ETH

ETH

ቲክቫህ ኢትዮጲያ

ዩኒቨርሲቲው የሙያ ማበልፀጊያ ማዕከላትን በሁሉም ካምፓሶች ሊያቋቁም ነው

ተማሪዎችን ከመጀመሪያ ዓመት እስከ ምርቃ ድረስ ለሥራው ዓለም የሚያዘጋጁ የሙያ ማበልፀጊያ ማዕከላት በቅርቡ በዩኒቨርሲቲው ሁሉም ካምፓሶች እንደሚቋቋሙ ተገለፀ፡፡

የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝደንት ዶ/ር የቻለ ከበደ እንደገለፁት ማዕከላቱ  ተማሪዎች ተመርቀው ከወጡ በኋላ የሚያጋጥማቸውን የሥራ ላይ ክሂሎት ክፍተት ለመቅረፍ ወደ ዩኒቨርሲቲ ከገቡ ቀን ጀምሮ  የተለያዩ ሥልጠናዎችንና ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት ተማሪዎቻችንን በክሂሎትም ሆነ በሥነ-ልቦና የሚያዘጋጁ ናቸው ብለዋል፡፡

ማዕከላቱ ተማሪዎቻችንን ተወዳዳሪና ብቁ በማድረግ 80 በመቶ የዩኒቨርሲቲያችን ምሩቃን በተመረቁበት አንድ ዓመት ውስጥ ሥራ እንዲይዙ ለማድረግ የተያዘው ዕቅድ እውን ለማድረግ ያግዛሉ፡፡ ከዚህም ባሻገር ማዕከላቱ ከተለያዩ ቀጣሪ ኢንዱስትሪዎች ጋር ስምምነቶችንና ግንኙነቶችን በመፍጠር ለተመራቂዎቻችን የሥራ ዕድሎችን የሚያመቻቹ እንደሚሆኑ ዶ/ር የቻለ ገልፀዋል፡፡

ለሁሉም ተመራቂ ተማሪዎች መንግስት የሥራ ዕድል መፍጠርና መቅጠር አይችልም ያሉት ዶ/ር የቻለ ማዕከላቱ ተማሪዎቹ ከዚህ አስተሳሰብ ወጥተው በራሳቸው ሥራ ፈጣሪ እንዲሆኑም ይሠራሉ ብለዋል፡፡

ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት


              

Report Page