ETH

ETH

ቲክቫህ ኢትዮጲያ

የጎንደር ዩኒቨርስቲ ማስጠንቀቂያ መስጠቱን ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት DW ዘግቧል!

የጎንደር ዩኒቨርስቲ፣ የመማር ማስተማሩን ሒደት አዉከዋል፣ ተማሪዎቹን ለግጭትና ሁከት አነሳስተዋል፣ ጉዳቶችን አድርሰዋል በተባሉ ተጠርጣሪዎች ላይ የሚደረገዉ ምርመራ ባስቸኳይ ተጣርቶ ዉጤቱ እንዲገለጥ ጠየቀ።የዩኒቨርስቲዉ ሴኔት ከትናንት በስቲያ ባደረገዉ ስብሰባ እስካሁን ወደ ትምሕርት ገበታቸዉ ያልተመለሱ ተማሪዎች እስከ መጪዉ ሰኞ (ታሕሳስ 13 ድረስ) እንዲመለሱ አስጠንቅቋልም።ሴኔቱ እንዳስጠነቀቀዉ ተማሪዎቹ እስከ ታሕሳስ 13 ድረስ ወደ ትምሕርት ገበታቸዉ ካልተመለሱ  በራሳቸዉ ፈቃድ ትምሕርት እንዳቋረጡ ይቆጥረዋል።

የዩኒቨርስቲዉ የሕዝብና የዓለም አቀፍ ግንኙነት ኃላፊ ወይዘሮ ይዳኙ ማንደፍሮ ዛሬ በስልክ እንዳረጋግጡልን በቁጥጥር ስር የሚገኙ ተጠርጣሪዎችን ጉዳይ ዩኒቨርስቲዉ በቅርብ እየተከታተለ ነዉ። ቁጥራቸዉን ግን መጥቀስ አልፈሉጉም። ከእንግዲሕ የዩኒቨርስቲዉን የመማር ማስተማር ሒደት ለማወክ፣ ተማሪዎች «ደሕንነት እንዳይሰማቸዉ» ለማድረግ የሚሞክሩ ወገኖችን ለመቆጣጠር ዩኒቨርስቲዉ ከፀጥታና ከሌሎች «መንግሥታዊ አካላት» ጋር በቅርብ ተባብሮ እየሠራ መሆኑንም ወይዘሮ ይዳጁ አስታዉቀዋል።ወይዘሮ ይዳኙ እንደሚያምኑት የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በተደጋጋሚ የሚጋጩት በተደጋጋሚ እንደሚባለዉ በጎሳና በዘር ተከፋፍለዉ ወይም ስር የሰደደ ጠብ ገጥመዉ አይደለም፤ ተማሪዎችን ለማጋጨት «የተደራጀ» ያሉት ኃይል ግፊት እያደረገባቸዉ ሳይሆን አይቀርም ይላሉ።

ወይዘሮ ይዳኙ እንደዘረዘሩት ማንነታቸዉ በዉል የማይታወቅ ወገኖች በተሰወረ ወይም በማይታይ ቁጥር ለተማሪዎች ሥልክ እየደወሉ ይዝቱባቸዋል፣ ትምሕርት እንዲያቋርጡ አለያም አደጋ እንደሚደርስባቸዉ የሚያስፈራሩ ማስታወቂያዎችን ይለጥፋሉ፣ ሌላ አካባቢ የተፈፀሙ ግድያ፣ግጭትና ድብደባን ጎንደር ዩኒቨርስቲ የተፈፀሙ እያስመሰሉ ፎቶ ግራፎችንና መልዕክቶችን በማሕበራዊ መገናኛ ዘዴ ያሰራጫሉ። ዩኒቨርስቲዉ የተማሪዎችን ደህንነት ለማስከበር፣ ችግር ፈጣሪዎችን ለመቆጣጠርና ከዚሕ ቀደም የታዩ ግጭቶች እንዳይደገሙ ለመከላከል «የዩኒቨርስቲዉ አመራሮችም፣ ከፍተኛ ማኔጅመንቱም፣ ሁሉም «እጅና ጓንት» ሆኖ ይሰራል ይላሉ ወይዘሮ ይዳኙ።በዩኒቨርስቲዉ ቅጥር ግቢዎች ቁጥራቸዉ አነስተኛ ቢሆንም የፌደራል ፖሊስ ባልደረቦች መስፍረቸዉንም አረጋግጠዋል።

(DW)

Report Page