#ETH

#ETH


የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠ/ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አይሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ለሚደረግላቸው የክብር አቀባባል ሥነ-ሥርዓት የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይከሰት አሽከርካሪዎች የተለመደውን ትብብር እንዲያደርጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጥሪውን አስተላለፈ፡፡

ታህሳስ 02/2012 ዓም የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠ/ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የኖርዋይ ኦስሎ ቆይታቸውን አጠናቅቀው አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አይሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በሚደረግላቸው የአቀባበል ሥነ-ሥርዓት ላይ በርካታ የከተማችን ነዋሪዎች እና የውጭ ሀገር ዕንግዶች በተገኙበት የአቀባባል ሥነ-ሥርዓት ስለሚደረግ በመንገዶች ላይ የትራፈክ መጨናነቅ አንዳይከሰትና አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ኮሚሽኑ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

በዚህም መሠረት፡-ነገ ታህሳስ 02 ቀን/2012 ከለሊቱ 11፡00 ሰዓት ጀምሮ የአቀባበል ሥነ ሥርዓቱ እስከ ሚጠናቀቅ ድረስ ከአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አይሮፕላን ማረፊያ ጀምሮ እስከ ብሔራዊ ቤተ-መንግስት ባሉት ግራና ቀኝ መንገዶች ላይ ተሸከርካሪን ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓት ማቆም የተከለከለ ሲሆን ፡-አሽከርካሪዎችም አማራጭ መንገድ እንዲጠቀሙ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

 ከኡራኤል ቤ/ክርስቲያን ወደ መስቀል አደባባይ

 ከቦሌ ዓለም አቀፍ አይሮፕላን ማረፊያ ወደ መስቀል አደባባይ

 ከቦሌ ኤድናሞል ወደ ቦሌ ዓለም አቀፍ አይሮፕላን ማረፊያ

 ከብሔራዊ ቤተ-መንግስት ፤ ከፍል ውኃ ፤ ከለገሀር ፤ከካሳንችስ፤ከሳንጆሴፍ ትምህርት ቤት ፤ከስታዲየምንና ከሃራምቤ ሆቴል አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስዱ መንገዶች ለጊዜው ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

አሽከርካሪዎች በሥራላይ ያሉ የፀጥታ አካላት የመንገድ መረጃን በመጠየቅና ሌሎች አማራጭ መንገዶችን በመጠቀም የተለመደ ትብብራቸውን እንዲያደርጉ ኮሚሽኑ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠ/ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ለሠላም መስፈን ላበረከቱት አስተዋጽዎ የተበረከተላቸው ሽልማት ለመላው ሠላም ወዳድ ኢትዮጲያዊያን የተበረከተ ሽልማት በመሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ለመላው የሐገራችን ህዝቦች የእንኳን ደስ አለን መልካም ምኞቱን ይገልጻል ፡፡

ህብረተሰቡ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘት እና መረጃ ለመስጠት በስልክ ቁጥሮች ፡- በ011-1-11- 01-11 ፣011-5-52-40-77 ፣011-5-52-63-02 ፣011-5-52-63-03 ወይም በነጻ ስልክ መስመር 991 እና 987 መጠቀም እንደሚቻል ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

Report Page