላገኘ በዚህም መሰረት የእርምት እርምጃ ወስዶ ጥቅምት 23 ቀን 2012 ዓ.ም በድጋሚ ልዩ አስቸኳይ ስብሰባ ማድረጉን፣ ስብሰባው የተጠራው በምክር ቤቱ አባላት ፒቲሽን መሆኑን፣ የስብሰባው ቀንና ሰአት ስራ አስፈጻሚው በወሰነው መሰረት ማካሄዱን፣ በዚህ ምክር ቤቱ ሁለተኛ ጉባኤ የኦዲትና ኢንስፔክሽን አባላት ተገኝተው ስብሰባውን መታዘባቸውን ከዚሁ ጋር በማያያዝም በቦርዱ የተሰጠው መመሪያ መሰረት በዚሁ አስቸኳይ ስብሰባ ይህንን የእርምት እርምጃ መውሰዱን በመግለፅ በዚህ ጉባኤ የተሰጡ ውሳኔዎች እውቅና አግኝተው ተፈጻሚ እንዲሆኑ ተገቢውን ሁሉ እንዲደረግለት ጠይቋል።

በዚህም መሰረት ቦርዱ ከላይ የተጠቀሱትን ሰነዶች፣ መተዳደሪያ ደንቡን እንዲሁም ቃለጉባኤዎቹን ከመረመረ በኋላ ህዳር 29 ቀን 2012 ዓ.ም ከፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ጋር ውይይት ያደረገ ሲሆን፥ ይህ አስቸኳይ የፓርቲው ብሔራዊ ምክር ቤት ስብሰባ በፓርቲው ህገ ደንብ መሰረት የተከናወነ ስብሰባ መሆኑን ቦርዱ መገንዘቡን ነው የገለፀው።

በመሆኑም ቦርዱ ጥቅምት 23 ቀን 2012 ዓ.ም በተደረገው የፓርቲው ብሔራዊ ምክር ቤት ስብሰባ የተወሰኑት ማለትም የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫ፣ የጠቅላላ ጉባኤ ቀን እና የጠቅላላ ጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ ምርጫ ፣ አራት አባላቱን ከስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እና ከብሔራዊ ምክር ቤት ማሰናበቱ እና ሌሎች ቃለ ጉባኤው ላይ የሚገኙ ውሳኔዎች ህጋዊ ናቸው ብሎ በመወሰን ለሚመለከታቸው አካላት ተገቢውን የትብብር ደብዳቤ በመጻፍ ማሳወቁን አስታውቋል።

(የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ)

Report Page