ETH

ETH

ቲክቫህ ኢትዮጲያ

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በዘንድሮ አመት ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እያከናወነ ይገኛል፡፡ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ከቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ምን ይማሩ ይሆን?

እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ዩኒቨርሲቲው ሠላም ርቆት ከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደ ነበር ይታወሳል ለመሆኑ ዘንድሮ ምን ተሰራ  የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጫላ ዋታ የሚከተለውን ገልጸዋል፡-

በዩኒቨርሲቲው ሠላማዊ የመማር ማስተማር ሥራ ለማስቀጠል ለነበሩ ችግሮች ቅድሚያ ተሰጥቶ በጥልቀት የሁኔታ ትንተና በማድረግ የህግ የበላይነት እንዲከበር ተደርጓል፡፡ ከዚህም ባለፈ ችግሮቹን በመለየት ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር ተነጋግሮ ሃላፊነት ሰጥቷል፣ በየደረጃው ያሉት አካላትም የተሰጣቸውን ሃላፊነት ለቅመው በመሥራትና ውጤቱንም በጋራ በመገምገም በሠላም መስፈን ውጤታማ እንደሆኑ ፕሬዝዳንቱ ይገልጻሉ፡፡  ተማሪዎችና ዩኒቨርሲቲው በጋራ በደረሱበት ስምምነት ከፌዴራልና ከክልል የተውጣጡ የጸጥታ አስከባሪ አካላት ከዩኒቨርሲቲው ፖሊስ ጋር በጥምረት በሠላም ማስጠበቅ ሥራ ላይ መሰማራታቸው፣ በሌላ ጎን የአካባቢው ማህበረሰብ በባለቤትነት ስሜት ዩኒቨርሲቲውን ነቅቶ መጠበቁ ሠላም እንዲሰፍን መርዳቱን ዶ/ር ጫላ ገልጸዋል፡፡

ያልተገባ ስነምግባር ለማሳየት የሞከሩ ሠራተኞችና ተማሪዎች ላይ በጋራ በቃል ኪዳኑ ሰነድ መሠረት

ከምክር እስከ ዲስፕሊን ጥሰት እርምጃ እንደሚወሰድ በዚህም ዩኒቨርሲቲው 3 ተማሪዎችን ከትምህርት ገበታ ማሰናበቱን፣ ሌሎች የጥፋት ሙከራዎችን በእንጭጩ በማጨናገፍ የጥፋተኞችን ስም እና የፈጸሙትን ጥፋት ማስታወቂያ ቦርድ ላይ በመለጠፍ አጥፊዎቹ እንዲታረሙ፣ ሌሎቹ እንዲማሩ ተደርጓል ብለዋል፡፡ ለደንብ ጥሰት ጉዳዮች የተቋቋመው የለውጥ ኮሚቴ የሚቀርብለትን ሪፖርት ተመርኩዞ ጉዳዩን መርምሮ እርምጃ ይወስዳል፣ ከኮሚቴው ሃላፊነት በላይ የሆነ ጉዳይ ለዩኒቨርሲቲ ማኔጅመንት ቀርቦ ብያኔ ይሰጠዋል ብለዋል ዶ/ር ጫላ፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ለተማሪዎች ደህንነት ሲባል እንደ አስፈላጊነቱ በማንኛውም ሰዓትና ቦታ ዶርሚተሪ ጨምሮ ድንገተኛ ፍተሻ እንደሚደረግና፣ የተለያዩ ክፍሎች የማጥራት ሥራም እንደሚሰራ የገለጹት የዩኒቨርሲቲው አለም አቀፍና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ናቸው፡፡

Report Page