#ETH

#ETH


እንደ ዶ/ር ሙላቱ አለማየሁ ገለጻ የሚዲያው ዘርፍ በሀገራችን ከተጀመረበት 1992( እ.ኤ.አ ) ጀምሮ ብዙ ውጣወርረዶችን ማለፉን ይጠቅሳሉ፡፡ አንድ ጊዜ የህዝብን ድምጽ ሌላ ጊዜ ደግሞ የመንግስትን ድምጽ በማሰማት አልፎ አልፎ ገለልተኛ ሆነውም ለመዘገብ ሲሞክሩ ዘመናትን አልፈዋል፡፡ መንግስትም ለዘርፉ እድገት እንዲሁም ለሞያው ክብር ማነቆ የሆኑ ህጎችን ሲቀርጽ አንዳንዴም ከዛ በተቃራኒው ህጎችን ሲያሻሽል ቆይቷል፡፡የሚዲያዎችን ጉዳይ የመቆጣጠር ኃላፊነት የተሰጠው የኢትዮጵያ የብሮድ ካስት ባለስልጣንም እስካሁን በተሰጠው ስልጣን ለመጠቀም ሲሞክር ቆይቷል፡፡ 


አሁን ላይ ግን የሚዲያ ነጻነትን ማስከበር በመንግስት ብቻ ሳይሆን እስከ ህዝቡ ዘልቆ የሚገባ ጉዳይ ሆኗል፡፡ ጋዜጠኛ መብቱ ሳይረገጥ የመዘገብ መብቱ እንደተጠበቀ ሆኖ የህብረተሰቡንም ትክክለኛ መረጃ የማግኘት መብት መጣስ የለበትም፡፡ ሀገራችንን ወደፊት ሊያሻግሯት ከሚችሉ ጠንካራ ተቋማት መካከል አንዱ ሚዲያ ለመሆኑ ክርክር የለውም ይህንን የምንመራበት መንገድ ግን ሞያዊ ስነ-ምግባሩን በጠበቀ ትክክለኛ፣ ታማኝ፣፡ሚዛናዊ፣ ፍትሐዊ፣ ምሳሌያዊ መርሆዎችን ተጠቅሞ እንዲራመድ ካልስቻልነው ጉዳቱ የዛኑ ያህል የከፋ ይሆናል፡፡ 

የሚዲያ ካውንስል ተቋቁሞ የደስራ መግባቱን የሚገልጹት የካውንስሉ ሰብሳቢ አቶ አማረ አረጋዊ ይህ ካውንስል ሞያው የሚደርስበትን ጫና ለመቋቋምና ሚዲያዎችም የስነምግባር ህጉን ተከትለው እንዲሰሩ ያስችላቸዋል ብለው ይገልጻሉ፡፡ ከዚህ ቀደም ቅሬታዎች የሚስተናገዱት በሞያው ስነ-ምግባር የመጨነቅ ጠንካራ ማህበር ባለመኖሩ ማሰር እንደ መፍትሔ ሲቆጠር ቆይቷል ሲሉም ይገልጻሉ፡፡ አሁን ላይ ካውንስሉ ከማሰር በተሻለ መንግስትንም ሆነ ሚዲያዎችን በቅድሚያ ተጠያቂ ማድረግና ከየትኛውም ወገን ቅሬታን መቀበል ካውንስሉ ሊሰራቸው ካሰባቸው ስራዎች አንዱ ነው፡፡ 

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ም/ዋ/ዳ/ አቶ ወንደሰን አንዷለም በበኩላቸው ባለስልጣኑ ከዚህ ቀደም ሳይንሳዊ መንገድ አልተከተለም አሁን ላይ ሳይንሳዊ መንገድ በመከተል ለሚዲያ ተቋማት አለማቀፍ ስልጠናዎችን ጭምር እያመቻቸ ይገኛል ሲሉ ይገልጻሉ፡፡ በአንጻሩ የጥላቻና ሀሰተኛ መረጃዎችን በሚለቁ ሚዲያዎች ላይ ጠንከር ያለ እርምጃ እንደሚወሰድም ገልፀዋል፡፡

በአጠቃላይ ሚዲያዎችን በሙሉ በአንድ ላይ መኮነንም ሆነ በአንድ ላይ ተጠያቂ ማድረግ ለሚፈጠሩ ችግርች ሁሉ ወደ ሚዲያው ጣት መቀሰር የሚያሳስብ ለመሆኑ ዛሬ በነበረው የአዲስ ወግ ዝግጅት ላይ የተነሳ ሀሳብ ነው፡፡ ዝግጅቱ ከሰዓትም ሲቀጥል በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ትኩረቱን ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

#TIKVAH

Report Page