#ETH

#ETH


እነ ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ የተጠረጠሩበት የወንጀል መዝገብ ተዘግቶ በነፃ ተሰናበቱ!

ከሰኔ 15 / 2011 ዓ.ም ከከፍተኛ መሪዎች ግድያ ጋር በተያያዘ ዋናውን ጉዳይ በማቀነባበርና በመምራት ተጠርጥረው በእስር የቆዩት እነ ብርጋዴር ጀኔራል ተፈራ ማሞ፣ ኮሎኔል አለበል አማረ፣ ኮሎኔል በአምላክ ተስፋ እና ኮማንደር ጌትነት ሽፈራው በተጠረጠሩበት ወንጀል በምርመራ መዝገቡ ላይ ዐቃቤ ሕግ የአያስከስስም ውሳኔ ተሠጥቷል፡፡

ተጠርጣሪዎች በተጠረጠሩበት ወንጀል በጊዜ ቀጠሮ ምርመራው ሲካሄድ ቆይቶ የተጠረጠሩበት የምርመራ ውጤት ዋስትና የማይከለክል በመሆኑ ከጥቅምት 12/2012 ዓ.ም ጀምሮ በ10 ሺህ ብር ዋስትና ተለቅቀው ነበር፡፡

ከዚያ በኋላ በተጠርጣሪዎች ላይ የተደረገው ምርመራ ዐቃቤ ሕግ ተጠቃሎ ደርሶት የምርመራ መዝገቡ ላይ ዐቃቤ ሕግ ክስ ለመመሥረት የሚያስችል የወንጀል ድርጊቱን የማቀነባበር፣ የመምራት እና ኃላፊነታቸው ስላለመወጣታቸው የሚያረጋግጥ የሰውና የቴክኒክ ማስረጃ ባለመገኘቱ በአንፃሩ ወንጀሉ ከተፈፀመ በኋላ ሁኔታውን ለመቆጣጠር ያደረጉት ጥረት በማስረጃ በመረጋገጡ የአማራ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ መስሪያ ቤት ዐቃቤ ሕግ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ አንቀጽ 42 ንዑስ አንቀጽ 1/ሀ/ መሠረት የክስ አይቀርብም ውሳኔ አስተላልፏል፡፡ ለዋስትና ያስያዙት ገንዘብ እንዲመለስላቸውም ወስኗል፡፡

(የአማራ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ መሥሪያ ቤት)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia


Report Page